>

የሜቴክ አባት ጀነራል ፋንታ በላይ መሆናቸውን ስንታችን እናውቅ ይሆን? (ዘ አዲስ)

የሜቴክ አባት ጀነራል ፋንታ በላይ መሆናቸውን ስንታችን እናውቅ ይሆን?

ዘ አዲስ
 

 ሁሉም የመከላከያ ፋብሪካዎች የተሰሩት በነጀነራል ፋንታ ነው

ሜቴክ ካሉት ግዙፍ የመከላከያ ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱም በወያኔ ዘመን ያልተሰራ መሆኑና – የሀሳቡ ባለቤትም ሆነ ፕሮጀክቶቹን መሬት ያስነኩት እነ ጀነራል ፋንታ በላይ መሆናቸውን ስንታችን እናውቅ ይሆን? በማስረጃ ልጀምር….
ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ The Ethiopian Revolution በሚለው በባለ 437 ገጽ መጽሃፋቸው ስለ ቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊትና የውጊያ ውሎዎቹ ብዙ ጽፈዋል:: ገጽ 136 እና 137 ላይ ግን ሞስኮ ላይ ስለተካሄደውና በጸብ ስላለቀው የጀነራል ፋንታ በላይና የሩሲያዊው ከፍተኛ የጦር መኮንን አድሚራል ግሪሼን (Admiral Grishen) የጦር መሳርያ ግዢ ስብሰባ ዘርዘር አድርገው ጽፈውታል::
ጀነራል ፋንታ ሞስኮ እዚህ ስብሰባ ላይ የተገኙት የጦር መሳርያ ለመግዛት ሲሆን የራሻ አቻቸው አድሚራል ግሪሼንም ሩሲያን ወክለው ለመደራደር ነው:: ጀነራል ፋንታ በላይ ሩስያ እንድትሸጥላቸው የጠየቁት ሚግ 23 ML ( MIG 23 ML  ኢንተርሴፕተሩ( አየር ላየር የሚዋጋም ጭምር) ሲሆን BN ደግሞ ቦምበሩ ነው) , 12 ሚ 25 ( ተዋጊ ሄሌኮፕተሮች) እና 10 L-39 አውሮፕላኖችን ነበር::
ጀነራል ፋንታ ቀጠሉ ” ያሉንን ሚ 8 እና ሚ 17 ሄሌኮፕተሮችም ሩስያ እየላክን ማሳደስ (Overhaul)አንፈልግም:: ራሳችን ማደስ እንፈልጋለን:: ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ አውሮፕላን  መስራትና ማደስ እንፈልጋለን” በማለት አድሚራሉን አስደንጋጭ ጥያቄ ጠየቋቸው:: አድሚራሉም ጀነራል ፋንታ ያቀረቡት የሚ8 እና 17 ሄሌኮፕተሮችን ኢትዮጵያ ውስጥ ኦቨርሆል የሚያደርግ ኢንዱስትሪ ለመስራት እንደማይፈቅዱ ተናግረው ይልቁንስ አንቶኖቭ 12ን ግዙ ብለው ማግባባት ሲጀምሩ:: ኩሩው ጀነራል ፋንታ አንቶኖቭ 12 የደከመና የቆየ አውሮፕላን ነው እሱን እንዴት ግዙ ትሉናላችሁ ብለው በንዴት ስብሰባውን አቋርጠው ወጡ::
ፋንታ አላረፉም:: መሳርያ ከውጭ በመግዛት ኢትዮጵያ ደህንነቷን በቋሚነት ማስጠበቅ አትችልም የሚል ጠንካራ እምነት የነበራቸው የአየር ኃይል አዛዥና በኋላም በዚሁ አቋማቸው ምክንያት ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሆኑት ፋንታ በላይ – ሰሜን ኮርያን በማሳመን የስምንት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን አስጀመሩ:: ፕሮጀክቶቹ የአየር ኃይል ( ቀድሞ ሲቪል መሃንዲስ አሁን ደጀን የተባለው የአውሮፕላን ፕላንት): ጋፋት የአውቶማቲክ ጦር መሳርያ ማምረቻ : ሖርማት የተለያዩ ቀላልና ከባድ መሳርያ ጥይቶችና ፈንጂዎች ማምረቻ: አሰብ የአነስተኛን መካከለኛ ተዋጊ ጀልባዎች ፋብሪካ : ፕሮጀት 40 ሺህ በመባል የሚታወቀው የታንክና የብረት ለበስ የጦር መኪና ማምረቻ ፋብሪካና የወታደራዊ ትጥቅ ፋብሪካ ሲሆኑ – ከዚህ ጋር ከራሺያ ጋር በመደራደር ቤላሩስ ትራክተሮችን የሚያመርተውን ናትፋ( ናዝሬት ትራክተር ፋብሪካን )አቋቋሙ::
የእውቁ የታሪክ ሊቅ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተማሪ የሆነው ዶክተር ፋንታሁን አየለ The Ethiopian Army from Victory to collapse የሚለው ድንቅ የዶክትሬት ቴሲሱ  ላይ ስለያንዳንዱ ወታደራዊ ፕሮጀክቶች ይተርክልናል:: ገጽ 58
1. ጋፋት የክላሺንኮቭና መትረየስ ፋብሪካ – ሞጆና ደብረዘይት መሃል
” the North Koreans helped Ethiopia establish several armament plants. One of these was the Gafat Engineering Plant (named the Elala Gada Project) set up at Mojo. Starting
from late 1989 it was meant to produce 20,000 assault rifles of the Kalashinkov generation and 1400 LMGs annually. A total of 122,507,163 Birr was allocated for the completion of the
project.  በ1981 ሥራ የጀመረ
2. ሖርማት ( ጉደር) – የሮኬት : መድፍና ሞርታር ጥይት ፋብሪካ
“The other North Korean-supported undertaking was the Hormat Project, an
ammunition plant to be established at a place called Hormat near Gudar. The plant was planned to produce on a shift basis 50,000 shells for 60 mm mortars, 160,000 shells for 82 mm mortars 30,000 shells for 100 mm artillery guns, 50,000 shells for 122 mm field howitzers, and 20,000 shells for 130 mm artillery guns annually. The government allocated 259,200,000 Birr (125,712,391.30 USD) obtained from North Korea. The ammunition plant was expected to begin actual production in 1990. በ 1982 ሥራ የጀመረ
3.  የታንክና የጦር መኪናዎች ፋብሪካ – ደብረ ዘይት (የሚስጥር ስም መኮድ/ ፕሮጀክት 40 ሺህ)
North Korea was also a member of the consortium of Communist states besides the USSR, Rumania, Yugoslavia and China that agreed to help Ethiopia in setting up a gigantic industry for the production of small arms and heavy weapons along with their spare parts. The heavy industry
was planned to produce 7.62 mm automatic assault rifles, 7.62 mm LMGs and HMGs various anti-tank and anti-aircraft guns, mortars, 73 mm – 130 mm artillery pieces as well as T-55 main battle tanks, BTR-60 APCs, BRDM-2 and BMP-I armoured vehicles.
….
In 1989 ( 1981 Ethiopian calander), the Ethiopian government signed a project agreement with North Korea to set up a plant for the production of various explosives ranging from hand grenades to anti-tank rockets.
4. ደብረ ዘይት የአውሮፕላን ኦቨርሃውሊንግ ( Over hauling)ፕላንት  ( ቅጽል/ የሚስጥር  ስም ሲቪል መሃንዲስ)
በኋላ ስሙ ደጀን አቪዬሽን ተብሎ ስሙ የተቀየረው ፕሮጀክት  ደግሞ ሙሉ ለሙሉ የቀድሞው ኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለሙያዎች ፕሮጀክትና የአየር ኃይሉ አዛዦች የነጀነራል ፋንታ: ጀነራል አመሃ የስስት ልጅ ነበር:: በወቅቱ ሩሲያዊው አማካሪ ጀነራል የነበረው ጀነራል ሰርጌይ  ደግሞ እንዲህ  ይለናል
” የኢትዮጵያው ጀነራል ፋንታ በላይ የአውሮፕላን ኦቨርሆውል ፕላንት ኢትዮጵያው ውስጥ የመክፈቱን ሂደት ቀጥሎበታል:: ባጭር ግዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ሚጎችን ሀገሯ ውስጥ ኦቨርሆውል ታደርጋለች:;”
“The Dèrg règime had an ambitious plan to produce and overhaul heavy armored vehicles, tanks and many other medium and heavy weapons. That is why the Bishoftu complex was establish around 1987( 1979 Ethiopian calander). The Debrezeit airforce complex has also overhauled MIG fighting jets for long.”
5. የአሰብ (ሃሌብ ደሴት)  የአነስተኛ መካከለኛ ፈጣን የጦር ጀልባ ፋብሪካ
” November 1985 ( 1977 Ethiopian Calandar), North Korea provided Ethiopia a 6 million birr interest-free loan to be used to purchase equipment with which to construct a shipyard on Haleb Island, off Aseb. It was expected the shipyard to produce wooden-hulled and steel-hulled craft ranging in size from 5,000 to 150,000 tons displacement. ”  https://www.globalsecurity.org/military/world/ethiopia/industry.htm
6. ሆምቾ የጦር መሳርያ ተተኳሽ ጥይቶች እና ሮኬት ፋብሪካ The Homicho Ammunition Industry
“The first of two Ethiopian defense industry sites believed to have ties to North Korea—the Homicho Ammunition Industry—was established in 1987 ( 1979 Ethiopian calander)  as ‘Project 130’ and subsumed under the parastatal Metals and Engineering Corporation (METEC) in 2010. Based near Ambo, its production lines include: small, medium and heavy ammunition; tank shells, mortar bombs and grenades; and 120mm ‘Katyusha’ rockets.[4] The Homicho complex is the largest North Korean-assisted site.” https://www.38north.org/2014/12/aberger122314/#_ftn4
ሲጠቃለሉ
1. ጋፋት የክላሽና መትረየስ ፋብሪካ  በ 122,507,163 ብር   ተሰርቶ በ1981 ዓ.ም ሥራ ጀመረ
2. ሆርማት የመድፍና ሮኬት ጥይቶች ፋብሪካ በ259,200,000 ብር  ተሰርቶ በ1980/81 ሥራ ጀመረ
3. ሆምቾ የፈንጂና ሮኬት ፋብሪካ በ1980/81 ሥራ የጀመረ
4 ደብረ ዘይት አውሮፕላን ፕላንት ( አሁን ደጀን) በ1979 በከፊል ሥራ የጀመረ
5.ሃሌብ የፈጣን ጀልባ ፋብሪካ 1977
6. መከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ( መኮድ) 1981 በከፊል ስራ የጀመረ
7. ናዝሬት ትራክተር ፋብሪካ በ1977 የተሰራ
ሜቴክ
በአዋጅ ቁጥር 183/ 2010 እነዚህን በዘመነ ደርግ የተሰሩ የጦር መሳርያ ፋብሪካዎችን አንድ ላይ በአንድ እዝ  በማድረግ ሜቴክ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው እነ ሊቀ ዘራፊ ክንፈ ዳኘው እጅ ውስጥ ወደቁ::
ድሮ:-
 ጀነራል ሲባል የሀገሩን ሃብት ለማዳን ሲል ከነጭ ተጣልቶ ለሀገሩ ፋብሪካ የሚገነባና የሀገሩን ሃርድ ከረንሲ የሚያድን ነበር:: ታሪክ ምስክር ነው:: የነ ጀነራል ፋንታ በላይ ታሪክ ይመስክር::
ዛሬ:-
 ጀነራል ማለት ጀነራል  ጠቅላይ ሌባ ነው:: ሁሉንም የሚሰርቅ::
Filed in: Amharic