>
8:12 pm - Wednesday June 7, 2023

የእለቱ ወግ:- የሞሮኮው አባወራ (ተስፋዬ ሀይለማርያም)

የእለቱ ወግ:- የሞሮኮው አባወራ

ተስፋዬ ሀይለማርያም

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጃዋርን ዘብጥያ ሊያወርደው እንደሚችል የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠው ሰማን። ይህንን የ”አርፈህ ተቀመጥ” ማስጠንቀቂያ ስሰማ የሞሮኮው አባወራ ታሪክ ትዝ አለኝ።
በሞሮኮ የሚኖሩ ባልና ሚስት አንድም ቀን ሳይጣሉ 70 ዓመት ሞላቸው። በዚህ የተደነቀው ጋዜጠኛ ምስጢሩ ምን እንደሆነ አባወራውን ሲጠይቀው እንዲህ ብሎ መለሰለት፣
“የእኔና የሚስቴ የሠርጋችን ቀን ድግሱ ከተጠናቀቀ በኋላ ሙሽራዬን በአህያዬ ጭኜ እኔ በእግሬ ከጎን እየተራመድኩ ስንሄድ አህያው ሙሽራዬን መሬት ላይ ጣለብኝ።  እኔም ‘አንተ አህያ ይሄ የመጀመሪያ ጥፋትህ ነው’  አልኩት።
መንገዱን እንዳጋመስን አህያው አሁንም ሙሽራዬን መሬት ላይ ጣለብኝ። እኔም ‘አንተ አህያ! ይሄ ሁለተኛ ጥፋትህ ነው’ አልኩት።
በመጨረሻም ወደ ቤታችን ሰንቃረብ አህያዬ ሙሽራዬን መሬት ላይ ጣለብኝ።  በዚህን ጊዜ ሙሽራዬን አቅፌ አነሳኋትና ሽጉጤን አውጥቼ ግንባሩን ብዬ ገደልኩት።
ሙሽራዬም በድርጊቴ ደንግጣ በጥፊ አጮለችኝና እየጮኸች ‘አንተ እብድ ነህ! ያገባሁት ሰው በሽተኛ ነው’ እያለች ስትወራጭ እኔም እንዲህ አልኳት ‘አንቺ ሴትዮ ! ይሄ ላንቺም የመጀመሪያ ጥፋትሽ ነው”
አዎ! ለእኔ አህያው ጃዋር ሲሆን፣ ሙሽራዋ ህዝብ ነው። ባልየው ደግሞ መንግሥት።  መንግሥታችን እንደ ሞሮኮው አባወራ ለአህያው የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል። ቀጣዩን የአህያውን ጥፋትና የመንግሥትን እርምጃ በጉጉት እንጠብቃለን።
Filed in: Amharic