>
9:07 am - Wednesday December 7, 2022

ታሪኩ አበራ ማነው? [ዘመድኩን በቀለ (ክፍል 1,2,3)]

ታሪኩ አበራ ማነው?

 

ዘመድኩን በቀለ
“ ግሪታዴ” ታሪኩን አበራን ላስተዋውቃችሁ። ግሪታዴ ማለት ግሪ ግሪሳ፣ ታዴ ተሃድሶ ሲቆላመጥ ነው። ግሪታዴ ታሪኩ አበራ ማነው?
•••
ከዓደዋ ትግራይ ተመድቦ በመጣው ዳኛ የተሰየመው የአራዳ ምድብ 6 ተኛ የወንጀል ችሎት አይተ ሙሉ ጊደይን የመሃል ዳኛ አድርጎ ተሰይሟል። በተከሳሽ ጠረጴዛ ውስጥ እኔ ዘመዴ ቆሜያለሁ። ጠበቃዬ አቶ ጌትነት እና የከሳሼ ጠበቃ የሆነው የመንግሥት ዐቃቤ ሕግም ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። ጓደኞቼና ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ሠራተኞችም በሙሉ በችሎቱ ታድመዋል። ክሱ አስቀድሞ በጋዜጦችና በመጽሔቶች ጡዞ ስለነበር ተመልካቹ ብዙ ነበር።
•••
ባለፉት ችሎቶች ትግሬው ዳኛና እኔ በችሎቱ ውስጥ አልተግባባንም ነበር። እናቴ ሞታ ሐረርጌ ሔጄ አንድ ችሎት አምልጦኝ ነበር። እናም ፖሊስ አስሮ እንዲያቀርበኝ ሲታዘዝ ፖሊስ ትእዛዙን ተቀብሎ አስሮ አላቀረበኝም ነበር። እናም ዳኛው ፖሊስን ለምን እንዳላሰረኝ ሲጠይቀው የእናት ሞት ሀዘን ላይ ነበር እናም ለዛሬ እንዲቀርብ ነግረን ተመልሰናል። ልጁ ካለው ማኅበራዊ ኃላፊነትና ሥነ ምግባር አንጻር ብዙ ልንጫነው አልፈለግንም። በመሆኑም ጥፋቱ የእኛ ነው። ታላቅ ይቅርታም ክቡር ፍርድቤቱን እንጠይቃለን ይላል ፎሊስ ነፍሴ ።
•••
ትግሬው ዳኛ አበደ። ጦፈ። ለምንድነው?  ያላሰራችሁት ነው እያልኩ ያለሁት? ለምን ታስሮ አልቀረበም? እኔ ስለ እሱ እናት ሞት ምን አገባኝ። ወዘተ ብሎ አበደ። ፖሊስ አሁንም በትህትና መልሶ ይቅርታ ጠየቀ። እኔ ዘመዴ እስከዚህ ሰዓት ድረስ በትእግስት ነበር የምሰማው። ትግሬው ዳኛ ግን አላቆመም። ቀጥሎም የማያውቃትን ሟች እናቴን አምባሻ በቀደደው አፉ ዝምብሎ መዘርጠጥ ጀመረ። ከዚህ በላይ መታገስ አልቻልኩም። ደግሞስ ምንአባቱ ይመጣል አልኩና ያን በኮታ ተሹሞ የመጣን ገመድ አፍ አማርኛ እንኳ በቅጡ መናገር የማይችል የህወሓት አሽከር ዳኛ ትንፋሽ እስኪያጥረው ድረስ ተግትጌ አፉን አስያዝኩት። የፍርድ ቤቱ ታዳሚ ጭምር ስሜቱን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ ነበር የተናገርኩት። ደግሞም በእናቴ ሞት በመሳለቁ ሳላስበውም አለቀስኩ። ታዳሚውም ሁሉ አለቀሰ። ዳኛው ደነገጠ። ፖሊሶቹም ደስ ሲላቸው አያለሁ። ከዚያን ዕለት ጀምሮ እኔ የሐረር ቆቱው ዘመዴና የዓድዋው ትግሬ ዳኛ ችሎት ውስጥ ሙግታችን ለተመልካች ግሩም መዝናኛ ሆኖ ቀጠለ።
•••
የዛሬው ቀጠሮ የከሳሽ የአቶ በግዋሻው ደሳለኝ ምስክሮች የሚሰሙበት ዕለት ነው። ምስክሮቹን ለማየትም ለመስማትም ማንነታቸውን ለማወቅም ጓግተናል። እናም ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ የምስክሮቹን ስም ተራ በተራ እየጠራ አስተዋወቀ።
1ኛ፥ ታሪኩ አበራ
2ኛ፥ ሙሴ ምናምን
3ኛ፥ ናትናኤል ቴቬዝና
4ኛ፥ ፓስተር አሰግድ ሳህሉ እንደሆኑ ተናገረ።
•••
የታሪኩ አበራና የሙሴ ሲገርመኝ የ4 መንታው የጊዮርጊስ ክለብ አስጨሻሪው የናትናኤል ቴቬዝና የፓስተር አሰግድ ሳህሉ አልገረመኝም ነበር። የታሪኩንና የሙሴን ምስክርነት ግን ለመስማት ቋምጯለሁ።
•••
ታሪኩ አበራ ማለት ወዶ ገብ ቀጭን ጴንጤ ነው። በወቅቱ መናፍቅ ለመሆን መከራውን የሚበላና ከሚገባው በላይ እየተጋጋጠ የነበረ ሥጋ ቅብ ጴንጤ ነበር። መርካቶ ሰባተኛ ተወልዶ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ያደገም ምስኪን አዲስ አበቤ ነው። ኮልፌ ልብስ ስፌት፣ አውቶብስ ተራ አካባቢም መጋዘን ከፍቶ ለማደግ ይጣጣር እንደነበር ሰምቻማለሁ። ታሪኩን የማውቀው ኮሌጅ ገብቶ ሰባኪ ለመሆን ሲለማመድ ነበር።
•••
እንደ ብዙዎቹ ሰባክያነ ወንጌል ታሪኩም በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምህረት በኩል እንደነ መምህር ዘላለም ወንድሙ ዓለምን መዞር ህልሙ ነበር። እንደ መምህር ዘበነም ሀብታምና ዝነኛ መሆን፣ እንደ መምህር ምህረተ አብም ታዋቂ መሆን፣ እንደነ በግዋሻው፣ ዘራፊና ትዝታው ኢንቬስተር መሆን ይመኝ የነበረ የዋሕ ነበር። ታሪኩ በዚህም አለ በዚያ ነጭ ድህነቱን አሸንፎ ምስኪን እናቱን መርዳት እንደሆነ ዓላማውን አውቃለሁ። እናም ዛሬ ለበግዋሻው ተደርቦ ሊመሰክርብኝ መምጣቱን ሳይ ምን ሊል እንደሆነ ጓጉቻለሁ። ልብ በሉ ታሪኩ አሰላለፉ ከበጋሻው፣ ከአሰግድ፣ ከትዝታውና ከዘርፌ ጋር ነው።
•••
የሆነ ቀን የእጅ ስልኬ ይጠራል። ሃሎ ታሪኩ አበራ ነኝ። የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ ነኝ። አንድ መጽሐፍ አዘጋጅቿለሁ። እየውና በአንተ በኩል ታትሞ ለህዝብ ቢደርስልኝ ይለኛል። መጽሐፍ የራሴን እንጂ የሰው እንደማላሳትም ነገርኩት። “የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች” በሚለው የበግዋሻው ደሳለኝ መጽሐፍ ጀርባ ላይ የእኔ መዝሙር ቤት ስም መጠቀሱን ይነግረኛል። አዎ ልክነህ ስለዚያ መጽሐፍ ግን የማውቀው ነገር የለም። በግዋሻው ያለፈቃዳችን ነው የብዙዎቻችንን የመዝሙር ቤቶች ስም ያስገባው፥ እናም አላሳትምም እለዋለሁ። የግድ ሲለኝ ባይሆን ልመልከትልህ ብዬው በሽት የተዘጋጀ የመጽሐፉን ቅጂ ይሰጠኛል። አየሁት። እናም ጠርቼው ተነጋገርን። መጽሐፍህ የኢህአዴግን የ5 ዓመት የልማት ዕቅድ ነው የሚመስለው። ይሄ የመንግሥት ፖሊሲ ነው የሚመስለው። ለህዝበ ክርስቲያኑ የሚጠቅም ነገርም የለምውም። ባይሆን በእመቤታችን፣ በክርስቶስ አምላክነት ዙሪያ ሲዲ ቪሲዲ አዘጋጅ። እሱ ለብዙ ነገር ይጠቅምሃል። አንደኛ ገቢም ታገኝበታለህ ምእመናንንም ታስተምርበታለህ። ሁለተኛው ደግሞ ትታይበትና አሜሪካም አውሮጳም ተጋባዥ ሆነህ ትሄድበታለህ በዚያም ፈረንካ ትቋጥርበታለህ ብዬ ምክሬን ለገስኩት። ከዚያ በኋላ ነው ታሪኩ አበራ እስከዛሬ ከብዙ ሰው አእምሮ የማይጠፉትን “ ጽዮን ማናትና” ኢየሱስ ማነው? የሚል ስብከቶቹን ሠርቶ ለህዝብ የለቀቀው።
•••
ከእነዚህ ሥራዎቹ በኋላ ታሪኩ እውቅና አገኘ። በየዐውደ ምህረቱ ተጋባዥ መምህርም ሆነ። አበሉም የሲዲ ሽያጩም ከፍ አለ። ጫማም ቀየረ። ሱሪም ቀየረ። ሆቴል መመገብም ጀመረ። ታሪኩ ችግሩ ካልሲው ላይ ብቻ ነበር። ወዛ ሲል ደግሞ ከምህረተአብ ጋር ገጠመ።እናም በተለይ ለእስልምና ጥያቄ መልስ ይሰጥ በነበረበት አንድ ወቅት ሁለቱ ዝነኛ ሆኑ። እውነት ለመናገር ታሪኩ ድህነቱ ጠልፎ ባይጥለው ኖሮ ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ይጠቅም የነበረ ልጅ እንደሆነ እኔ ዘመዴ እመሰክርለታለሁ። መሰሪ አይደለም። ትሁት ነው። እነ በጋሻው ታሪኩን ያገኙት በቃኝ የማያውቅ በፍቅረ ንዋይ ያበደ ይሁዳ መሆኑን ስላዩና ስላወቁ ነው። የመጀመሪያ የኮልፌ የልብስ ስፌቱን ንግድ በቤተ ክርስቲያን ዐውደምህረት ላይ ቆሞ ወደ ልብስ ስፌት ፋብሪካነት ቀይሮ ኢንቨስተር መሆን ይመኝ የነበረ ህልመኛ መሆኑን ስለተረዱ ነው በምኞቱ የጠለፉት። ታሬ ፍቅረ ንዋይ ጠልፎ የጣለው ምስኪን ልጅ ነው። ድህነት እኮ በጣም ክፉ ባላጋራ እኮ ነው።
•••
እናም ዛሬ ታሪኩ ለበጋሻው ምስክር ሆኖ እኔን ለማሳሰር ተሰይሞ ከች ብሏል። ታሪኩ ተጠርቶ ገባ። ቀና ብሎ አላየኝም። እንዳጎነበሰ፣ እንዳቀረቀረ ገብቶ ተቀመጠ። ሁሉም ሰው ደነገጠ። መጽሐፍ ቅዱሱን አነሣ፣ ጨበጠ፣ አስማሉት ግጥም አድርጎ ማለ። ጓጓሁ ምን ብሎ ነው የሚመሰክርብኝ? ምስክርነቱን ለመስማት ተጣድፌያለሁ። ከዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ጀርባ አንዲት ግን ሴት እንዳለች አውቃለሁ። ይህቺ ሴት የአዝማሪው መሐሙድ አሕመድ የቀድሞ ሚስት የዓድዋ ትግሬዋ ወሮ እጅግአየሁ ከበደ ናት። ጂጂ መጀመሪያ እኔን አጠመደችኝ። አንተ ሰውን የማስተባበር ፀጋ አለህ። እኔ ደግሞ አባ ጳውሎስንም። መለስ ዜናዊንም የማዘዝ አቅሙ አለኝ። እናም በጋራ ሆነን ቢዝነስ እንሥራ፣ አንተም ካሴት ስትቸረችር መዋል የለብህም አለችኝ። ጥፊ ከዚህ አልኳት። ጠፋች።
•••
ከእኔ በመቀጠል ምህረተ አብ ጋር ሄደች ሁለት ሳምንት አይቷት በሦስተኛው እኔው ራሴ አቆራረጥኳቸው። “አለን” የሚለውን መዝሙሩን ላሳትምለት ከእኔ ቤት የመዝሙሩ ጥናት ላይ እንዳለን ለምህረተአብ ትደውልለታለች። ዘመዴ ጋር መዝሙር እያጠናሁ ነው ይላታል። “ እሱን ሰው ተወው፣ አይበላ ወይ አያስበላ” ትለዋለች። ይደነግጥና የስልክ ወሬውን እንደጨረሰ ይጠይቀኛል? ለምን እንዲህ አለችኝ ይለኛል። ተቀራርባችኋል አልኩት። አዎ አለኝ። በል ጥፋ እንዳታጠፋህ ብዬ የሆነውን ሁሉ ነገርኩት። እግዚአብሔር ይስጠው ምህረተአብ ከእጅጋየሁ ኤልዛቤል ፊት እልም ብሎ ጠፋ። ተፋታት። ገላገላት።
•••
የዓድዋ ትግሬዋ እጅግአየሁ አሁንም አላረፈችም። ማኅበረ ቅዱሳንን ሞከረች አልተመቿትም። በመጨረሻ ፓትርያርኩን አዋርዷል፣ ህወሓትን ሰድቧል ብላ ታሳድደው የነበረው በጋሻው ላይ አይኗ አረፈ። የበጋሻው ቲም ደግሞ በወቅቱ የሪያል ማድሪድ ስብስብ ነው ተብሎ ይታማ ነበር። ባንዱ አሪፍ አሪፍ አዝማሪና ሙዚቀኞችም ነበሩት። ሊቀ ዘማውያን ትዝታው፣ ኮማሪት ዘርፌ፣ ሉጢው እዝራ፣ ሚጢጢው ፓስተር ሀዋዝ፣ እነያሬድ አደመ፣ አሸናፊ ገብረማርያም፣ አሰግድ ሳህሉ፣ ዳግማዊ ደርቤ፣ እስጢፋኖስ ሳህሌ ቄሴ( እስጢፋኖስ በእነ ጳውሎስ መረዋ ትግል በጊዜ ነው የተለያቸው) ምርትነሽ። ( ምርትነሽም ከወደቁ በኋላ ተለይታቸዋለች) ብቻ አሪፍ የቴዲ አፍሮን አቡጊዳ ባንድን የሚያስንቅ ስብስብ ነበረው። እናም ያንን ቲም ተቀላቀለች።
•••
እጅግአየሁ ብልጥ ናት። ትግሬነቷን፣ ዓድዋነቷን በሚገባ ለቢዝነስ የተጠቀመችበት ሴትም ናት። መጀመሪያ እነ በጋሻውን ከፓትርያርኩ አስታረቀች። ለፓትርያርኩም ቦሌ። መድኃኔዓለም በራፍ ላይ አቡነ መርቆሬዎስን የሚመስል ሃውልት ከእነ በግዋሻው ጋር ሆና አቆመች። ከዚያ በኋላ ቀራንዮ የሚል የኢየሩሳሌም የጉዞ ማኅበር መሠረተች። ህዝቡንም አጥባ አሰጣችው። እነበጋሻውም ዝናቸውን ተጠቅመው ከብረው አከበሯት። ገንዘብ መጣያ እስኪጠፋ ድረስ ህዝቡን ዘረፉት።
•••
በፊደል ሬስቶራንት ባለቤት በቡና ክለብ የደጋፊዎች ማኅበር ኮሚቴ በኤርትራዊው አቶ ኤፍሬም በኩል ሊዋጉኝ ብዙ ሞከሩ። አልቻሉኝም። በመጨረሻም ጂጂዬ አሏት እነበግዋሻው። ጂጂዬ ለሥራችን እንቅፋት የሆነ ሰው አለ። እንዴት ይወገድ? ይሏታል። ማነው እሱ? ዘመድኩን በቀለ ዘመዴ ይሏታል። የሚገርመኝ ሲሰድቡኝም፣ ሲከሱኝም ዘመዴ ነው የሚሉኝ። አቆላምጠው እኮ ነው የሚያስገቡልኝ። አርማጌዶን ብሎ በህዝብ እንድንጠላ አድርጎናል። እናም በመንግሥት በኩል የሆነ መላፈልጊ ይሏታል። ዓድዋዊት ወዲያው መላዋን ይዛ መላ ፍለጋ ጀመረች። ከዓድዋው ሊቀጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ዘንድ ደብዳቤ አዘጋጀች። ዘመድኩን እነዚህን የተቀቡ ሰባክያን መናገር መብት የለውም የሚል ደብዳቤ ለፍርድ ቤት አዘጋጀች። አሁን በቅርቡ ከዐቃቤ ሕግ ኃላፊነቱ የተነሣው አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ነው አቶ ፀጋዬ ብርሃኑን የተባለውን በወቅቱም የህወሓት ሚንስተር ዴኤታ በባሌም በቦሌም ብላ አዘዘችው። ትግሬ ዐቃቤ ሕግ፣ ትግሬ ዳኛ ተመደበብኝ። እናም የትግሬዎች ስብስብ ለእነበጋሻው አድልቶ ለፍርድ አበቃኝ። አይ አቡነ አረጋዊ አባቴ።
•••
የሚገርመው ነገር ደግሞ ሌቦቹ ትግሬዎች በዚህ መልኩ ቢከቡኝም ሃይላይ ታደሰ የሚባል የሥራ ባልደረባዬ ደግሞ እውነቱን ስለሚያውቅ ከእኔ ጋር ይንከራተት ነበር። መምህር ልሳነወርቅ የተባለ የህወሓት ወዳጅም እንዲሁ ከጎኔ ነበር። በተለይ ሃይላይ ታደሰ አቤት በሌባ ሲበሳጭ አይጣል ነው። ሚንስትሩ ቢሮ እኔ ጠበቃዬ አቶ ጌትነትና ሃይላይ ነበር የገባነው። እናም ከብዙ ውይይት በኋላ ከላይ የመጣ ትእዛዝ ነው። ምንአባቴ ላድርግ እስኪለን ድረስ አወራን። ክሱም ፍርዱም ቀጠለ።
•••
ታሪኩ ለዚህ ቡድን ነው እንግዲህ ሊመሰክርብኝ የመጣው። ዐቃቤ ሕግ ታሪኩ ሊመሰክር የመጣበትን ጭብጥ አስረዳ። ታሪኩም ምስክርነቱን ጀመረ። አቤት ቀደዳ፣ አቤት ውሸት፣ ባይበላስ ቢቀር? ይበጠረቅ ጀመር። ዝርዝሩን ቆይቼ  እመለስበታለሁ። ዳኛው እራሱ አፍሮ መምህር ዘመድኩን ይሄን ምስክር መክሰስ ትፈልጋለህ እስኪለኝ ድረስ በችሎቱ ውስጥ ተዋረደ። ጠበቃዬ ጌትነት፣ እኔም እየተፈራረቅን ታሪኩ አበራን በመስቀለኛ ጥያቄ አጥበን፣ ጨምቀን፣ አሰጣነው።
… ይቀጥላል። ነገ የእህተ ማርያም አጀንዳ ስላለብኝ የታሪኩ አበራን ጉዳይ ዛሬውኑ እንቋጨዋለን። ጠብቁኝ። ደግሞስ የትአባታችሁ መሄጃ አላችሁ። ጠብቁኝ ብያለሁ ጠብቁኝ።
♦♦♦♦

“ግሪታዴ” ታሪኩ አበራ ማነው?  

 [ክፍል ፪] 

• ያለ ክፍያ ዘና ብላችሁ አንብቡት። ጮክ ብላችሁ አትሳቁ። ባልበላ አንጀታችሁ ላንቃችሁ እንዳይሰነጠቅ አደራ። 
 ይሄን ጦማር ግሪታዴ ታሪኩ አበራ ራሱ ሲያነበው በሳቅ ፍርፍር እየበላ ነው ብዬ አስባለሁ። ከሞቱት በቀር በህይወት ያሉት ምስክሮቼ ናቸው። ሁሉንም ከአእምሮዬ መዝገብ ቤት አውጥቼ ነው የምጽፍላችሁ። መልካም ንባብ።
•••
ሄይ ኳረንቲኖች አንዴ ሰብሰብ በሉ። ሳሎን ያላችሁ፣ ጓዳ መኝታቤት፣ በረንዳው ላይ ያላችሁ ሰብሰብ በሉ። ዕድሜ ለኮሮና  የትአባታችሁ መሄጃ አላችሁ። አዳሜ ከሰሰሎን ጓዳ፣ ከጓዳ ኩሽና፣ ከኩሽና መኝታቤት ትንገላወጂያለሽ። ቅድም ፍርድቤት ነበር ያቆምኳችሁ አይደል? እንቀጥል። ማነህ እዚያ ጋር እስቲ ዝም በል። አትረብሽ። ዳይ ቀጥሉ ወደ ንባብ።
•••
መጀመሪያ ዐቃቤ ሕጉ እንደ መግቢያ ነገር የሚዋሸውን እየጠቆመ ታሪኩን ጠየቀው። ታሪኩም የሌለ ተቀደደ። ተበረጠቀ አይገልጸውም። እንዲህም አለ። የሆነ ቅዳሜ ቀን ዘመድኩን የሆኑ ወጣቶችን ሰብስቦ ቅድስተ ማርያም በመላክ ትዝታው ሳሙኤልን አስደብድቦታል። ሌሎችንም ብር እየከፈለ ሲያስደበድብ አይቻለሁ ይላል። ደነገጥኩ። እኔማ የሆነ ዝግጅት ለማቅረብ ቲያትር እያጠናንም መሰለኝ። ግን ሃቁ ፍርድቤት ዳኛ ፊት ነው ያለነው። እንዲህ የሚያወራውም ግሪታዴ ታሪኩ አበራ ነበር። የሆነ ግዜ ደግሞ ስልኬ ላይ ደውሎ እነ በግዋሻውን፣ እነ ትዝታውን እስከደም ጠብታ ድረስ አልፋታቸውም እፋለማቸዋለሁ ብሎኛል ይላል። ዳኛው መሃል ይገባና መምህር ዘመድኩን ነው እንዲህ የሚለው? ይለዋል። አዎ ይላል ግሪታዴ ታሪኩ። ምን ማስረጃ አለህ ይለዋል። እየመራው መሆኑ ነው እንግዲህ። ቀርጬዋለሁ። በስልኬ ድምጹን ቀርጬዋለሁ ይለዋል።
•••
አሁን የእኔ ጠበቃ አቶ ጌትነትና የእኔ ተራ ደረሰ። መስቀለኛ ጥያቄ ጠይቁት ተባልን። አጣደፍነዋ። እስኪያልበው አጣደፍነው። ጌትነት ጠበቃዬ ታሪኩን ጠየቀው። ዘመድኩን ትዝታውን ሊያስደበድበው ወጣት አደራጅቷል፣ ሲያስደበድበውም አይቻለሁ፣ ብርም ይከፍል ነበረ ብለሃል።
ግሪታዴ ታሪኩ፥ አዎ በማለት መለሰ።
ክሱ የበጋሻው ነው። ትዝታውን ለምን ያስደበድበዋል? ከትዝታው ጋር ፀብ አላቸው?
ታሪኩ ዝም
ጌትነት ቀጠለና ጠየቀው። ብር ሲሰጥ አይተሃል አይደል።
አዎ አለ ታሪኩ የተዘጋጀለትን ወጥመድ ሳያውቅ።
አንተ የት ሆነህ ነበር ያየኸው?
ሮሚና ካፌ ጋር ሆኜ አለ ታሪኩ።
ስንት ብር ሲሰጥ አየህ?
መቶ መቶ ብሮች።
መልካም በግምት ምን ያህል ትራራቁ ነበር?
ኧረ ራቅ ይላል ትንሽ?
መልካም ራቅ ካለ ታዲያ መቶ ብር ይሁን 1 ብር በምን አወቅክ? ደግሞስ ብሩን ሲሰጥ ሂዱና ትዝታውን ደብድቡት ሲል እንዴት ሰማኸው?
ግሪታዴ አላበው። ዝምጭጭ አለ።
ዐቃቤ ሕጉ ጣልቃ ገባ። አካሄድ ነው ሥነ ሥርዓት ነገር አለ። ዳኛውም ጥቅሴ ነበርና ሌላ ጥያቄ ጠይቁ አለ። ጠበቃዬ ሕጉን ጠቅሶ ለማስረዳት ሲሞክር ትግሬው ዳኛ ጠበቃዬ ላይ በዓባይ ፀሐዬ፣ በመለስ ዜናዊ፣ በስብሐት ነጋ ስታይል ቧይ ብሎ አንቧረቀበት። ጠበቃዬ ታግሶ ሊቀጥል ሲሞክር ሲስተማቸው ገባኝና። ጌች እኔ እጠይቀዋለሁ አንተ ቆይ እረፍ አልኩት። እሺ አለኝ። ጠበቃው ጓደኛዬ ነው። አብረን ብዙ ሥራየሠራን ምርጥ ልጅ ንው። ጌችዬ ባለህበት ሰላም ሁንልኝ።
እኔ ዘመዴ መስቀለኛ ጥያቄዬን ጀመርኩ እሺ ታሬ እኔና አንተ የግል ፀብ አለን?
የለንም
ምን ቀን ነው?  ብር እየከፈልኩ ትዝታውን ያስደበደብኩት?
ቅዳሜ በዚህ ቀን።
በስንት ሰዓት
ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ
እኔ ዳኛውን ልብ በሉ ቀኑንና ሰዓቱን ያዙልኝ። ጻፉልኝ።
ዳኛው እየተቀረጸ ነው ቀጥል።
እኔ ታዲያ የዚያን ዕለት እኮ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመራቂዎች ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤ ነበር። እኔ ደግሞ የማኅበሩ የሥራ አመራር ውስጥ ኃላፊ እንደሆንኩ ታውቃለህ። በዚያን ቀን ደግሞ ማኅበሩ ለ2 ቀን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስብሰባ ነበረው። እዚያ ስብሰባ ላይ እኔም አንተም አብረን ነው የዋልነው። በመሃል ወጣ እንዳትለኝ እንኳ የተመደብኩት ካሜራ የመቅረጽ ሥራ ላይ ነበር። አንተንም ቀርጬሃለሁ። ስብሰባው ሲያልቅ ማታላይ አብረን ነው የወጣነው። እናስ በየት በኩል ወጥቼ ነው ትዝታውን የማስደበድበው? መረጃው በእጄ ነው። የማኅበሩም ፕሬዘዳንትም ሆነ ጸሐፊ ይመሰክራሉ። ደግሞም ሁለቱንም ቀን ምሳም እዚያው ስለነበረ እየፈረምን ነው አብረን የዋልነው። ሊቃነጳጳሳቱም ተማሪዎቹም አሉ። ምን አስበህ ነው ግን መዋሸት የፈለከው ታሬ? በማለት ጠየቅኩት። ታሪኩ ዝም፣ ጭጭ አለ። ከምር አሳዘነኝ። ውኃ ውስጥ የገባች አይጥ መሰለ። አሳዘነኝ። አንጀቴን በላው።
•••
ዳኛው መልስለት እንጂ አለው። ታሪኩ ዝም አለ። ዳኛውም በሰጨው። ዐቃቤ ሕጉም ተናደደ። ታሪኩም ያጠናውን ድራማ ሳይተውነው ማንቁርቱን ይዘን እኔና ጠበቃዬ ችሎቱ ውስጥ አስተፋነው። ኤት‘አባቱ አለ አጎቴ ሌኒን። ታሪኩ በብርድ አላበው። የችሎቱ ታዳሚም ሳቀበት። ዳኛው ወደ እኔ ዞሮ ጠየቀኝ።
አሁን ላልከው ነገር ማስረጃ ታቀርባለህ?
እኔ ዘመዴ። አዎ። የሰነድም፣ የሰውም ማስረጃ አለኝ። የማኅበሩ ሰብሳቢ መምህር ማንያዘዋል የእኔም የእሱም ጓደኛ ነው። ሌሎችም ቀርበው ማስረዳት ይችላሉ።
መልካም። ይሄ ደወለልኝ ስላለው ነገርስ? የምትለው አለህ አለኝ ትግሬው ዳኛ ።
የለኝም ነገር ግን ስልኩን እኔ አልደወልኩለትም እንጂ እርግጥ ነው እሱራሱ ታሪኩ ደውሎ ሲያናግረኝ ያለውን ቃል በቃል ነግሬዋለሁ። ቀርጬዋለሁ የሚለው ግን ብከሰው ያለፈቃዴ በመቅረጹ ብቻ አሳስረዋለሁ። እነ ትዝታውንም እነ በጋሻውንም አልፋታቸውምም ብዬዋለሁ። አሁንም በፍርድ ቤቱ ፊት እደግመዋለሁ አልፋታቸውም ብዬ ክችች። አለቀ።
ዳኛው መለሶ ጠየቀኝ። ምስክሩን መክሰስ ትፈክጋለህ?
ማን ታሪኩን? እኔ በፍጹም መክሰስ አልፈልግም። አልከሰውም። መድኃኔዓለም ይክሰሰው። የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይፍረድበት። እኔ አልከሰውም።
ታሪኩ ጎብጦ ወጣ።
•••
ዐቃቤ ሕጉ ሁለተኛ ምስክር ጠራ። ዘማሪ ዲያቆን ሙሴ ብሎተጣራ። ሙሴ ገባ። ሙሴ ማለት ከጎጃም የመጣ ዲያቆን ነው። ምስኪን ነበር። የቅርብ ዘመዶቹ እንኳን ሀመሰይሰሙለትን፣ እራሱ ብቻ የሚሰማው አንድ መዝሙር አውጥቶ በግድ በየቤተ ክርስቲያኑ እየዞረ እየሸጠ ይኖር ነበር። በኋላ ላይ አንድ ቀን ሳየው አምሮበት፣ ሸበላ ሆኖ፣ ፀዳ ብሎ አየዋለሁ። እንዴ ምን ተገኘ ስለው አንድ አጎቴ ከውጭ ሀገር መጥቶ የቲሸርት ፋብሪካ ከፍቷል። እዚያ እየሠራሁ ተለውጫለሁ ይለኛል። ከምር ደስ አለኝ። እናም ለረጅም ጊዜ ሳላየው ቆይቼ አሁን ለምስክርነት ሲመጣ ደነገጥኩ። ደግሞም ገረመኝ። በየት በኩል ተገናኙት ብዬም ደነቀኝ። እየተቆናጠረ ገባ። እየተንጎማለለ።
•••
ይሄን ምስኪን አሰልጥኖ የላከው ደግሞ የፊደል ሬስቶራንቱ ባለቤት ኤርትራዊው አቶ ኤፍሬም ነበር። ኤፍሬም ማለት የነንዋይ ደበበ ፕሮሞተር የነበ። ዘርፌን ከናይት ክለቡ ወደ አዝማሪነት የቀየረ። በሚሊንየሙ ጉባኤ የተገኘውን ገንዘብ እምሽቅ አድርጎ የበላ የቤተ ክርስቲያን እምባ ያለበት ነው። ቦሌ አካባቢ ነበር ፌደል ሬስቶራንት የሚል ከፍቶ ይሠራ የነበረው። እሱ ነው ሙሴን አሰልጥኖ የላከብኝ።
•••
ፋራው ሰገጤዋን ሙሴንም በተራዋ ወጥ በወጥ አድርገን መለስናት። ያ እየፎለለ የገባው ልጅ ዳኛ ፊት ምኑን ከምኑ ያድርገው። እያየሁት ሟሟ። ሟሸሸ። ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት ከልቤ አዘንኩበት። አንድ ቀን ክፉ ደግ ተነጋግረን የማናውቅ ልጅ ከመሬት ተነስቶ ለመናፍቅ ጥብቅና ቆሞ ሊመሰክርብኝ ሲመጣ አዘንኩበት። እዚያው ቆሜ ስንቶች በእንዲህ ያለ የሐሰት ምስክሮች ህይወታቸው እንደተመሰቃቀለ ሳስብማ የባሰ አዘንኩበት። ዳኛውም የምትለው አለህ አለኝ? እኔም ቅድም ጨብጦ የማለበት የእግዚአብሔር ቃል ይፍረድበት። ምንም አልልም አልኩኝ።
•••
ሙሴ ዐይኔን ሳያይ አቀርቅሮ ወጥቶ ሄደ። ይሄ ልጅ ብዙም ሳይቆይ ከደረሰች ነፍሰጡር ሚስቱ ጋር ከናዝሬት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳለ ሲኖትራክ በላዩ ላይ ወጥቶ ከነ እርጉዝ ሚስቱ ተጨፍልቀው ሞቱን መባልን ሰማሁ። ደነገጥኩም። ነፍስ ይማር።
•••
ዳኛው ቀጠለ። ሦስተኛ ምስክር ይግባ አለ። ዐቃቤ ሕጉ ይበቃኛል። ቀሪዎቹ ምስክሮችም ከዚህ የተለየ ስለማይመሰክሩ ይበቃኛል አለ። እናም እነ ቴቬዝ አመለጡኝ። ናትናኤል ቴቬዝ ማለት የአባኮራን የአራት መንታ ልጅ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ስታዲየም በማስጨፈር ይታወቃል። የበገጋሻው ብር ተደራዳሪም ነበር። ደፋር የጎጃም በረንዳ ልጅ ነው። ከታኪሲ ተራ በአንድ ጊዜ ሰባኪ የሆነ ልጅ ነው። ኧረ የሆነ ጴንጤ መጽሐፍ ስሙን ቀይሮ ሁሉ አሳትሞ ነበር። የዱባይ ሴቶችን ከነ ትዝታውና ታሪኩ አበራ ጋርም የፈጀ ነው ይሉታል። እኔ ግን አላየሁም።
•••
እኔም ለሚቀጥለው ቀጠሮ ምስክሮቼን ይዤ እንድቀርብ ተነግረኝ። ስለምኑ ነው የማስመሰክረው ብዬ ትግሬውን ዳኛ ጠየቅኩት። እሱም አንዲት ወረቀት አወጣና አሳየኝ። ኮፒውንም ለጠበቃዬ ሰጠው። እናም ይሄን ደብዳቤ ፓትርያርኩ ናቸው የጻፉት። ደብዳቤው የሚለው ፀጋው የበዛላቸውን አገልጋዮች ዘመድኩን መቃወም አይችልም ነው የሚለው። እናም አለ ዳኛው። አንተ ኦርቶዶክስን ወክለህ መናፍቅ ለምትለው አካል መልስ መስጠት ትችላለህ የሚል ወይ የሰው ወይ ደግሞ የሰነድ ማስረጃ አቅርብ አለኝ ዳኛው
የሰው ምስክርነት
1፥ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሀዲስ ኪዳን መምህሩን መምህሬን መምህር ደጉዓለም ካሳን።
2፥ መምህሬንና ወንድሜን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን
3፥ ክቡር ሥራ አስኪያኪያጁን አባ ኃይለጊዮርጊስን
4፥ የምሩቃን ማኅበሩን መምህር ማንያዘዋልን ቆጥሬ ወጣሁ።
•••
ለደብዳቤዋ ግን መላ ፈለኩ። በወዳጆቼ ሊቃነ ጳጳሳት በኩል ቅዱስ ፓትርያርኩን አናግሬ ለምን እንደዚያ እንደጻፉብኝ ማወቅ ፈለግኩ። እሳቸው ጋር መግቢያ መንገዱ ግን ዝግ ሆነ። ወዳጆቼ ሊቃነ ጳጳሳቱም ፈሩ። አታነካካንም አሉኝ።  እናም ሳስበው አንድ ዘዴ መጣልኝ። አንዲት በቅርብ የማውቃት እንደ ቤተሰብም የምትሆነኝ እህት አለችኝ። እናም ሁሌ ስንገናኝ አባ ጳውሎስ ደውለውልኝ ልጆቼን ባረኩልኝ፣ ዛሬ ምሳ እሳቸው ጋር ነበርን ስትለኝ እንደኖረች ትዝ አለኝና ደወልኩላት። የወዳጄ ሴት ልጅ ሴቷ ልጄን ክርስትና ታነሣለች። እናም ደወልኩላት። ጉዳዩን አጫውቼ ከአባ ጳውሎስ ጋር እንድታገናኘኝ እንደምፈልግም ነገርኳት። በደስታ ብላ ለጸሐፊያቸው ለእማሆይ ሮማን ደውላ ቀጠሮ አስይዛልኝ ገባን።
•••
ጉዳዬን ማቅረብ ጀመርኩ። መከሰሴን። የተከሰስኩት ደግሞ በዚህ እርስዎ በጻፉብኝ ደብዳቤ መሆኑን ነገርኳቸው። ያሬድ የሚባል ወንድምም አላቸው እሱም ለእኔ ተደርቦ በእልህ አስረዳ። እንዴት ለመናፍቃን አለቃ ለበጋሻው በእርስዎ ቲተር እዚህ ቤተ ክርስቲያን ልጅ ላይ ይጻፍበታል ብሎ ተሟገተልኝ። እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው ሆነው አይናቸውን ጨፍነው ሲሰሙ የቆዩት ቅዱስነታቸው አባ ጳውሎስም አይናቸውን ገለጥ አደረጉና ሁለት ትእዛዝ ሰጡ። ብፁዕ አቡነ ገሪማን ጥሩልኝ። መዝገቤቱን አባ ማንትስንም በዚህ ቁጥር የተጻፈ ደብዳቤ ኮፒ ይዘህ ና በሉት ብለው አዘዙ። እስከዚያው ኢንተርቪ እያደረጉኝ ቆዩ። ያው የተለመደ ነው። የት ተወለድክ? የወላጆችህ ትውልድ የት ነው ምናምን የሚል ነው። ጎጃሜና የዓድዋ ትግሬ እንደሚያርቁብ እሰማ ነበርና እኔ ሐረርጌነቴን ነገሬ ሌላ ኢንተርቪ ሳይቀጥል ብፁዕ አቡነ ገሪማ መጡ። የመዝገብ ቤቱም መነኩሴ ፋይሉን ይዘው መጡ።
•••
ፓትርያርኩ ጠየቁ?  ይሄ ደብዳቤ ከምር ስለ እውነት በእኔ ቲተር የተጻፈ ነው? አሉ በመገረም። አቡነ ገሪማ አነበቡትና በፍጹም በእኔ በኩል አላለፈም አሉ። መነኩሴውም መለሱ እኔም የመጣልኝን ደብዳቤ ማስቀመጥ ነው እንጂ ስለመጻፉ በምን አውቃለሁ አሉ? ደብዳቤዋ በሆነ መንገድ ተሠርታ ሕጋዊ መስላ የወጣች ናት። እናም ፓትሪያሪኩ ማነህ የእኔ ልጅ አሁን እኔ ምን ልርዳህ? ለፍርድቤት ወይም ለፖሊስ ልጻፍልህ? አሉኝ። ወዳጄና ወሮ አይኒና ወንድማቸው አቶ ያሬድ አዎ አሉ። እኔ ግን አልፈልግም። አልኳቸው። ለምን ይጠቅምሃል አሉኝ። እኔም አልኳቸው። አዎ ይጠቅመኛል። ነገር ግን እኔ ማወቅ የፈለኩት አንድ ፓትርያርክ ለተራ ወመኔ ቦዘኔ ለሆን ወጠጤ ልጆች ጊዜ ሰጥቶ ለጸባችን አጋዥ ደብዳቤ መጻፉን ገርሞኝ እሱን ነገር መበር ማወቅ ፈልጌ የመጣሁት። እናም አሁን አውቄያለሁ። ሁለተኛ ደግሞ እኔ እነዚህን ወጠጤዎች አሸንፋቸዋለሁ። ሳሸንፋቸው ግን በፓትሪያርኩ አጋዥነት ነው እንዲባል አልፈልግም። ሁልጊዜ ስለጉዳዩ ባስታወስኩ ቁጥር ልወቅሶትም ስላልፈለኩ ነው እርስዎን ማናገር የፈለግኩት ብዬ እቅጩን ነግሬያቸው ተባርኬ ወጣሁ። አቤት ወይዘሮ አይናለም የዚያን ዕለት የወረደችብኝ ወርጂብኝ አይጣል። ታዲያ ለምን አለፋኸኝ። አንተ ዘመዴ ደግሞ አጉል ታበዛዋለህ።
ብትታሠር ምን ትጠቀማለህ? ልጆችህ ና ሚስትህ አያሳዝኑህም ወዘተረፈ አለችኝ። እኔ ዝም ጭጭ ብዬ ተግሳጿን ጠጥቼ አመስግኜያት ተለያየን። ዋናው በአዳም በኩል የተዘጋውን ዳጃፍ በሴት በኩል ማስከፈቴ ነው።
•••
ይሄ ነገር አሁንም አላለቀም። ነገር ነገርን እየመዘዘ ከዚህ ደርሷል። እናም የግድ መቋጨት አለበት። በቀጣዩ ጦማር መፍትሄ እንሰጠዋለን። ፍርድ ቤቱ እንዴት ተቋጨ፣ ታሪኩ ከዚያ በኋላ እንዴት ግሪታዴ ጴንጤ ሆነ፣ እንዴት እንግሊዝ መጣ፣ ማን ወሰደው? በእንግሊዝስ ምን እየሠራ ነው። በአጭር በአጭሩ ተመልክተን እንዘጋዋለን።
•••
ጠብቁኝ የትም እንዳትሄዱ። ምድረ የወሬ ሱሰኛ ሁላ። ዘንድሮማ የወሬ ጠኔ በአፍጢማችሁ እንዳይደፋችሁ ነው የማደርጋችሁ። ዘመነ ኮሮናንማ እንዲህ ፏ ሽር ብትን አድርጌ ነው ፈታ አድርጌ የማሳልፋችሁ። ሳቅ ከአፋችሁ አይጥፋ። ማንበብ ልመዱ።
ርቀት ይጠበቅ
እጃችሁን ታጠቡ
አፍህን ሸፍን።
•••

“ግሪታዴ” ታሪኩ አበራ ማነው?

 [ክፍል ፫ ] 

★ ቀደም ብለን ብቻችንን የጀመርነው የተለመደው የጸሎት መርሀ ግብራችን ከ96,664 ቤተሰብ በላይ ባፈራው Http.t.me/ZemedkunBekeleZ የቴሌግራም ቻናላችን ላይ ዛሬም እንደ ትናንቱ ይቀጥላል። ቅድሚያ ይሄ ይነበብ።
 ሳያነብ ኮመንት የሚሰጠውን ስለምቀስፈው ብዙም አትጨነቁ። በነገራችን ላይ በፌስቡክ ስሙ #Samuel_Tibebu የሚለው የግሪታዴ ታሪኩ አበራ ሌላኛው አካውንቱ ነው። እንድታውቁት ብዬ ነው። ለእኔ የመልስ ምት ብሎ መድከም የሚጀምረው በዚያኛው አካውንቱ ነው። እኔን፣ ምህረተአብን፣ ማኅበረ ቅዱሳንና ዳንኤል ክብረትን መስደብ ሲፈልግ በዚያ ነው የሚጠቀመው። ዛሬ መጻፍ ይጀምራልና በዘከያ ተከታተሉት።
•••
እናንት ገዳፈኞች ሳልወድ ጎትጉታችሁ፣ ጎትጉታችሁ የማልፈልገውን ታሪክ አስጀምራችሁ መቋጫ አጥቼ ተቸገርኩ አይደል? ነገርን ነገር እያነሳው እኮ እንደ ክር ተመዝዞ ተመዝዞ አላልቅ አለኝ። የፈጀውን ይፍጅ እንጂ ትረካዬንማ አላቆማትም።
★ እናንተም የትም አባታችሁ መሄጃ የላችሁም እየተገላበጣችሁ ተጋቷት። ነገ የታሪኩ ይቋጭና የእህተ ማርያም ይቀጥላል።
•••
የእኔ ምስክሮች ከመሰማታቸው በፊት ኤልያስ የሚባል ጋዜጠኛ በሆነ አሁን በማላስታውሰው ሰው በኩል አገኘኝ። አገኘኝና አወራኝ። ምን ልርዳህም አለኝ። ምንም አልኩት። ተው ሰዎቹ ያሳስሩሃል አለኝ። እንደፈለጉ አልኩት። ኬሬዳሽ። የሆነ ቀን ኤልያስና ከጋዜጠኛ ብርቱካን ሀረገወይን ጋር  አገናኘኝ። ብርቱካን ካዛንችስ የሚገኘው ቤቷ ቀጠረችኝ፣ ሄድኩ ረጅም ሰዓት አወራችኝ። ቆይታም በሌላ ቀን ደውላ ዛሬ እፈልግህሃለሁ በዚህ ሰዓት ና ብላ ቀጠረችኝ። የጋዜጠኛ ብርቱካን ባለቤት በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደርና የፕሬዘዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስም ፕሮቶኮል ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል። ከእሳቸው ጋር ልታገናኘኝ ይሆን እንዴ እያልኩ በውስጤ ሳብሰለስል “ዛሬ አንድ ትልቅ የኢህአዴግ ሰው ሊያወራህ ይፈልጋል እናም ስልክህን አጠፋፋና እንሄዳለን ትለኛለች። ማነው? የት ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የለም። ውኃ የመሰለ ቪ8 መኪና መጣ፣ ሹፌሩ እኔና ብርቱካን ገብተን ጉዞ ጀመርን።
•••
ከርቸሌ ሚካኤል አካባቢ እንደደረስን መኪናው ብርሃን ዘኢትዮጵያ ጣይቱ የባህል ማዕከል” የሚባል ግቢ ጋር ደርሶ ቆመ። በሩ ተከፈተና ገባን። ትልቅ ግቢ፣ የጎጆ ቤቶች ያሉት ሰፊ ቤት ነው። የነገሥታቱ ፎቶ እስከ መለስ ዜናዊ ድረስ የተሣሉበት ግቢም ነው። አንዲት ጎልማሳ ሴት ተቀበለችን። እሱ ነው አለቻት ብርቱካንን። አዎ አለች ቡርቱካን። ተከተሉኝ ተባልና ተከትለናት ወደ አንደኛው ጎጆ ቤት ገባን። ቤቷ ውስጥ አንድ በቴሌቭዥን ብቻ የማውቀው የሃገሪቷ አድራጊ ፈጣሪ ሰው በአካል ተቀምጦ አየሁት። ሰላም ብለነው ጠቀመጥን። እሱ ነው? አላት በጥያቄ መልክ ብርቱካንን? አዎ አለችው። እንቀጥላ ውይይታችንን አሉ ሰውዬው። ይቻላል አልኩኝ እኔ የውይይቱን ርዕስ ባላውቀውም በውይይቱ መሳተፍ አያቅተኝም ብዬ ማለት ነው። ያው እኔን ታውቀኛለህ ብዬ እገምታለሁ አሉ ባለሥልጣኑ። በሚገባ እንጂ። በሚገባ አውቆታለሁ። እርስዎን የማያውቅ ሰው አለ እንዴ አልኳቸው። ደህና እንቀጥል አሉ አቦይ ስብሀት ነጋ።
••••
መጀመሪያ ስሜ ተተነተነ፣ የአባቴም የአያቴም ተቆጠረ። ከዚያ የእናቴ አባት እስከ አያት። እናቷም አልቀሩ። ሐረር ለምን እንደተወለድኩም ተጠየቅኩ። አዲስአበባ መቼና ለምን እንደመጣሁ፣ እስከስንተኛ ክፍል እንደተማርኩ፣ በቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ድርሻዬን፣ ሥራዬ፣ ኑሮዬ። የሚስቴ ዘር ሁሉ ተጠየቀ። ሁሉንም መለስኩ። የመጀመሪያው ቀን ምርመራ በዚህ አበቃና ለሁለተኛ ቀን ቀጠሮ ይዘን ተለያየን። የአቦይ ሹፌር በቪ8 መኪናው ሌሊት 7ሰዓት እኔን ቤቴ አድርሶኝ እንዲመጣ ታዘዘ። እንደታዘውም አደረገ።
•••
በሁለተኛውም ቀን በሰዓቴ ካዛንችስ እሄዳለሁ። ሃናን ዳቦ ቤት ጋር እጠብቀዋለሁ። ያ ቪ8 መጥቶ መጀመሪያ እኔን ከዚያ ብርቱካንን ይዞን እብስ ብሎ ይሄዳል። ዛሬም አቦይ ብቻቸውን እዚያው ጎጆ ቤት ውስጥ ናቸው። ለአቦይ የሆኑ የአረቄ መዓት ተደባልቆ ይሰጣቸዋል። ለብርቱካን ውኃ። እኔ ብሞት ንክች አላደርግም ብዬ ብርድ ይጠጣኛል። አቦይ ስብሃት ዛሬ መረር ብለዋል። ጥያቄያቸው በሙሉ ማኅበረ ቅዱሳን ዙሪያ ነው። እኔ ዝም። ተናገር እንጂ ሃሳብ ስጥ። እኔም ስለማኅበረ ቅዱሳን የማውቀው ነገር የለም አልኩኝ ኮስተር ብዬ። አባል አይደለሁም። በመጽሔት በጋዜጣና በአገልግሎታቸው ካልሆነ ስለማኅበሩ አላውቅም አልኩ። እንዴ? ማኅበረ ቅዱሳን አይደለህማ አሉ አቦይ ስብሃት? አዎ አልኩ? ታዲያ ለምንድነው የምትሟገትላቸው? በየፌስቡኩ፣ በየመጽሔቱ ለምን ትሟገትላቸዋለህ አሉኝ? ምክንያቴን አስረዳሁ። ተቆጡ። ታዲያ ከነበጋሻው ጋር ለምን ትጣላለህ? ምንስ ያገባሃል? አበዱብኝ አቦይ። እኔም ግማሽ ትሁት፣ ደግሞም ደፋር ለመምሰል እየተወዛገብኩ በኋላ ደግሞ እንዳይታዘቡኝ፣ ፈሪ ነው እንዳይሉኝ ብዬ ሄጵ አልኩ። ብርቱካን ኧረ ቀስ በል እስክትለኝ ድረስ ዊኒጥ ዊኒጥ አልኩ። ቡካትያም ነገር ነው እንዳይሉኝ የውስጤን ጭንቀት ደብቄ ከሽማግሌው ጋር የሌለ ገተታ ጀመርኩ። መጠጡን በላይ በላዩ ይጨልጡታል። ስካራቸውን ከእኔ ጋር በመጯጯህ ያሳልፉታል። ለሦስተኛ ቀን ተቀጣጥረን በትላንቱ መንገድ ተለያየን።
•••
ከመለያየታችን በፊት ግን ራሴ ሞልቼ እንድመጣ ቃለመጠይቅ አዘጋጅተው ሰጡኝ። መጠይቁ በሙሉ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ነው። በራሳቸው እጅ ጽሑፍ የተዘጋጀም ነው። እኔ ታዲያ ምኔ ሞኝ ነው የማኅበረ ቅዱሳኑን መምህር ታደሰ ወርቁን ጠራሁና ጉዳዩን ነግሬ ቃለመጠይቁን እኔን ሆናችሁ ሞልታችሁ በቶሎ ለነገ ስጡኝ እና ለሽማግሌው ልውሰድለት ብዬ ሰጠሁት። እነ ታዴም ተሰብሰበው እኔን ሆነው ስለማኅበራቸው ሞልተው ጽፈው ሰጡኝ። በኮምፒዩተር አዘጋጅቼ ነበር የሰጠሁት። ስንገናኝ አቦይ ስብሃት ተደነቀ። ቀዝቀዝም አለ። ሼባውን ሠራሁለት። ከዓድዋ መጥቶ ሊያጃጅለኝ ያምረዋል እንዴ አልኩኝ በሆዴ። በአፌማ አብጃለሁ እንዴ ሆሆይ !
•••
እንዲህ እንዲህ እያልን 7 ይሁን 8 ቀን ብቻ እዚያው ቤት እየተገናኘን የጉድ መዓት እየሰማሁ አሳለፍን። ሹፌሩ የምትገርም ሰው ነህ አለኝ እየተላመድን ስንመጣ። እዚህ ቤት እኮ አቦይ ጳጳሳቱን ሁሉ አስመጥቶ አምጰርጵሮ ነው የመለሳቸው። አንተ ግን ተሳፈጥከው። የሐረር ልጆች ጠባይ ነው። የንቀት አይደለም ሲል ሰምቼዋለሁ። እናም ትንሽ ብትረጋጋ አለኝ። ሞኜ በውስጤ እንዴት እንደቀዘንኩ አላየህ ብዬ በአፌ ሹፌሩም ላይ በል እባክህ ጥፋ። ሁለት ነፍስ የለ እያልኩ መተርተሬን ቀጠልኩ። እሱም ላይ ሄጵ አልኩበት። ሹፌሩ እየሰለለኝም ከሆነ የራሱ ጉዳይ ብዬ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም በሚለው ቀጥዬበታለሁ። ለሹፌሩም ለተጋሩውም አንንድ አይነት አቋሜን አሳይቼያቸዋለሁ። አንዳንዴ ግን ብቻዬን ስሆን ምን ሆኜ ነው ብዬ ራሴን እወቅሳለሁ። የምን ቅብጠት ነው። ባትሪ እንዳፈላሁ ሁሉ ይሰማኛል። ዛሬ እንኳን ሄጵ አልልም እልና እዚያ ስደርስ አፌ ሌላ ልቤ ሌላ ሆነው ቁጭ። ልቤ ኧረተው ዘመዴ አትቅለብለብ ይለኛል፣ አትሳፈጣቸው ይለኛል። አፌደግሞ ልቤን አልሰማ ብሎ ጲሪሪሪሪም ጳራራራም ብሎ መልሶ ራሴኑ ያሸማቅቀኛል። አልተገናኝቶም።
•••
የመጨረሻው ቀን ማስጠንቀቂያ ነበር። ከእነበጋሻው ፊት ገለል በል። እምቢ ካልክ ለሚደርስብህ ነገር በሙሉ ኃላፊነቱ የራስህ ነው። እናም ውሳኔው ይሄ ነው። ምርጫው የአንተ ነው አሉኝ አቦይ። ዝም ብሎ መውጣቱ ፈሪ ሊያሰኘኝ ሆነ። ብርቱካንም ወሮ ሳቤላም ሊታዘቡኝ ሆነ። ከምር ሁለቱም ሴቶች በአቋሜ ደስተኞች ናቸው። ሆኖም ከራሴ ጋር ስሟገት ቆየሁና የሞት ሞቴን ተነፈስኩ። “ አላቆምም። የሚመጣውን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። የሚል ቃልን የሞት ሞቴን አምጬ የግዴን ተነፈስኩባቸው” አከተመም አልኳቸው። አንዴ ከበሰበስኩ አይቀር ብዬም መተርተሬን ቀጠልኩ “ ህወሓት ከትግራይ መጥታ፣ ከአክሱም ጽዮን ከቅዱሳኑ ሃገር መጥታ እንዲህ ለአፍራሾች ዱላና ድጅኖ አቀባይ በመሆኗ አዝናለሁ አልኳቸው።” ዋይ ሙን አባቱ ይላል ይሄ ጭንጋፍ የማታውቀው ነገር አለ አርፈህ ተቀመጥ አሉኝ። አልቀመጥም ልል ፈለኩና ቅድም ተናግሬው የለ አሁን ምንአስደገመኝ፣ ደፋር ለመምሰሌ እንደሆነ አንዴ ተመዝግቦልኛል ብዬ ፈርቼ ፍርሃቴም እንዳይታወቅብኝ እየተኮፈስኩ ተሰነባብተን ተለያየን።
•••
ቀጣዩ የፍርድ ቤት ቀን ደረሰ። የእኔ ምስክሮች ቀረቡ። መምህር ደጉና ሌሎቹም የመከላከያ ምስክሮቼ ቀርበው መሰከሩልኝ።
ዳኛው ሙሉ የኔታን ደጉን ይጠይቃቸዋል። ዘመድኩንን
ያውቁታል?
አዎን አውቀዋለሁ።
በጋሻውንስ?
እሱንም አውቀዋለሁ።
የትነው የሚያውቋቸው?
ተማሪዎቼ ናቸው። ዘመድኩን ጨርሷል። በጋሻው ለክረምት እረፍት እንደወጣ አልተመለሰም። በዚያው ቀርቷል። ኋላ ላይ መጋቤ ሀዲስ መባሉን ሰምቻለሁ።
ዐቃቤ ሕግ ጠየቀ?  መጋቤ ሀዲስ ተብሎ መጠራት አይችልም እንዴ?
የኔታም መለሱ። ሳላስተምረው? ሳይማር መጋቤ ሀዲስነት ከየት ይመጣል?
እና ማን ሰጠው?
እንጃ የሰጠውን ነዋ መጠየቅ።
ዳኛው ቀጠለ ዛሬ የመጡበት ጉዳይ ብሎ ብዙ ከዘበዘበ በኋላ በመጨረሻም ዘመድኩን ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክሎ ለተሃድሶ ለመናፍቅ እያለ መልስ መስጠት ይችላል እንዴ አላቸው?
እንግዲያስ። ይችላል እንጂ። አስተምረን ያስመረቅነው ኋላ ምን ሊያደርግ ኖሯል። መልስ ሊሰጥ። አንደበት ሊሆናት መስሎኝ። እና እኔስ ምን አደከመኝና አስተማሪ እሆናለሁ። ይችላል አሉት። ቀሪዎቹም እንዲሁ መስክረው። ፍርድቤቱ ጉባኤቤት መስሎ ቃለህይወት ያሰማልን ተባብለን ተለያየን። የመጨረሻ የፍርድ ቀን ደረሰ።
•••
አንድ ቀን አንድ አልባሌ የሚለብሱ እግራቸው ላይ የሚያማቸው፣ ጊዮርጊስ የሚተኙ፣ ጎንደርም አሁን ደግሞ እንጦጦ ማርያም የሚኖሩ አባት ከሱቅ መጡና ባለቤቴን ከቤታችሁ የዛሬን አሳድሩን ይላሉ። ሰውየው የተጠቀሙ መሆናቸውን አውቃለሁና ይምጡ እንሂድ ብዬ ይዣቸው ሄድኩ። ሰክረዋል አይገልጻቸውም። ሆን ብለው እንደሆነ እኔ አውቃለሁ። የብዙ ባህታውያን ጠባይም ነው። እቤት እንደደረሰን የት እናንጥፍላቸው ብለን ስንጨነቅ አንድ ሲሚንቶ ማጠራቀሚያ የነበረ ቆርቆሮ ቤት እያሳዩን እዚህ ነው የማድረው አሉ። ምንጣፍ አልፈልግም አሉ። እሺ ይሁን ብለን ተሰናብተናቸው ልንሄድ ስል ጠሩንና እርስዎ አሉኝ እኔን እኮ ነው። እርስዎ ለ3 ወር የሉም አይደለ እኔ እዚህ ሆኜ ቤቱን እጠብቃለሁ አሉን። በስካር አንደበት ነው ብለን ይሁን ብለናቸው ተለይተናቸው ወደ ክፍላችን ሄድን።
•••
በማግስቱ የፍርዱ ቀን ዳኛው ከመሬት ተነስቶ እምቧከረዩ አለ። ፎገራ። ሁሉም ሰው ደነገጠ። እኔ ዝም አልኩኝ። ቆሰቆሰኝ። ዝም ጭጭ አልኩኝ። ከጠበቃዬ ጋር ተጯጯሁ። ፍርድ ቤቱ የሆነ የፑልቤት ጸብ መሰለ። በመጨረሻም ጠበቃዬ እንዲቀመጥ አደረኩትና ዳኛውን ከመቀመጫው ብድግ ብድግ እስኪል ጋትኩት። ሁለት ጠበቆች ለሌላ ጉዳይ የመጡ ሊዳኙን፣ ሊገላግሉን ሞከሩ። አንደኛው ጠበቃ ወደ እኔ መጥተው ከፍ ባለ ድምጽ እየተቆጡኝ፣ በለሆሳስ ድምጽ ደግሞ የታባቱንስና አምበሳ ነህ አንጀቴን ነው ያራስከው እያሉ እንባና ሳቄን ቀላቀሉብኝ። ጌትነትን ጠራሁት ቆይ አሁን ባከናንበው ስንት ወር ነው የምቀጣው አልኩት? 6 ወር አለኝ። አመክሮ ሲነሳ ይቀንሳል አለኝ። ኤትአባቱ አልኩና ዳኛውን አስተማርኩት። 6 ወር ፈረደብኝ። 6 ዓመት አይሻልህም አልኩት ማቅለያ አቅርብ አለኝ። አላቀርብም አልኩት። ጠበቆቹ ክቡር ፍርድ ቤት የጥፋት ማቅለያን ጥቅም እንድናስረዳው ይፈቀድልን አሉት። አስረዱት አላቸው። እኔ አውቀዋለሁ አልኳቸው። ቤተሰብ አስተዳዳሪ ነኝ፣ ልጆቼ ሚስቴ እንድል አይደል። አልልም አልኳቸው። 5 ወር ወደ ከርቸሌ አለኝ። አንድ ቀን ጣቢያ አድሬ ወደ ከርቸሌ ነካሁት። በዚያም 3 ወር ታሪክ ሠርቼ ወጣሁ። ቆይቶ ነው እኚያ አባት ለ3 ወር የለህም ብለው የነገሩኝ ትዝ ያለኝ። እኚያ አባት አንድ ዓመት ሙሉ ከቤቴ ተቀምጠው ሄዱ። አንድ ቀን የከርቸሌ ቆይታዬን እተርክላችኋለሁ።
•••
ክፍል 4 ይቀጥላል። ታሪኩ ሙሉ ለሙሉ ጠቅልሎ ወደ ተሃድሶ ካምፕ መግባቱን፣ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ካምፕ መጠቀማቸውን፣ ከዚያም ጉዞ ወደ እንግሊዝ እንዴት እንደሆነ በአጭሩ ጠቅሼ እዘጋዋለሁ።
•••
ሻሎም !   ሰላም !  
ዘመድኩን በቀለ ነኝ። 
ሚያዝያ 2/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic