>
6:04 pm - Wednesday June 7, 2023

ችግሩ ከስም አይደለም !  (ታዬ ደንደአ)

ችግሩ ከስም አይደለም ! 

(ታዬ ደንደአ)
* ባንዳነት የግል ባህሪ ነዉ! ባንዳ ከየትኛዉም ብሔር ወይም ሀይማኖት ሊሆን ይችላል! ለግል ፍላጎቱ የሀገሩን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ሰዉ ባንዳ ነዉ! 
—-
አንዳንዶች ስለባንዳነታቸዉ ሲጠየቁ በስም ሊያታልሉ ይሞክራሉ! የአባታቸዉ ስም መሀመድ ወይም ጀማል ባይሆን እንደማይጠረጠሩ ያወራሉ። ግን ይህ አባባል እራሱ ባንዳነት ነዉ! የህዝብን አንድነት በሀይማኖት ምክንያት ለማላላት የተሸረበ ሴራ!
ባንዳነት የግል ባህሪ ነዉ! ባንዳ ከየትኛዉም ብሔር ወይም ሀይማኖት ሊሆን ይችላል! ለግል ፍላጎቱ የሀገሩን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ሰዉ ባንዳ ነዉ! ጀግንነትም በብሔር ወይም በስም ወይም በሀይማኖት አይወሰንም።
ለሀገሩ ጥቅም በቁርጠኝነት የሚሰለፍ ሁሉ ጀግና ነዉ! መሀመድ አል-አሩሲ፣ ሸኪራ፣ ሰብሪና  እና ብዙ ሌሎች በራሳቸዉ ተነሳሽነት ለኢትዮጵያ ጥቅም የሚታገሉ ጀግኖች ናቸዉ።
ጌታቸዉ፣ ህዝቄል፣ ፀጋዬ እና ሌሎች በርካታ ደግሞ ለግል እና ለቡድን ፍላጎታቸዉ ከግብፅ ጋር ኢትዮጵያ ላይ የሚያሴሩ ባንዳዎች ናቸዉ! ችግሩ የስም ወይም የሀይማኖት አይደለም!
እውነት ነው! ኢትዮጵያዊ ሰውን የሚመዝነው በአስተሳሰቡ እና ለሀገሩ ባለው ቀናኢነት ነው። ሙስጠፌን የወደደው እና ጃዋርን የሚቃወመው ለሀገር ባላቸው እይታ እና አቋም ብቻ ነው!!
Filed in: Amharic