>

በህገ ወጥ መንገድ የመንግሥት የሥልጣን ጊዜ መራዘሙን ተከትሎ የኦነግ እና ኦፌኮ የጋራ መግለጫ

በህገ ወጥ መንገድ የመንግሥት የሥልጣን ጊዜ መራዘሙን ተከትሎ የኦነግ እና ኦፌኮ የጋራ መግለጫ

የፌዴሬሽን ምክርቤት የመንግስትን የስልጣን ዘመን በማራዘሙ ያደረብንን ስጋት መግለጽ እንወዳላን፡፡ ድርጊቱ ሕገ ወጥና ህግን ያልተከተለ ድርግጊት ስሆን ህገ መንግስቱን ከመጣሱም በላይ የሀገሪቱን ሰላም እና መረገጋት አደገ ላይ የሚጥልም ነዉ፡፡ ከመጀመሪያዉም ጀምሮ ህገ መንግስቱ የመንግስትን የስልጣን ዘመን ማራዘም የማይፈቅድ መሆኑን ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ በመሆኑም አማራጭ የመፍትሄ ሐሳብ ማቅረባችን የሚታወስ ነዉ፡፡
መንግስት ያቀረበዉን አማራጭ በመቃወም ሌላ አማራጭ የመፍትሄ ሐሳብ ብናቀርብም፤ መንግስት በተናጥል ዉሳኔዉ ጸንተዉ የተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን ወደ ህገ መንግስት አጣሪ ካዉንስል መርቶታል፡፡ ካዉንስሉም የመንግስትን አቋም ከሚደግፉት ባለሞያዎች ጋር ብቻ የይስሙላ ዉይይት በማድረግ በአሚከሱ (amicus) ላይ የተለየ ምልከታ ያለቸዉ የመደመጥ ዕድሉ ተነፍጓል፡፡ በተጨማሪም የጥቅም ግጪትን የማስቀረት መርህ ተጥሷል፡፡ ስለሆነም ዉሳኔዉ የመንግስትን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ መሆኑ የሚገርም አይሆንም፡፡
ከመሠረታዊ የዉክልና ድሞክራሲ መገለጨዎች አንደኛዉ በመደበኛነት በተወሰነ ጊዜ ምርጫ ማካሄድ እና የተመረጡትም የሕዝብ ተወካዮች የሥራ ዘመናቸዉም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ስሆን የስራ ዘመናቸዉም ስጠናቀቅ ኃላፍነታቸዉን የምለቁ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ለነሐሴ 21 2012 ዓ.ም እቅድ ተይዞለት እንደነበር የሚታወስ ነዉ፡፡ ሆኖም ግን የምርጫ ቦርድ መንግስት የኮሮናን ቨይረስ ስርጭትን ለመከላከል በእንቅስቃሴ እና በመሰብሰብ ላይ ገደብ በመጣሉ ምርጫ ለማካሄድ እንደማይችል ገለጸ፡፡ በወቅቱ ምርጨን ለማራዘም ምንም ዓይነት የህገ መንግስት መሠረት ሰይኖር አጠቃላይ ምርጫን ማንሳፈፍ ህገመንግስታዊ ቀዉስ የሚያስከትል እና ከመስከረም 30 2013 ዓ.ም በኃላ አድስ የተመረጠ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳይኖር ማንኛዉም መንግሥታዊ ዉሳኔና ድርጊት በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጠዉን የአምስት ዓመት የስራ ዘመንን የምጥስ ይሆናል፡፡  የህገመንግስቱ አንቀጽ 54(1) እና 58(3) እንዲሁም የምርጫ ህጉ አንቀጽ 7 ምርጫ በየአምስት ዓመቱ መደረግ እንደለበት ይደነግጋል፡፡ የምርጫ ጊዜን ለማራዘም በር የሚከፍት ነገር አያሳይም፡፡
የአሁኑ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በ1987 የፀደቀ ስሆን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እና በየጊዜዉ የምደረግ መደበኛ ምርጫን በሀገሪቱ እዉን ያደረገ ነዉ፡፡  የህዝቦችን በመንግስት አስተዳደር የፖለቲካ ተሳትፎ በሚየረጋግጥ መርህ የተቃኛ ስሆን፤ ህገመንግስቱ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የፖለቲካ ብዘሃነትን እንደ ወሳኝ መርህ የተቀበለ ነዉ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብት እና ተግባራትም ከህገ መንግስቱ የተቀደ ሆኖ በሀገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲ ህግ ዉስጥ ተካቷል፡፡
በሀገሪቱ የመድበለ ፓርቲ ምህዳር ዉስጥ ተመዝበዉ፤ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ ከላይ በተጠቀሱት ህጎችና መርሆዎች መመራት አለባቸዉ፡፡ ስለሆነም የአከባቢያዊ እና የፌዴራል ምርጫን በተናጠል በአንድ ፓርቲ ብቻ የማራዘም ስልጣንን አጥብቀን እንቃወማላን፡፡ የፌዴሬሽን ምክርቤት ዉሳኔ በዚህ መንግስት ለህዝብ የተገባዉ ቃል በመታጠፉ በቋፍ ላይ ያለዉን የህዝብን ቅራኔ የሚያባብስ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ወደ አመጽ ልያመራ የሚችል ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ልቀሰቀስ እንደምችል ስጋታችንን መግለጽ እንወደላን፡፡ ይህም ወደ አደባባይ የሚመልሰን ብቻ ሳይሆን ከዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የህብረተሰብ ጤና ተግዳሮቶች ጋር እየተጋፈጠ ላለዉ መንግስት ችግሩን ለመቆጣጠር አዳጋች ይሆናል፡፡
በገዢዉ ፓርቲ የኛን እና የሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመፍቴ ሐሳብ እንዲሁም የዜጎችን ጥሪ  ሙሉ በሙሉ ቸል መባሉ ከመስከረም 30 2013 ዓ.ም በኃላ የሚከሰት ህገ መንግስታዊ ቀዉስን ለማስቀረት ሁሉን አካታች የፖለቲካ ዉይይት አለማድረጉ እጅጉን የሚያሳዝን ነዉ፡፡ የገዢዉ ፓርቲ የራሱን መንግስት የሥራ ዘመን በተናጠል የማራዘም ዉሳኔ ግልጽ የሆነ ህገ መንግስታዊ ጥሰት ከመሆኑም በላይ ስልጣንን ካለአግባብ መጠቀምም ነዉ ብለን እናምናለን፡፡ በተጨማሪም በህገ መንግስቱ የተረጋገጣዉን የዲሞክራሲ እና መድበለ ፓርቲ የመንግስት አስተዳደር መርህ ጋር የሚፃረር ከመሆኑም በላይ በመንግስት ኃላፍነት የተወሰና የሥራ ዘመን የሚለዉን የህገ መንግስት መርሆን የሚሸረሽር ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት የገዢዉን ፓርቲ በተናጠል እና  ኢህገ-መንግስታዊ በሆነ መንገድ የመንግስት የሥራ ዘመንን ለማራዘም  የወሰነዉን የተናጠል ዉሳኔ አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ አሁንም በድጋሜ ገዢው ፓርቲ መድረክ አመቻችቶ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጥልቀት ተወያይቶ መፍትሄ በማመንጨት ከፓለቲካዊ መግባባት ይደረስ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ
ሰኔ 3, 2020
ፊንፊኔ
Filed in: Amharic