>

ኣምባሳደር ኣውዓሎም አአ ቦሌ ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤትበግድ ውጣ ተባለ!!!  (ኣስገደ ገብረስላሴ) 

ኣምባሳደር ኣውዓሎም አአ ቦሌ ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤትበግድ ውጣ ተባለ!!! 

 

 

ከኣስገደ ገብረስላሴ 
የቀድሞ የኢህኣደግ በኤርትራ  ባለ ሙሉ ስልጣን   አምባሳደር ኣውዓሎም ወልዱ  የዓረና ትግራይ ማእከላይ ኮሚቴ ፣ የኢትዮጱያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክርቤት የሆነው  ፤ በትግራይ ያሉ የኣረና ትግራይ  ኣባላት  በህዋሓት አማራርና ካድሬዎቹ ያጋጠማቸው  ያለው ግፍና መከራ ፣በሀገራቸው አንደኛ ዜጋ መሆን ተስኖዋቸው። እንደ  2ኛ ዜጋ ሆነው፤ ቤት ተካራይተው እንኳን የማይሩባት ትግራይ እንደሆነችባቸው ሁሉ ፤ ኣምባሳደር ኣውዓሎም ወልዱም የጓዶቹ እጣ ፈንታ ደርሶት ተከራይቶ ከሚኖርባት የኪ /ቤቶች ቤት ውጣ ተብሎ በጭንቀት ላይ  እተንከራተተ ይገኛል ። !በሁለት ስርኣቶች የተገደለ  ፍጡር   ።
አንባሳደር ኣውዓሎም ወልዱ በ1967 ዓ ም   ጸረ ደርግ ትግል ጀማሪዎች ወደ ትጥቅ ትግል የዘመተ  ኣንዱ ሆኖ፤  ከ 1971  ዓ ም  እስከ 1993 ዓ ም  ከማ / ኮ እስከ ስራ ኣስፈጻሚ(ፖሊት ቢሮ)  በመሆን ህወሓት ኢህአደግን መርቷል  ። ነገር ግን ለ17 ኣመት ታግሎ ደርግ ተሸንፎ ከስልጣን ከተወገደ በኃላ እስከ 1990 ዓ ም  የኤርትራ የኢትዮጱያ ሙሉ  ኣንባሳደር ባለስልጣን ሆኖ ሰርቷል።
አንባሳደር ኣውዓሎም ወልዱ  ህዋሓት ኢህአደግ ሆኖ ከ1967 ዓ ም እስከ 1993  ለ27 አመት እየመራ ከቆዬ በኃላ በወቅቱ በሀሳብ ልዩነት የህ  ዋ ሓ ት  ማ /ኮሚቴ መሰናጠቅ ጋር ተያይዞ  በመለስ ኣንባ ገነን  ስርአት እና አማራር ያለኣንዳች ርህራሄ  የጥሮታ ኣበልና ፣የአገልግሎት ክፍያ ወይ የክብር ስንብት ቁራጭ  ነጭ  ወረቀት  እንኳን ሳይሰጠው በመባረሩ ፣እስከ ኣሁን ልጆቹ ለማሳደግ በኣንድ ህንጻ ተቋራጭ በኣንስተኛ ክፍያ እየሰራ ንሮውን እየገፋ ቆይቶዋል ።  ኣንባሳደር ኣውዓሎም በህዋሓት ኣማራሮች ያለኣንዳች ክፍያ ማባረራቸው ብቻ ኣይደለም የበደሉት በህንጻ ተቋራጩ ተቀጥሮ ሲሰራም አሰሪው እንዲያባርረው ግፊት ያደርጉበት ነበር ።ህንጻ ተቋራጩ ግን ቦታ ኣልሰጣቸውም ።
ኣንባሳደር ኣውዓሎም  ወልዱ ሁሉም የህዋሓት ኢህኢደግ ኣማራር ፣ካድሬዎቻቸው ፣  እንዲሁም ኣንባሳዶሮች ፣የክልልል አስተዳዶሮች የክልልና የአዲስ ኣበባ የከተማ መሬት ስልጣናቸው በመጠቀም  ተቀራምተው ወረው  ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ቢላዎች ከዛም ኣልፎው የትላልቅ ኩባንያዎች ባለቤቶች በመሆን ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ቢሊዮኖሮች ሆነው የሀገራችን ገበያ ጠቧቸው በውጭ አገር ትላልቅ ኩባንያዎች ኣቋቁመው የኣለማችን ትጃሮች ጋር ተዋዳዳሪ ሆነዋል ።
አንባሳደር አውዓሎም ወልዱ  ከሱ  ጋር አምባሳደሮች ፣ሚኒስቲሮች የቢሮ ሀላፊዎች ከነሱ ጋር ቁርኝት የነበራቸው ጥገኛ ካድሪዎች ፣የጦር፣የፖሊስ መኮኖኖች ፣የድህንነት ባለስልጣን መሪዎችና ሰራተኞች ፣በአዲስ ኣበባ ፣ኣዳማ ፣ባህርዳር ፣ ጎንደር  ፣ጅማ ፣ኣዋሳ ፣ባህርደር ፣ደብረማርቆስ ፣ደብረብርሀን ፣ደሴ ፣ኮንቦልቻ ፣በመቐለ ፣በኣክሱም ፣ሽረ እንዳስላሴ ፣በዓድዋ ፣በዓዲ ግራት ፣ በውቅሮ በድሬዳዋ ፣ጅጅጋ፣ ሀረር ፣ ወዘተ በራሳቸው በራሳቸው ስልጣን (በየኣካባቢው ከሚገኙ ባለስልጣናት በመሻረክ ) ከሁለት እስከ ኣምስት ህንጻዎች ፣በተጨማሪም በሌላ ሰው ስም  በማስመሰል ሀገራችን ሲቆጧጠሯት ። *( ኣንባሳደር ኣውዓሎም ግን በመላው የሀገራችን ከተሞች በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ መሬት ይሁን ቤት የለውም)።ኣንባ ሳደር ኣውዓሎም በሁሉም መስፈርት በሙሱና ፣በወገናውነት በዘመድ ኣዝማድ ፣በከባባዊነት ፣ በጥቀመኝ ልጥቀምህ ፣ በዘር በሀይማኖት የማይታማ መሆኑ ፣በሁሉም ኣካባቢ የሚገኙ ከኢህአደግ  የተባረሩ ፣ማለት የህ ዋ ሓ ት ፣የባኤዴን የኦሆዴድ ፣የደሂደን ፣የኣጋር ፓርቲዎች  ኣማረር ፣እንዲሁም የኣሁኑ የለውጢ ሀይሎች ባዮች እጅግ ጥቂት ግለሰዎች  ይኖሩ እንደሆን እንጅ  ፤ሌሎች ግን ሁሉም ለማለት ይቻላል በሁሉም መስፈርት የበሰበው  ኢህኣደግ ታማኝ ካድሪዎች በመሆን ሰው ብሉ ከተባሉም የሚጨክኑ የነበሩ  ተዋናኝ ታማኝ ካድሬዎች  ስለነበራችሁ። ለአንባሳደር ኣውዓሎም ከለብሱ ጀምራችሁ በቅንነት በሚስኪንነቱ ቷውቁታላችሁ  ።ራሳቸው የጠ/ ም ብልጽግና ፓርቲ ኣማራሮች ካድሬዎችም የኢህኣደግ ኣባል በነበራችሁበት ከሁለት ቤት በላይ ኣላቹሁ ።ምናልባችም በዘመነ ጠ/ ምኒስቴር ኣብይ ኣህመድ ያልተማእከለ ገንዘብ ኣዋጣጥ ምክንያት እጅግ ቡዙ ቢሌን ገንዘብ  በመበተን ስላለ  ከዛም ከዚህ እያላችሁ  ጨምራችሁበት ትሆናላችሁ ።በተጨማሪም የፈረሰው ኢህኣደግ ለጋሲ በመከተል የግል ቤታችሁ እያለ በመንግስት ቤት እየኖሯችሁ ኪራይ ቤት እየዛቃችሁ እንደምትኖሩ የኢትየጱያ ህዝቦች ሁሉ  ኣበጥረው ያውቃሉ ።
የኣሁኑ ይባስ ኣምባሳደር ኣውዓሎም  ወልዱ  ለሀገራችን የሚጥቅም የዲሞክራሲ መንገድ በመያዙ  (በማፍለቁ )በመለስ የተቀጠቀጠው እና ዜግነቱ የተነጠቀው አልበቃም ብሎት ፤ኣሁን ደግሞ የአብይ ኣህመድና ካድሬዎቹ በዚሁ እድሜው  በአዲስ ኣበባ ወረዳ 24 ቀበሌ 20 አካባቢ የሚገኝ ኣሮጌ የክራይ ቤቶች 28 አመት ከኖረበት በኃላ የኪራይ ቤቶች ባለስልጣኖች ነን ባዮች መጥተው  ያለአንዳች ማስጠንቀቅያ  ውጣ ብሎውታል ።እዋ በኣሁኑ ጊዜ የት ይውደቅ ። ኧረ ጎበዝ ለምትሰሩት ስራ በግብታውነት ከምትጋልቡ ቆም ብላችሁ አስቡ ።የግለሰው መብት እናከብራለን የምትሉን የቱ ላይ ነው ።(ቤቱ  አስፈልጉዋቸው ከሆነ ደግሞ  ይህ ቤት መንግስት ስለፈለገው ቅያሪ እንሰጣሀለን ማለትም እኮ ጨዋነት ነው ። ያለቅያር ቤት በጠራራ ጸሀይ ና ውጣ ማለታቸው ሁለተኛ የቁም ግድያነው ።
በክራይ ቤትች ወይ በቀበሌ ቤት ይኖሩ የነበሩ ሚሌኖች ህዝቡች እኮ መንግስት ኮንደምኔም ሊሰራበት ስለፈለገ ከተፈላጊ ቦታ ኣንስቶ ሲወስደደቸው በተሰራ ኮንደምኔም ወይ ሌላ ቂያሪ ሰጥቶ ነው ስለዚህ በኣንባሳደር አውዓሎም ወልዱ እየወሰዳቹሁ ያላችሁ እርምጃ  ኣሮጌው ኢህደግ የፈጸመው ኢሰባኣዊ ስራ ፤ኣሁን በወጣቱ ኢህኣደግ የሚወሰደው ያለው እርምጃ  ሁለተኛ ዝዋሪ ወገምት ነው ።
                              መቐለ ፤
                       28  / 07  / 20  12
            እርስ በእርሳችን ከምንባላ ከምንወናጀል ! !
     ሊበላን እየመጣ ላለው ሰው በላ ኮረና ቫይረስ ወረርሽን  !
      ለመከላከል  ለማጥፋት በህብረት እንረባረብ ! !
Filed in: Amharic