>

"የአስቴር ጉዳይ አሳሳቢ ሆናል፤  እስክንድር ነጋን ስንታየሁ ቸኮል ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል!!! " ( ገለታው ዘለቀ)

“የአስቴር ጉዳይ አሳሳቢ ሆናል፤ 

እስክንድር ነጋን ስንታየሁ ቸኮል ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል!!! ”  ገለታው ዘለቀ

ዮሴፍ የእሱወርቅ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ  ተጠባባቂ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀን  ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አነጋግሬው የሚከተለውን እንዳስተላልፍለት ጠይቋል!!
ገለታው:- እስክንድር ነጋን ለጥቂት ደቂቃዎች እንዳገኘውና እንዳናገረው ና….
1ኛ  ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበትና
2ኛ  ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር በሆነች ድፍን ( confined) ክፍል ውስጥ እሱንና ስንታየሁ ቸኮልን ለየብቻ እንዳጎሯቸው
3ኛ ከክክፍሉ ጥበት በተጨማሪ እጅግ ቀዝቃዛ በመሆኑ ለበሽታ እንዳረጋለን በሚል መስጋቱን ገልፆፅኛል ብሏል።
ገለታው ለእስክንድር ስንቅ እንዳቀበለው ገልፆ ስንታየሁን ለማናገር “ከአንድ ሰው በላይ ማየት አይቻልም” በመባሉ እንዳላገኘው ሆኖም የስንታየሁ ባለቤት ልብስ እንዳቀበለችው ነግራኛለች ብሏል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ እቶ ገለታው ዘለቀ ለ2 ትኛ ጊዜ  እስክንድርን እንዳገኘውና ለመጀመሪያ ጊዜ ከስንታየሁ ጋር እንደተገናኘ ስንታየሁም  ድብደባ እንደተፈፀመበት አረጋግጦልኛል ብሏል
አስቴርን በተመለከተ ” ከበላይ አካል ትእዛዝ ስላልመጣ “ማየትም ማግኘትም ስንቅ ማቀበልም እንዳልተቻለ ባለቤቷም  ሊያገኛት እንዳልቻለ ከተያዘችም 48 ሰአት እንዳለፈው ና በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳለች ነግሮኛል።
በመጨረሻም ገለታው  “በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እዚህ ያለነው ድምጻችን ስለታፈነ ድምፅ ሁኑን” ብሏል።የስልክ መስመሩ ከፍትኛ የጥራት ችግር ነበረበት!!!!
Filed in: Amharic