>
5:13 pm - Wednesday April 19, 9015

የዓብይ አህመድ አስተዳደር ኢትዮጵያን በእስላማዊ ገጽታ በመቀየሩ ስራ ተጠምዷል! (መምህር ታሪክ አበራ)

የዓብይ አህመድ አስተዳደር ኢትዮጵያን በእስላማዊ ገጽታ በመቀየሩ ስራ ተጠምዷል!

ምህር ታሪክ አበራ

★ …አረቦቹን ለማስደስትና ኢትዮጵያን የአረቦች ኢምፓየር ለማድረግ  በዓብይ አህመድ እየተሄደበት ያለው የጥፋት መንገድ በአስቸኳይ መቆም አለበት…
የሃይማኖት አባቶች፣ቅዱስ ሲኖዶስ፣መምህራነ ወንጌል፣የታሪክ ሊቃውንት ፣ሕዝበ ክርስቲያን ሁላችሁ መንግሥት ሃገርንና ታሪክን የሚያበላሽ መሰሪ ተግባር ሲፈጽም እያያችሁ በቸልታ  ዝም ማለታችሁ ይብቃ!!  ትውልድና ታሪክ አምርሮ ይወቅሳችኋል።እግዚአብሔርም ያዝንባችኋል።★
★ በኢትዮጵያ አልነጃሽ የሚባል እስላማዊ  ንጉሥ አልነገሠም ።አረቦቹን ለማስደስትና ኢትዮጵያን የአረቦች ኢምፓየር ለማድረግ  በዓብይ አህመድ እየተሄደበት ያለው የጥፋት መንገድ በአስቸኳይ መቆም አለበት።ይህ  የሃገርን ታሪክ የሚያጠለሽና የትውልድን ግንዛቤ የሚያዛባ  ሐሰተኛ ትርክት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ላይ  እንዲህ ተስቀሎ መታየቱ እጅግ አሳፋሪ ነው።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን የተሳሳተ የመንግሥት ሴራ በሕዝብ መገልገያ አይሮፕላን ላይ ለጥፎ መንቀሳቀስ የለበትም።ይህ የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቅና ምን ታመጣላቹ የሚል የዕብሪት መልዕክት ነው።ይህንን አጥብቀን እንቃወማለን!! ★
ዓብይ አህመድ ከአፍሪካ ሕብረት ጽ/ቤት አጠገብ አልነጃሽ የተባለ መስኪድ እንዲሰራ ማዘዙና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ይህ ስም ተለጥፎ በዓለም አቀፍ በረራዎች  እንዲተዋወቅ ማስደረጉ እንደ እባብ ገላውን አለስልሶ መርዝ የሆነ ተንኮል በሀገሪቱ ላይ እየሰራ መሆኑን ማሳያ ነውና ክርስቲያኖች ይህንን የክፋት አካሄድ እንደቀላል ሳናይ አጥብቀን ልንቃወም ይገባል።
Filed in: Amharic