>

የሽግግር መንግስት የሚለውን ሀሳብ አልደግፈውም ስል...?!? ታየ ቦጋለ አረጋ (ኢልመ ደሱ ኦዳ)

የሽግግር መንግስት የሚለውን ሀሳብ አልደግፈውም ስል…?!?

ታየ ቦጋለ አረጋ (ኢልመ ደሱ ኦዳ)
የሽግግር መንግሥት 
ሰሞነኛ የፖለቲካ አጀንዳ በመሆን ጎልቶ የወጣውና መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነው የሽግግር መንግሥት ጉዳይ ነው። ይህንን ካርታ ከሳቡት ቡድኖችና ከበስተጀርባው ካለው ፍላጎት አኳያ፤ ይዘቱን አቅልሎ መውሰድ የማይተመን ዋጋ ያስከፍላል።
*
በዓመፅና በግርግር ለሚያተርፉ የፖለቲካ ነጋዴዎች እና ቁማርተኞች ሰለባ ላለመሆን አሥር ጊዜ ለክተን አንድ ጊዜ እንቁረጥ!!!
(((((እንቅልፍ የሚያሳጣን አንድ ሀገር ብቻ ያለን መሆኑ እንጂ፤ እንደ አብዛኛው ዳተኝነትማ ዝምታ ወርቅ በሆነ ነበር። “ሀገር የምትጠፋው ከእኩያን ሴራ ይልቅ በመልካሞች ዝምታ ነው” እንዲሉ የረጋ ወተት ቅቤ በሚወጣው ልክ፤ የረጋ ኩሬ በውስጡ የከረፋ ሽታ እንደሚፈጥር ካልተገነዘብን፤ እኛስ ብንሆን?!)))))
*
ወደ ታሪካዊ መነሻው ስንሄድ፦
የሽግግር መንግሥት በአውሮፓ ከ19ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ ጀምሮ ብቅ ያለ ሲሆን፤ ዓላማው በዋናነት ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ሀገር ተረጋግታ እንድትቀጥል የሚቋቋም ጊዜያዊ የመንግሥት አይነት ነው።
*
ከአውሮፓ ውጪ ያሉ የአብዛኞቹ ሀገሮች የሽግግር መንግሥታት ታሪክ እንደሚያሳየን በስመ የሽግግር መንግሥት የተፈጠሩ ቡድኖች፤ ሥልጣንን ጠቅልለው በመያዝ የለየላቸው አምባገነን ሆነው መከሰት ነው። ይህም ሀገሮችን ከድጡ ወደ ማጡ ሲዘፍቃቸው ተመልክተናል። ከኢራቅና ሶሚሊያ ጀምሮ… ለምዕራባውያኑ ጣልቃ ገብተው አተራምሰው ለመውጣት በር ይከፍትላቸዋል።
*
ሌላው ይቅርና በኢትዮጵያ እንኳ ጭብጣችንን መሬት ለማስያዝ ብንወስድ፦
፩ ደርግ፦ ጊዜያዊ መንግሥት (Provisional Government) በተሰኘ ስያሜ “የተፈጠረውን የሥልጣን ገዋ ለመድፈን” በሚል ብቅ ብሎ፤ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ ከወታደሩ እንኳ የተሻሉትን፦
1ኛ/ ብርጋዲየር ጀነራል ተፈሪ በንቲ
2ኛ/ ሌተናል ኮሎኔል አማንሚካኤል አምዶም
3ኛ/ ሌተናል ኮሎኔል አጥናፉ አባተ እና መሰል ቁመናዎችን በመግደል፤
በምትኩ የበታች አመራሮችን
1. እነ ሻለቃ መንግሥቱ ኃይለማርያም
2. 50አለቃ ለገሰ አስፋውና ቡድናቸውን ሥልጣን ላይ በመኮልኮል 17 ዓመታት
ደርግ፦ ደ = ደብድብ ር = ርገጥ ግ = ግዛ
(ትርጉሙ አብዮት ለውጥ ወያኔ… ማለት ቢሆንም)
እስኪባል ድረስ ኢትዮጵያን ምሁር አልባ አድርጓት አለፈ።
፪. በተመሳሳይ ነገር ግን በከፋ ሁኔታ ወያኔ የሽግግር መንግሥት (Transitional Government) የተሰኘ አወቃቀር በመፍጠር ኦነግንና መሰል የታጠቁ ያላቸውን 17 የውሸት የፖለቲካ ድርጅቶች በማጃመል አጃቢ ካደረጋቸው በኋላ፤ ከኦነግ ጀምሮ በካልቾ እየጠለዘ አባሮ፤ ቢያንስ እንደ ደርግ የኢትዮጵያ ፍቅር በሌላቸው (ተክለብርሃን ወልደአረጋይን ጨምሮ) ቁምጣ ለባሽ ሽፍቶች ተክቶ የሀገርን ክብር ለ27 ዓመታት አዋረደ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 42 የቀለም ቀንድ ምሁራንን ከመካነ ትምህርት በማባረር ጀምሮ፦
“ከደገፈን ማይምም ቢሆን ይምራ”
በሚል ከፋፋይና ግፈኛ ቡድን ፈጥሮ፤
 በተማረበት ቋንቋ መናገርና መፃፍ የማይችል – በክፍል ውስጥ እያለፈ ካባ የለበሰ፤ ውስጡ ቀፎ “ምሁር” እና የደቀቀ የትምህርት ጥራት ሳይሆን ማሽቆልቆል ፈጠረ።
 (ወያኔ ትህነግ ከደርግም የባሰ እጅግ አራጅና በህቡዕና በግልፅ ሚሊየኖችን ያጠፋ ሆኖ አለፈ።)
*
ወደ “ኮሮናው የሽግግር መንግሥት” ሀሳብ እንለፍ፦
በሀገራችን ምርጫው ከህጋዊ አማራጮች መሀከል የተሻለውን ተከትሎ ቢሄድ ለዘመናት የተገነባች ሀገር አንድ ዓመት ታግሶ፤ በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ማስቀጠል የሚቻልበት እድል ሰፊና እጅግ ተመራጩ ነው።
መጀመሪያ እስቲ ከዚህ አስከፊ የኮሮና ወረርሺኝ ማለፋችን ይታወቅ!!!!!))))))))
*
ህጋዊ ክርክሩን በምክንያት አልፌ
“የኮሮና የሽግግር መንግሥት” ይቋቋም ብንል፦
1. ለማቋቋም ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?!
2. የሚያቋቁሙት እነማናቸው?!
3. የሚቋቋሙት እነማናቸው?!
4. ምርጫ ለማካሄድ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?!
((((((((NB. እስከዚያው በማይደማመጥ “የኮሮና የሽግግር መንግሥት” እንመራ ወይስ በተረጋጋው “የብልፅግና መንግሥት”?!
በየትኛውም ደረጃ የብልፅግናውን መንግሥት እንጥላው፤ ሀገርን ለምንወድ ቢያንስ አሁን ባለው ሁኔታ ከበጣም መጥፎ ይልቅ መጥፎ የሚሆን ይመስለኛል። የጭራቆቹ አማራጭ ግን?!)))))
እዚህ ጋ ትንፋሽን ሰብሰብ አድርጎ ፖለቲከኞቻችንን ማሰብ ነው።
ወያኔን ከሰሜን በሚገባ አስቧት።
ሸኔን ከምዕራብ ዐስተውላችሁ ተመልከቱ፤
በየሠፈሩ ያሉትን የጎበዝ አለቆችና በየክልሉ የማይደማመጡ ተፃራሪ ቡድኖችን ለአፍታ ዐይናችሁን ጨፍናችሁ መዝኑ፤
ገና በሪፎርም ላይ ያለውን ሠራዊት አቋም ፈትሹ፤
 የየክልሉን ልዩ ኃይል “ተፋጠጥ” ገምግሙ፤
የኮሮናውን መዳረሻ በጥልቀት መዝኑና
“ወቪድ 83 =
ልቪድ 97 =
ጀቪድ = 86″
ፍላጎትና ምኞት …
ከግብፅ ጋር ያለን ያልተወራረደ ሂሳብ እና የዓለማቀፉን ሴራ ደረጃ ደምራችሁ፦
“የኮሮና የሽግግር መንግሥት” እናቋቁም ብንል እንኳ፦
የማቋቋሚያ አዋጅና ረቂቅን ማነሳሳት
ወደሚመለከተው ኮሚቴ መላክ
የህዝብ አስተያየት መሰብሰብ
የማፅደቅ ሂደት
የአባላቱ ስብጥርና አሰያየም
የማይደማመጡ የአቋቋሚ ኮሚሺን አባላት አካሄድ
ወዘተርፈ ሲታሰብ በራሱ የሚወስደውን ጊዜና የሚያመጣውን ጫና መመልከት ይቻላል።
*
በመጀመሪያ ደረጃ የእውነት እንነጋገር ከተባለ ህገመንግሥት አለን ወይ?!
 1923 (1931) የመጀመሪያው የተፃፈ ህገመንግሥት፣
1948 (1955) የተሻሻለው የቀኃሥ ህገመንግሥት፣
ደርግ ሊወድቅ አራት ዓመት ሲቀረው የወጣው 1979(1987) የኢህዲሪ ህገመንግሥት
እና
1987 (1995) የወጣው የወያኔና ኦነግ (የኢፌዴሪ “ህገአራዊት” = ህገመንግሥት የህዝብ ይሁንታና ህጋዊ ተቀባይነት አላቸው ወይ?! ብለን ብንጠይቅ፤ መልሱ ምን አማራጭ አለን?! ብቻ ይሆናል።
(***እኔ እንኳ ህገመንግሥት ሳይሆን ከዚህ በኋላ “ህገ ህዝብ” ይባል በማለት በተደጋጋሚ እየወተወትኩ ነው። በህዝብ የቆመ ህገመንግሥት ሲኖረን እንጂ የእስካሁኖቹማ የመንግሥት እንጂ የህዝብ አይደሉም።)
*
የዘወትር የፖለቲካ ቲያትረኛው (ተዋናዩ) ልደቱ ከዓመት በፊት ባደረገው ዲስኩር፦
“አስፈላጊ ከሆነ ህገመንግሥቱን መጣስ ይቻላል” ለማለቱ አስረጂውን የቪዲዮ ሊንክ እናያይዛለን።
*
ለማንኛውም በህግ ሙግት በተሻለው አማራጭ መጓዝ በቀጣይ የሚታይ ሆኖ፤ የሥልጣን ጥመኞች እና የኪሳቸውና የዝናቸው አምላኪዎች፤ ሀገሬን ኢትዮጵያን ወደከፋ ችግር ለመውሰድ ቀን ከሌት ሲሰለፉ፤ አንድ ጥያቄ ብቻ ጠይቃለሁ፦
መለስ ዜናዊ ከነወያኔ ፍጡራኑ እና የሁሉም አቅጣጫ እኩይ ፅንፈኞች…
(((((((******* ይህ ምስኪን 80እጅ አርሶአደር
የየፋብሪካው የደሀ ደሀ ላብ አደር
የከተማው ለፍቶ አዳሪ ምስኪን
የጎዳና ጠርዝ ነዋሪዎች (ጎዳና ተዳዳሪ አይመቸኝም)
ብርድ ላይ የሚቆሙ የገላ ገበያ ምስኪን ተሰላፊዎች
ሀገር የሚናፍቁ ስደተኞች…
በጥቅሉ ይህቺ ደሀ እናት ምስኪን ኢትዮጵያ ምን ብታደርጋቸው ነው እንዲህ ምጧን መከራና ጭንቋን የሚያበዙባት?!))))))))))))))))
*
*
*
አንረሳውም!
Filed in: Amharic