>
5:18 pm - Saturday June 15, 3574

አንዳርጋቸዉ ጽጌ፡-  በሶስት ጸረ ኢትዮጵያዊነት ሀይላት የአዕምሮ እጥበት የተደረገበት ሰዉ!!! (ሸንቁጥ አየለ)

አንዳርጋቸዉ ጽጌ፡- 

በሶስት ጸረ ኢትዮጵያዊነት ሀይላት የአዕምሮ እጥበት የተደረገበት ሰዉ!!!

ሸንቁጥ አየለ
1. አንዳርጋቸዉ ጽጌ መጀመሪያ የኢህዴን/ ብአዴን ባለስልጣን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጸሃፊ ነበር። ይሄን ሹመት ወያኔ ለአንዳርጋቸዉ ጽጌ ስትሰጠዉ የአዕምሮ እጥበት አድርጋበት ነዉ። በዚህም ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ አላት ፡ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተፈጠረች ነች እያለ የጻፈ ሰዉ ነዉ።
2.  አንዳርጋቸዉ ጽጌ ቅንጅት አማራ በዛበት ብሎ ከሌሎች ጸረ አማራ ሀይሎች ጋር ሆኖ ቅንጅት እንዲፈርስ ትልቅ አስተዋጾ አድርጓል። ቅንጅትን በማፍረስም ግ7 የተባለ ድርጅት መስርቶ ሻቢያ ኪስ ዉስጥ በመግባት ከኢሳያስ አፈወርቂ እና ተስፋዬ ገብራብ ጸረ ኢትዮጵያዊነትን እና ጸረ አማራነትን በደንብ ተምሯል።
በዚህም “ኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ጽንፍ መያዝ የለበትም። ጽንፈኛ ኢትዮጵያዊነት የአማራ አስተምህሮት ነዉ። አማራው ከኢትዮጵያ ስልጣ ተገሎ ወደኋላ መሆን አለበት” እያለ አስተምሯል።
 ለምሳሌ ተስፋዬ ግብረ እባብ በጻፈዉ አንድ ጽሁፉ ዉስጥ  ”  ኢትዮጵያ የሚለዉ በቅኝ ግዛት የተፈጠረ ሀገር መሆኑን ተወያዬንበት። ኢትዮጵያ የሚለዉን ነገር ኢንዲረሳዉ ተከራከርንበት” ሲል ጽፏል።
3. አሁን በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ኦነጋዉያን በአንዳርጋቸዉ ላይ የ አዕምሮ እጥበት አድርገዉበታል።
አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ የመጀመሪያ መጽሃፉ እኔ አማራ ነኝ ብሎ የጻፈ ሰዉ አሁን በጻፈዉ መጽሃፉ ደግሞ “ኦሮሞ ነኝ ። አማራ የሚባልም ህዝብ የለም” ብሎ መጻፉ ሰዉዬዉ ምን ያህል ተከታታይ የአዕምሮ እጥበት እና ግራ መጋባት ዉስጥ እንደገባ ግልጽ ነዉ።በዚህም አሁን በጻፈዉ ጽሁፉ እራሱን እንደገና ጠፍጥፎ ፈጥሮ አማራነቱን ክዶ እንዴዉም አማራ የለም በማለት እኔ ኦሮሞ ነኝ እስከ ማለት ሄዷል።
 4. በዚሁ ትዉልድን ለማደናገር በጻፈው ሶስተኛ መጽሃፉ ዉስጥ እስልምናን በፍትህ ተቀብላ በታላቅ አክብሮት ህልዉናዉ እንዲጠበቅ ያደረገችዉን ጥንታዊት ኢትዮጵያን ይከሳታል።
ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች መሃከል ጥላቻን ይረጫል። ነጻነት እማያዉቅ ነጻዉጭ በሚለዉ መጽሃፉ ዉስጥ ተዋህዶን ለማጥፋት የተራመደበትን ክስ ” እኛም እንናገር ትዉልድ እንዳይደናገር” ብሎ ትዉልድ ለማደናገር በጻፈዉ መጽሃፉ ደግሞ ይበልጥ የኢትዮጵያ ጠላት ያደርጋታል።
5.  ይሄን በሶስት ጸረ ኢትዮጵያዊነት ሀይላት የአዕምሮ እጥበት የተደረገበትን ሰዉ ተከትለዉ የሚራወጡ አንዳንድ አማሮች ፡ አንዳንድ ኦርቶዶክሶች እና አንዳንድ ኢትዮጵያን እንወዳለን የሚሉ ሰዎች አንዳርጋቸዉ በሶስቱ መጽሃፎቹ ምን መርዝ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደጋተዉ ቁጭ ብለዉ አንብበዉ ቢመረምሩ በራሳቸዉ በጣም ያፍሩ ነበር።
Filed in: Amharic