>

ግብጾችና ነገስታቱ - የአባይ  ጂኦ ፖለቲካዊ  ትንታኔና  የኢትዮጵያ  ነባራዊ  ሁኔታዎች!!! (አሉላ ቦጋለ)

ግብጾችና ነገስታቱ – የአባይ  ጂኦ ፖለቲካዊ 

ትንታኔና  የኢትዮጵያ  ነባራዊ  ሁኔታዎች!!!

አሉላ ቦጋለ
በዘመናት  በተለያዩ  ወቅቶች  በልዩ  ልዩ  መልክና  ስም  ኢትዮጵያን  ለመውረርና  የባህር  በራችንን   ለመዝጋት  ከመጡ  የውጪ  ባዕዳን  ኃይሎች ወራሪዎች  ከቅጥረኞቻቸውና   ከተላላኪዎቻቸው  ጋር  ጭምር  ትናንት  አባቶቻችን  ዛሬ  ደግሞ  እኛ  ያልተቋረጠ  ተጋድሎ  አድርገዋል    እያደረግንም  ነው።
         በዚህ  መንገድና  ቆራጥነት   የተሞላበት  የትውልዶች  ስንሰለታዊ   መወራረስ   የዚህችአገር  ዳር  ድንበር   ተከብሮ  አገራችን  ታፍራና  ተከብራ  ለመኖር  ችላለች።
    ይሁን  እንጂ  አገራችን   በመካከለኛው  ምሥራቅና  በአባይ  ሽለቆ  ባላት  ጂኦፖለቲካዊና    ስትራቴጂካዊነት   የተነሳ  መላው  የታሪካዊ  ጠላቶቻችን  ባስቀመጡት
የውስጥ  አርበኞች   5ኛው  ረድፈኞችና   የእናት  ጡት  ነካሾች  በሆኑት  ከሃዲ   የትግራይ  ወንጀለኞች  አማካይነት  ለጊዜው  የአገራችን  ዳር ድንበርና  ታሪካዊ  የባህር  በራችን   ለመነጠቅ  ተችሏል።
እንደሚታወቀው  በዘመነ  አገር  አሰሳና በቅኝ  ግዛት  ዘመን   የቀይ ባህርና   የአፍሪካ  ቀንድ  ስትራቴጂድካዊ  ጠቀሜታ  የተነሳ    ቀድመው  ለመጀመሪያ  ጊዜ   የተገነዘቡት   ቱርኮች  ሲሆኑ  ለረጅም   ጊዚያት  በመካከለኛው  ምሥራቅ    በባልካን  አገሮች   በስሜንና  ምሥራቅ  አፍርካ  ላይ  ከነበራቸው የበላይነት   በተጨማሪ  ቀይ  ባህርን   ለመቆጣጠርና   ኢትዮጵያን  ሙሉ  ለሙሉ  በቅኝ  ግዛት  ሥር  ለማድረግ  ከ16ኛው  ክፍለ ዘመን  ጀምሮ  ተደጋጋሚ  ሙከራ  አድርገው   ተሰናክለዋል።
   አልፎ  አልፎም ነገሥታቱና   መሳፍንቱ  እርስ  በርስ  ያለመስማማት   ቢኖርባቸውም   እንኳ   የኢትዮጵያዊነት  ሀገራዊ  ፍቅርና   ስሜት   ለሁሉም  የጋራ  ትውፍታዊ  ሀብታቸው   የሆነች  ሀገራቸውን  በኃይል  ለመቆጣጠር   የሚመጣውን  የባዕዳን  ወራሪ  ኃይል   በአንድነት  በመመከት   “ጥቁር  አናብስት ” የሚባሉት  ጀግኖች  ልጆችዋ  ከጫፍ  እስከ  ጫፍ  የሚያገሱባት  አገር  ጠላቶቿ  ወደ  ውስጥ   እንዳይዘልቅ  አድርገዋል።
    የቱርኮችን  እግር  ተከትለው  ወደ  አገራችን  ድንበሮች  የተጠጉት  ግብዖች   ነበሩ።      ግብዖች  ምኞታቸው  ከፍ  ያለና   የአባይን  ምንጭ  ጨምሮ  ቀይ  ባህርንና  ሜዲቴራኒያን እስከ  ህንድ  ውቅያኖስ  ያለውን  የብስ  ባህርንና  ውቅያኖችን  ለመቆጣጠር   በነበራቸው  የቆየ  ምኞት  ኢትዮጵያን  ሙሉ  ለሙሉ  ወይም  በከፊል  ከሱዳን  ጋር  ቀላቅለው  ለመግዛት  ጽኑ  ምኞትና  ህልም  አሳድረው  ይህንን  ግባቸውን  እውን  ለማድረግማሰብና  ሙከራ  ማድረግን  ከቱርኮች ተማሩ።
      ግብዖች  በአባይ  ጉዳይ  ለረጅም  ዘመናት  እንቅልፍ  ተኝተው  አያውቁም።        በአባይ  ተፋሰስ  ዙሪያ  ሰፊና  ጥልቅ  ጥናት  ያደረጉት  ፕሮፌሰር  ክንፌ  አብርሃም
(የአባይ  ጉዳይ)  በሚለው  መጽሐፋቸው   ከገጽ  11—22  ብሪቸሪ  ኮሎምቢ  የተባለውንጽሐፊ  ጠቅሰው   እንደዘገቡት  በተለይ  የእስልምናን   እምነት  የሚከተለው  የግብፅ  መንግሥት  አናሳ  በሆኑ  የግብፅ  ክርስቲያኖች ላይ  ያድርስ  የነበረውን  ግፍና  ጭቆና  የኢትዮጵያን  ነገስታት  ያስቆጣ  ስለነበር  የአባይን የውሃ  ፍሰት  አቅጣጫውን  ለማሳትና
ወደ  ግብፅ  እንዳይፈስ  ማድረግ  እንደሚችሉ  የሚገልጽ  ተደጋጋሚ  ዛቻና  ማስፈራራት  እንዲልኩ  አስገድዷቸው  ነበር።
        ከዚህ  በኋላ  ግብዖች  ኢትዮጵያን  ማዳከም  ከተቻለም  እንዲትበታተንና  እንዲትጠፋ  ማድረግ  የዘለዓለም  የቤት  አድርጋ  ወስደች።     የግብፅ  ፕሬዚዳንት  የነበሩትና  በካምፕዴቪድ  የግብፅን  ሉዓላዊነትና  ክብር  ሽጠው  በእሥራኤል  እግር ሥር ተንበርክከው እሥራኤል  1973ዓም  በኃይል  የያዘችውን  የሳናይን  በረሃ  በማስመለስ   በምትኩ  ለእሥራኤል  ዕውቅናና  የዲፕሎማቲክ  ግንኙነትከመመሥረቱም    ሌላ  ሌሎች  የአረብ  አገራትም   የእሥራኤል  ጠላት  እንዳይሆኑ  ከፍተኛ  የዲፕሎማቲክ  ሥራ  የሠሩትና  በወሮታው  ከአሜሪካ  1.5  ሚሊዮን ዶላር  በዓመት  የሚለገሥላት   አገር  መሪ  አንዋር  ሳዳት  በአንድ  ወቅት  ሲናገሩ፥
” የአባይን  የውሃ  ፍሰት  አደጋ  ላይ  የሚጥል ማንኛውም  ተግባር  በግብፅ  በኩል  ጠንካራ  የአፀፋ  እርምጃ  ይገጥመዋል   ወደ  ጦርነት የሚያመራ  ቢሆንም  እንኳን” ብለው  ነበር።ግብዖች  ከላይ  የነበረውን  በቤተክህነት  ምክንያት  ከኢትዮጵያ  ጥንታዊ  ነገሥታት  ጋር የምታደርገውን  ግጭት  ትታ
1፥ ከቤተክርስቲያኒቱ  ጋር  ሠላም  መፍጠርና  በዚያም  በኩል  ኢትዮጵያን  የምታዳክምበት    በውስጥ  ጉዳይ  ጣልቃ  እየገባች  ሁኬት   እና  ልዩነት   እየፈጠረች  የሚታዋክብበት፥
2፥ ከጎረቤት  አገሮች  ጋር  ሰላምና   መረጋጋት  እንዳይኖር   በማድረግ   ኢትዮጵያ  ሰላምና  መረጋጋት  አግኝታ  ወደ  ኢኮኖሚ  ግንባታ  በመዞር  በወንዞቿ    እንዳትጠቀም   የሚታውክበትን  ነፃ  ትኬት  ለማግኘት  ሳትታክት  የቤት  ሥራዋን  ሲትሠራ  ቆይታለች።
  ይህም  ሃቅ  እስከ  ቀዳማዊ  ኃይሌሥላሴ  ዘመነ መንግሥት  አጋማሽ  ድረስ  የራሷን  ጳጳስ እስኪታገኝ  ድረስ ፥  ግብፅ  ብዙ  ሙስልም  ሕዝብ  የሚኖርባት  አገር  ብትሆንም  የምሥራቅ  ኦርቶዶክስ  ቤተክርስቲያን  ማዕከል  በመሆን  ድርሻዋን  በሚገባ  የተጠቀመች  አገር  በመሆን  የኢትዮጵያ  ነገስታትን  ባርከው  የሚያነግሱት  ጳጳሳት  ከግብፅ  እስክንድሪያ  ውስጥ  እንዲቀቡ  የማድረጉን  ሥራ  ግብፅ  በጥበብ  ተጠቅማለች።  በዚህም  አድራጎት  ቢሆን  ግብዖች  እኛ  ፀድቀን  እንዲንኖር   ብቻም  ሳይሆን  ደልቶን
እንዳንኖር  የሚፈልጉ   ሕዝቦች  በመሆናቸው እንደገና  አስበውና  አቅደው  ለግልጽ  ወረራ ተዘጋጁ።
ኢትዮጵያን  በቅኝ  ግዛት  ለመያዝ  በእስማኤል ፓሻ  ዘመን  በአዲስና  በተጠናከረ  መልክ  በውጪ  ወታደራዊ  ባለሙያተኞች  በመታገዝ ከግብፅ  ተነስተው  ምፅዋን  ያዙ።
በዚህም  ግልጽ  ወረራ  ለማድረግ  ወደ  ምፅዋ  የገባውን  ጦር  ሙንሲንጀር  የተባለ  የስዊስ  ተወላጅ  ተቀብሏቸውና  መርቷቸው  ከረንን  ሀባብንና  መንሳን  በ1864  ዓም   ወረረ።በዚህን  ወቅት  ደግሞ  በሌላ  በጎንደር  ጠቅላይ  ግዛት  ሥር  ያሉትን  የጠረፍ  ወረዳዎች  ማለትም  መተማን አብደራፊን ቋራንና ደምቢያን  ሌላው  የግብፅ  ኃይል  ከሱዳን  እየተወረወረ  ወረረ።
በዚያው  በኤርትራ  በኩል  ከከረን  ለጥቆ   በአሥመራ  ከተማና  በምፅዋ  ወደብ  መካከል የሚገኘውን  ጊንዳዕን  በ1865ዓም  ያዙ።ዜውም  አፄ  ዮሐንስ  ሥልጣን  የያዙበት   አፍላ  ወቅት  በመሆኑና  በንጉሠ ነገሥታዊ  ዙፋን  ስር  ያሉትንና  ያመጹ  መሳፍንቶችንየማንበርከኩና   የማሳመኑ  ትግል  ራሱ  አድካሚ  በመሆኑ  የግብፅን  ግሥጋሴ  ለመግታት  ፈጣን  እርምጃ  ለመውስድ  አልቻሉም።
በዚህም  የተነሳ  ግብዖች  በይዞታቸው  ሥር  ያሉትን  ሕዝቦች  መብት  በመግፈፍ  ከፍ  ያለ  በደል   ፈጸመባቸው።ንጉሥ  አፄ  ዮሐንም  ችግሩን  ከጦርነት  ይልቅ  በሠላም  ለመፍታት  ታላቅ  ጥረት  አድርገዋል።
ለዚህም  በጊዜው  ኃያልና  ተደማጭነት  ካላቸው  የአውሮፓ  መንግሥታት  ጋር  ተጻጽፈው   በሽምግልና  እንዲረዷቸው  እየጠየቁ  ባሉበት  ወቅት   በ1867ዓም     ግብጾች  በኢትዮጵያ  ምሥራቃዊ  ክልል  የሚገኘውን   ዘ  ይ  ላ   የሚባለውን  ሌላውን  ወ  ደ  ብ  ያዘ።ቀጥለውም  ከዚያው  ተራምደው  የሐረርጌንክፍለ  ሀገር  ተቆጣጠሩ።
    ከዚያም  ዋናውንና  ጠቅላላውን  ወረራአድርገው  ወደ  ኢትዮጵያ  መሃል  ለመዝለቅ የሚከተለውን  ወታደራዊ  ዕቅድ  ነደፉ።
1፥  ከምፅዋ  የተንቀሳቀሰው  ዋናው  አጥቂ   ጦር  ካለበት  ቦታ  ተወርውሮ  መላውን  የስሜን  ደጋማ  አውራጃዎች  ከተቆጣጠረ  በኋላ  በወቅቱ  የአገሪቱ  መንበረ  መንግሥት ወደ አለበት  ወደ  ትግራይ  ጠቅላይ  ግዛት  አመራ።
2፥ የምሥራቁን  ጠቅላይ  ግዛት  የተቆጣጠረው  ወራሪ  ጦር  ከዘይላ  ወደብና ከሐረርጌ  በመነሳት  በሐረር  በኩል  ወደ  መሃል  አገር   ከማምራት  ይልቅ  በወሎ  በኩል ወደ  ት  ግ  ራ  ይ   ለመግባት  አጭርና  አቋራጭ  መንገድ  መምረጥና  ከዚያም  ከታጁራ( ጂቡቲ) ወደብ  በመነሳት  የአውሳ  አውራጃን  መቆጣጠርና  ትግራይን  ወደ ሚያዋስነው  ወ  ሎ    ጠቅላይ  ግዛት    እንዲያመራ  ሆኖ  ትግራይን  ከመሃል  አገር መቁረጥ   በመሆኑ  ከደቡባዊና  ከስሜን  አቅጣጫ  በመንቀሳቀስ  አፄ  ዮሐንስን  መቐለ  ላይ  እንደ   ጉጠት  ለመንከስ  የታቀደ  ማጥቃት  ነበር።  በዚህም  ፀረ  አንድነት  ወረራ    የስሜን  የግብፅ  ጦር  መሪ  የደንማርኩ   የጦር  መኮንን    ኤረንድሮፕ   የምሥራቁ  የግብፅ  የጦር  መሪ   ሙዚንጀር ፓሻ  ከየአቅጣጫው  ወረራውን  ቀጥለው የስሜኑ  ጦር  ከምፅዋ  ተነስቶ  ጥቅምት  14  ቀን  1868   ዓም  ዶጋሊን  ስሐጢንና  ጊንዳዕን  መላውን  አካለጉዛይ   ወረረ።ንጉስ  አፄ  ዮሐንስም  ከአድዋ  ሂዳር  2ቀን   1868  ዓም  70 ሺህ  ሠራዊት  ከትተውጉንደት  ከደረሱ  በኋላ  ገጥመው  እንደጉምበተናቸው።   እንደገናም   መልሶ  መቋቋም  አድርጎ  የመጣውን  የግብፅ  ጦር  በጉንዳጉንዲላይ  እንደ  ሾላ  ፍሬ  አረገፉ።
የምሥራቁም  በአፋር  ጅግናው  ሕዝባችን73  የሱዳንና  የግብፅ  ወታደሮች  ብቻ  ሽሽተው  ታጁራ  በመግባት  ሲተርፉ  ሌላው  በሙሉ  በአፋር  አሽዋ  ውስጥ  ሰመጠ።
በዚህ  መካከል  ንጉሡ  ወደ  ድርድር  ባመሩበት  ክፍተት  ግብፆች  ጊዜ  ሽምተው  ታህሳሥ  5  ቀን  1875   ዓም   ሌላ  ተጨማሪጦር  ምጽዋ  አራግፈው  ሳይውል  ሳያድር  ወደ  ደጋው  በመገስገስ   ከአሥመራ  40  ኪሎ  ሜትር  ጉራዕ  ላይ  ሰፈረ።
ንጉሡ  እንደገና  50  ሺህ  ጦር  ይዘውከአድዋ  በመነሳት  ወደ  ጉራዕ  ገሰገሱ።  አዲስ  የመጣው  የግብፅ  ጦር  በ40  መድፎች  ተጠናክሮ    የመጣው  የግብፅ  ወራሪ  ጦር  መጋቢት  7 ቀን  1875  ዓምክፉኛ  ተደቁሶ  ውጊያው  በዚህ  አከተመ ።
ከካይሮ  እስከ  ዛንዚባር  ድረስ  ለመግዛት  የታቀደው  የግብፅ  ቄሳራዊ  ግዛት  የመስፋፋት  ዓላማ  ከሽፎ  ለአፄ  ዮሐንስ  ትምህርት  ለመስጠት  የመጣው  የግብፅ  ወራሪ  ኃይል  ራሱ  ትምህርት  ቀስሞ  ለ3ኛ  ጊዜ  ምንም  ሙከራ  ሳይከጀል  ከሰመ።የእስማኤል  ፓሻ  የህዝብ  ድጋፍም  በእጅጉ  አሽቆለቆለ።ፓሻ  በጦርነቱ  ወቅት   እ/ር  አንድያ  ልጁን  እንደሰጠን    የግንፅ  ጦርም  ልዑላቸውን  እያየ  እንዲዋጋ  በማለት  የላከውልዑል  ሐሰንም   ኢትዮጵያን  ነፃ  ለማውጣት  ሳይሆን  ለማጥፋት  ነበር  ግን  ልሆነላቸውምከጦርነቱ  የተረፉትም  በቀይ  ባህር  እግራቸውን  ታጥበውና  በመርከብ  ተሳፍረው  ይሂዱ  እንጂ  አባይ  አፈራችንን  አጥቦ  ለም  አፈራችንን  ጭኖ  ረጅም  ርቀት  ተጉዞ  አገራቸው  ድረስ  እያመጣላቸው  ነው።
በግብፅና  በኢትዮጵያ  መካከል  ያለው  የረጅም  ዘመን  ታሪካዊ  ጠላትነት  ያለው  ነው   ዛሬ  ደግሞ  ከትናንትናው  ማለት  ከሶማሊያና  ከኤርትሪያ  ጣልቃገብነት  ተቀጥያ  የሆነውን  የውስጥ  አለመረጋጋትን  በመፍጠርና  በመጠቀም  ባለ  በሌለ  ኃይሏየሚታደርገው  ዲፕሎማሲያዊ   ሩጫ  ውሃ  አይቋጥርም  ወንዝም  አያሻግርም።
ግብፆች  ሁሉን  ነገር  የጣሉት  በአሜሪካኖችእጅ   ነው።በአንድ  ወቅት  አንድ  የአፍጋኒስታን ባለሥልጣን  ” የአሜሪካ  ወዳጅ  መሆን  ለም  አፈር  ካለው  ትልቅ  ወንዝ  ዳረቻ  ከመኖር  ጋር  ይመሳሰላል ነገር  ግን  በአንድ  ወቅት  ወንዙ  አቅጣጫውን  ሲለውጥ  ብቻህን  ምድረ-በዳ  ላይ  ትቀራለህ” እንዳለው   ቢሆንም  ዛሬ  የግብፅና  የUSA
ወዳጅነት  እንደ  ትናንቱ  ከሞቡቱ  ሴሴኮና  ከዛዬር (ኮንጎ  ዲ  ሪከሳዳም  ሁሴንና  ከኢራቅከዮናስ  ሳብምቢና  ከአንጎላ  ዓይነት  እንደ  ጧት  ጤዛ  የሚረግፍ  አይደለም።
ምክንያቱም  የስዊዝ  ቦይና  የግብፅ  እሥራኤል  ግንኙነት   ምክንያት  ግብፅ  ዛሬምበአሜሪካ  ፊት  ሞገስ  ያጣች  አይደለችም።ይሁን  እንጂ  ይህንን  ሁኔታ  በመጠቀም  ኢትዮጵያን  ተንበርካኪ  ለማድረግ  ከንቱ  ሩጫላይ  ነች።
       በዚህም  መሠረት ኦቦ  ጃዋር  ያልተረዳው ነገር  ቢኖር  ፥ የትም  የዓለም  ክፍል  የውስጥ  አለመረጋጋትና  አለመግባባት  የሚከሰተው  በመንግሥት  ሥልጣን  ጉዳይ  ብቻ  ነው።በኢትዮጵያ  ያለውና  ብሔራዊ  መግባባትን  አሳጥቶ  ላለፉት  50  ( ግማሽ ምዕተ ዓመታት)በአመጽና  በአለመረጋጋት  እየናጠን  ያለውናለግብፅም  ሆነ  ሌለሎች  ታሪካዊ  ጠላቶቻችንተጋላጭ  ያደረገን  የውስጥ  የፖለቲካ  ልዩነትበመንግሥት  ሥልጣን  አያያዝ  ጉዳይ  ሳይሆንአገርና  ሕዝብን  የመበተን  ትግል  በመሆኑ  በቀጥታና  በተዘዋዋሪ  መንገድ   የግብፅም  የሌሎች  ታሪካዊ  ጠላቶቻችን  መሳሪያና  5ኛ  ረድፈኞች  ለመሆን  በቅተናል።1969–70 በምስራቅ  በደቡብና  በስሜን  በተደረገው  ዓለም  አቀፍ  ወረራ  ወቅትኢህ አፓ  ከሞቃዲሾና  ከሻዕቢያ  ጋር  ወግኖሲቆም  በ1970   ጀምሮ     ትልቅ   የፖለቲካሽርክና  የፈጠረው  ኦነግ  የሻቢያን  ኃይልመንገድ  በመምራት  በኡንዱርማን  ሱዳን  ቀን  ቤት  ተዘግቶ ሻዕቢያ   ኢትዮጵያ  ሉዓላዊነትን  በመድፈር  1982 የአሶሳን  ከተማና  የሰፈራ  ጣቢያን  በመውረር  በቅብብሎሽ  የጦርነት  ስልት  የመንግሥትን  የመከላከል  አቅም  በመስበር  ህፃናት  ሴት  አሮጊቶችና  አቅመደካማ  ሰዎች  ሳይቀር  እንደ ሻትላና  ሳቡራ  አካባቢውን  ጽልመት  አልብሰዋል።
በውጪ  ኃይሎች  የተረቀቀውን  እና  የተሰጠውን  ፀረ  ኢትዮጵያ  ህገ መንግሥት  እንዳይሻሻልና  እንዳይነካ  በጽናት  በታገል  ጠላት  ኢትዮጵያን  ለማዳከምና  ለመበተን
የቀበረውን  የጊዜ  ቦምብ    በመጠበቅና  በዚህም  ሰበብ  ነዳጅ   ሳይቆፍር በገፍ  በሚፈስለት  ገንዘብ    መንጋ  በማደራጀት  በአንድነትየግብፅንና  የሱዳንን  ታሪካዊ  ቡርቦራና  ማዳከም  በጽናትና  በአንድነት  እንዳንመክትጋሬጣ  በመሆን  ላይ  ያለው  ራሱ  አያቶላጃዋር    ነው።
   ስለዚህ  አያቶላ  ጃዋር  የታወቀውን   የግብፅ  የአባይ  ጉዳይን  ፀረ  ኢትዮጵያ  ዕቅድና   የመካከለኛውን  ምሥራቅ  ጂኦፖለቲካዊ   ሁኔታ  ከመተንተን  ይልቅ  ብሔራዊ  መግባባት   የሚፈጠርበትን  በዘመናት  አብሮየኖሩትን  ሕዝብ  የሚበትን  የ21ኛው  ክፍለ ዘመን  የጎሳ  ፖለቲካ  የሚከስምበት ታሪካዊ  ሁኔታ  ላይ  ብሠራ   ኢትዮጵያዊነትና ብሔራዊ  ጥቅማችን  ይከበራል።
Filed in: Amharic