>

የዘር ማጥፋት እርምጃ በመንግስታዊ ሀይሎች እገዛ ተፈጽሟል‼ (እንግዳ ወልዳይ)

የዘር ማጥፋት እርምጃ በመንግስታዊ ሀይሎች እገዛ ተፈጽሟል‼

እንግዳ ወልዳይ

 

በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት(የጄኖሳይድ) መስፈርትን በሚገባ የሚያሟላ ወንጀል ተፈጽሟል።  እየተፈጸመም ይገኛል። 
 
ይህ እውነታውን በመሸፋፈን ሐቁንና መሐሉን የሌላው ተቃራኒ እድርጎ በመፈረጅ የሌለ የምርኮኛ መሐል ለመፍጠር የሚደረግ የቆዬ ብዙ ዋጋ ያስከፈለ የጅሎች ልማድ ነው።
ኢትዬጵያን በእውነትና በጥሬ ሀቅ ላይ እንጅ በ False Center and False Equivalence ማዳን አይቻልም።
ኦሮሞ ስለሞተ የዘር ፍጅት ሊሆን አይችልም ማለት ወንጀለኛ ለመደበቅ የሚደረግ ወንጀል ነው።
ሩዋንዳ የሁቱ ጽንፈኞች ቱትሲዎችን ሲፈጁ ከቱትሲ ጋር ወዳጅ ናቸው የተባሉ ሁቱዎችንም አብረው ነበር የፈጁት።
ሁቱዎች ስለሞቱ ግን ያ የዘር ማጥፋት ወንጀል አይደለም አልተባለም።
የዖሮሞ ጽንፈኞች የአማራ ና የሌላው ጎሳ ወዳጅ የሆኑ፣ ወይም መግደል ያልፈለጉና ማተብ ያሰሩ ኦሮሞዎችን ከሌላው ጋር አብረው ስለፈጁ የዘር ማጥፋት አይደለም ማለት አይቻልም።
የዘር ማጥፋት የሚሆነው ዘር ለይቶ ጥቃት ለፈጸም በግልጽ አውጆ ተነስቶ በመግደሉ ነው።
ስለዚህ ይህንን ወንጀል ያዘጋጁ፣ የረዱና ያስፈጸሙ የአገሪቱና የዓለም አቀፍ ሕጉ በሚያስገድደው መሰረት በመላው ዓለም ታድነው ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ይህንን የዘር ፍጅት ለማደባበስ፣ ለመደባበቅ የሚደረግ ሙከራ የወንጀሉ ተባባሪነት ነው የሚሆነው።Geleta Gammo
 
 
ጄኖሳይድ በኢትዮጵያ?
********************
በሃገራችን ጄነሳይድ (የዘር ማጥፋት) ተፈጽሟል አልተፈጸመም ለሚለው ጥያቄ የጄኒቫ ከንቬንሽንና በጉዳዩ ላይ የሚሰሩት የ Genocide Watch ፕረዝደንት Gregory H. Stanton የሚሉትን በዝርዝር መመልከት ጠቃሚ ነው። የፌስቡክ የሰሞኑ ንትርክም እነዚህን ሰነዶች የተመሰረተ ቢሆን ጠቃሚ ነው።
በቅድሚያ የጄኒቫ ከንቬንሽን የዘር ማጥፋትን እንዴት ይገልጸዋል? በቀጥታ የእንግሊዝኛውን ቅጂ እንውሰድ፣ ከዛም የግሬገሪ ስታንተንን የጄነሳይድ ስምንት ደረጃዎች ወስደን በእኛ ሃገር እየተፈጸመ ያለውን በአማርኛ እናክላለን።
In the present Convention, genocide means any of the following acts committed with intent to destroy, in whole or in part, a national, ethnical, racial or religious group, as such:
A. Killing members of the group;
B. Causing serious bodily or mental harm to members of the group;
C. Deliberately inflicting on the group conditions of life calculated to bring about its physical destruction in whole or in part;
D. Imposing measures intended to prevent births within the group;
E. Forcibly transferring children of the group to another group.
በሰሞኑ በቪኦኤ፣ በዶቸ ቬለና በሌሎችም የዜና አውታሮች የወጡትን ሪፖርቶች እንዲሁም የሟቾች ቤተሰቦች የሰጧቸውን ቃለመጠይቆች ላዳመጠ ከላይ ከ A እስከ C መፈጸማቸውን ያረጋግጣል። አማሮችና ክርስቲያኖች ኢላማ መደረጋቸውን ሪፖርቶቹ ከበቂ በላይ ግልጽ አድርገዋል። የሟች ቤተሰቦች እንደተናገሩት አስከሬን በአካባቢው እንዳይቀብሩ በገዳዮቹ ተከልክለዋል። በ D ና በ E የተጠቀሱትም  በአንድ ወይም በሌላ ወቅት በሃገራችን መፈጸማቸው አያከራክርም።
በግሬገሪ ስታንተን ትንተና መሰረት ደግሞ የዘር ማጥፋት ስምንት ደረጃዎች አሉት:
→ The first is Classification, when we classify the world into us versus them.
እኛና እነሱ የሚለው ክፍፍል በሃገራችን ከተጀመረ ከራርሟል። “ጨቋኝ”ና”ተጨቋኝ” ከታሪክ ተመርጦ እየተቀነጨበ ለጥላቻ ቅስቀሳና ለበቀል ማነሳሻ ውሏል።
→ The second is Symbolization, when we give names to those classifications like Jew and Aryan, Hutu and Tutsi, Turk and Armenian. Sometimes the symbols are physical, like the Nazi yellow star. Classification and symbolization are universally human and do not necessarily result in genocide unless they lead to dehumanization.
ነፍጠኛ፣አማራ፣ኦሮሞ፣ትግሬ፣ጉራጌ፣  ወዘተ። እነዚህ ስሞች በራሳቸው ችግር የላቸውም። አንድን ወገን ለማራከስና ለማንቋሸሽ ስንጠቀም ግን ችግር ይሆናሉ።
→ The third is Dehumanization, when perpetrators call their victims rats, or cockroaches, cancer, or disease; so eliminating them is actually seen as “cleansing” the society, rather than murder.
“አማራ ቆማጣ!” “Down Down Amhara!” “Down Down ነፍጠኛ!” የሰሞኑ መፈክር።
→ The fourth is Organization, when hate groups, armies, and militias organize.
ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ጥቃቱን የፈጸሙት በቡድን የተደራጁና የሚያጠቁትን ሰውና ንብረት መዝግበው የመጡ መሆናቸው ተገልጿል።
→ The fifth is Polarization, when moderates are targeted who could stop the process, especially moderates from the perpetrators’ group.
ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦችና በጥላቻ የታጨቁ ስብከቶች በትንተና መልክ ሲሰራጩ ከርመዋል። ከጥቃት ፈጻሚዎቹ ወገን የሆኑ ግን ጥቃቱን የማይደግፉ ወይም ለዘብተኛ የሆኑት ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። ግድያን ለማስቆም ጥረት ያደርጉ ግለሰቦች የግፍ ጽዋው ቀማሽ ሆነዋል።
→ The sixth stage is Preparation. Victims are identified and separated out because of their ethnic or religious
identity. Death lists are drawn up.
አማሮችና ክርስቲያኖች ኢላማ ተደርገዋል። አጥቂዎቹም የተገዳዮችን ስም ዝርዝር ይዘው እንደመጡ በሪፖርቶች ተጠቁሟል።
→ The seventh stage is Extermination, what we legally define as genocide, the intentional destruction, in whole or in part, of a national, ethnic, racial, or religious group.
ይህ ደረጃ ህጋዊ የጄነሳይድ ትርጉምን የሚገልጽና ሆን ተብሎ አንድ ቡድንን ለማጥፋት የሚፈጸም ጥቃት ነው። ይህም በሰሞኑ በግልጽ ተከናውኗል።
→ Denial. It is actually a continuation of the genocide, because it is a continuing attempt to destroy the victim group psychologically and culturally, to deny its members even the memory of the murders of their relatives.
Denial has a profoundly negative impact on everyone concerned. Denial harms the victims and their survivors.
ይህ ደረጃ የዘር ማጥፋት መፈጸሙን መካድ ነው። ክደቱ የዘር ማጥፋት ሂደቱን እንደመቀጠልም ይቆጠራል። ምክንያቱም የተጠቂዎች ወገን ላይ የስነልቦናና ባህላዊ ተጽህኖ በማድረግ ሃዘናቸውን እንኳ እንዳይወጡ ያደርጋል።
Filed in: Amharic