>
5:13 pm - Sunday April 18, 3943

በዓለም ላይ በከፍተኛ መጠን በቫይረሱ ተጠቅተው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ተችሏል!!! ኢብሮ ሹመታ

ኮሮና  A-27

በዓለም ላይ በከፍተኛ መጠን በቫይረሱ ተጠቅተው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ተችሏል!!!

ኢብሮ ሹመታ
1, የኮሮና ቫይረስ በአለም ላይ ከተሰራጨ ለመጀመርያ ግዜ ትላንት ቫይረሱ ካለባቸው የሞቱት እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቡዋል 2% ሆኖ 3,751 ሰው ብቻ የሞቱ እና ከእስከዛሬው ዝቅተኛው ሆኖ ተመዝግቡዋል አለም ላይ አሁን በቫይረሱ የታያዙ ሰዎች ከ3 ሚሊየን ቢያልፍም እሚሞቱት ግን በከፍተኛ መጠን መቀነስ እንደተቻለ እየታየ ነው
 2,የእንግሊዙ:- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ስራውን አደባባይ ላይ ወቶ በወሬ  ጀምሩዋል አካኪ ዘራፍ እያለ ነበር በጠዋቱ የእንግሊዝ ህዝብ የመጀመርያውን ትልቅ መስዋትነት እና ጥረት  ከፍሎ ሁለተኛው ምእራፍ ላይ ተሻግሩዋል ብሉዋል ፣ አሁንም ህዝቡ ከዚህ ቫይረስ እንዲጠነቀቅ አስጠንቅቀዋል ፣ እንግሊዝ ካለፉት ቀናት ትላንት ለመጀመርያ ግዜ ዝቅተኛውን ሞት አስተናግዳለች 413 ብቻ በሰሞኑ ከ8መቶ ወርዶ አያቅም ነበር
3, የጣልያን:- ዘዋሪ ኮንቴ ሀገራቸው may 4 የተዘጉ ነገሮች እንደሚከፈቱ ተናግረዋል የጣልያን የእግር ኳስ ክለቦችም እየተመረመሩ ልምምድ እንደሚጀምሩ እና ቀስ እያልን በጥንቃቄ ነገሮችን ወደ ነበሩብት ለመመለስ ጥረት እናረጋለን ብለዋል ፣ ካለፉት ተከታታይ ቀናት ጣልያን እንደትናት የሟቾች ቁጥር ወርዶ አያቅም 260 ሽማግሌዎች ብቻ ናቸው የሞቱባት ።
4, ቻይና:- በፕላዝማ ትሪትምነት ህክምና ከ 10 ሺ በላይ በጸና የታመሙ በሽተኞችን እንዳዳነች ተናግራለች ከ 600-700 ቫይረሱ ኖሮባቸው ከዳኑ ሰዎች እንደተጠቀመችም አክላለች ፣ ቻይና ባለፉት ቀናት ምንም አይነት ቫይረስ የተገኘበት እንደሌለም ገልጻለች ሁቤ ግዛት የነበሩ ጥቂት በሽተኞችንም አድና ሆስፒታሎችን ዘግታለች ።
5, ከአውሮፖ:- ብዙ ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች በማዳን እስፔን አንደኛ ሄናለች ከአለም ደሞ ሁለተኛ ናት ከ 23 ሺ በላይ ቢሞትባትም ካለባት 227ሺ በሽተኛ 118 ሺ እሚሆኑት ድነው እቤት ገብተዋል ትላንትም 288 ሰው ብቻ ሞቶባት ካለፉት ግዚያቶች ዝቅተኞው ሆኖ ተመዝግቡዋል ።
6, ኢራን:- ምንም ኮሮና ቢጫወትባትም ግን በህክምና ዘርፍ ማንም አይስተካከላቸውም ለዛውም በተለያዩ ማእቀቦች ሽባ ሆና ብቻ በቃ ለህክምና ለየት ያለ ተሰጥኦ እንዳላቸው ማንም ያቃል ፣ ካለባት 90,500 በሽተኛ 70 ሺ እሚሆኑትን አድናለች ።
Filed in: Amharic