>

"ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ"  (ሶሎ ማክ ዲ)

“ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ”

 

 ሶሎ ማክ ዲ
ስቀለው ×3 የሚል ድምፅ ይሰማል
በደም የታጠበ አንድ ቦስቋላ ሰው ከፊታቸው ቆሟል
በግርፋት ብዛት ስጋው ተበጣጥሶ
ነጩን ልብስ ተገፎ ቀይ ካባ ለብሶ
አንዴ ወደ ሄድሮስ
አንዴ ከጵላጦስ
ሸንጎ ፊት ሲያቆሙት
አይሁዶች ይላሉ በርባንን ፍቱና መሲሁን ስቀሉት
ደጋግመው
ደጋግመው
ይሰቀል ይላሉ በሚያስተጋባ  ቃል
ጵላጦስም አለ “እስኪ ሰከን በሉ ግርፋቱ ይበቃል
ይህን ሰው ለመስቀል አጣሁበት በደል
በግርፋት ልፍታው አልችልም ለመስቀል”
ግና መቼ ሆኖ
የካህናት አለቆች ህዝቡን ቀሰቀሱ
ሁሉን ቻዩን ጌታ በሃሰት ከሰሱ
የሰንበት ህግ ሽሮ እውር ስላበራ
ብዙ ተዓምራትን ቀድሞ ስለሰራ
የቄሳር ንግስናን ተገዳድሯል ብለው
ህዝቡን አሳመኑ በርባንን ፍታና መሲሁን ስቀለው
ፒላጦስም አለ እጆቹን አጥርቶ በውሃ እያጠበ
“እኔ የለሁበትም እንዳሻችሁ አርጉት ብሎ ያንን ንጽህ መሲህ ለህዝብ አስረከበ
ገረፉት በብዙ እስኪታይ አጥንቱ
በመከራ ብዛት ጠፋ ደም ግባቱ
ለራሱም ደፉለት የሾህ አክሊል ሰርተው
ተራራም አስወጡት መስቀል አሸክመው
ምራቅ እየተፉ የየደበበቡት
ከጎለጎታጫፍ ቀራኒዮ አወጡት
እጆቹ እና እግሮቹን በቢስማር ቸንክረው
ውዴን ሰቀሉብኝ አይሁዶች ጨክነው
ተጠማሁ ተጠማሁ ተጠማሁ ቢላቸው
ቆምጣጤ አጠጡት በሃሞት ደባልቀው
በግራ እና በቀኝ ወንበዴዎች መሃል
በሰው ተሰቀለ ድንቅ መካር ሃያል
በመስቀል ላይ ሆኖም
በግራ እና በቀኝ ሃሳብን መዘነ
ግራው አንጓጠጥ ቀኙ ተማጠነ
አትጥፊ ያላት ነብስ ስትዘርፍ የኖረች
በባከነ ሰዓት አንድ ቃል ተናግራ ገነትን ወረሰች
የግራዋ ነብስም ትዕቢት ስላፈናት
ለፅድቅ ሳትታደል ጨለማ ወረሳት
ትንቢቱ በሙሉ ያኔ ተፈፀመ
ነብሱ ስትለየው ሰማዩ ጨለመ
በመባርቅት ድምፅ አለም ተናወፀች
ጌታዋን መስቀሏል ምድርም አወቀች
ይህ ሁሉ ሲፈፀም አዛኚቷ እናቱ መስቀል ስር ነበረች
ደም እንባ እያነባች በ አስርቱን ሃዘናት
ሰዓሊለነ ቅድስት የአምላኬ እናት
ከዮሃንስ እና ዮሴፍ ጋር አብራ
ልጇን ቀርበረችው በአሳር በመከራ
ለተጠማ ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች ርህሩ
ልጇን ሲሰቅሉባት የሃዘኗን መጠን በልብዎ ያኑሩ
ስለሰልጅ በደል
የማይሞተው ሞተ ክርስቶስ ዘ-ስጋ
ግና ሞቶ አልቀረም
ሞትን ድል አድርጓል በዕለተ ፋሲካ
Filed in: Amharic