>
9:52 am - Friday June 2, 2023

‹‹ኦሮሞም ተገድሏልኮ...!››  አዎ ገላችኋቸዋል! ግን...!!! (አሌክስ አብርሃም)

‹‹ኦሮሞም ተገድሏልኮ…!››  አዎ ገላችኋቸዋል! ግን…!!!

አሌክስ አብርሃም

ከ1941 እስከ 1945 ሂትለር በመላው አውሮፓ አይሁዶችን በዘር እየለየ ሲጨፈጭፍ  ወደ 63 ሽ የሚደርሱ የሂትለር የራሱ አገር ዜጎችም በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ነበር ! አንዳንዶች ታዲያ  ልክ የዛሬዎቹ የኛ  ጨፍጫፊዎችን ሽፋን ለመስጠት ‹ኦሮሞም ተገድሏልኮ ›› እያሉ እንደሚጋጋጡት   ‹‹ጀርመኖችም ተገድለዋልኮ እንዴት ዘረኝነት ሊሆን ይችላል?››  እያሉ መከራከሪያ ማቅረባቸውን ሳነብ ወይ የክፉዎች  መመሳሰል ነው ያስባለኝ ! የጀርመን ዜጎች ለምን እንደተገደሉ ታውቃላችሁ? …. ከራሳቸው ዘር የወጡ  ገዳዮች በአይሁዶች ላይ የሚያደርሱትን ግፍ ስለተቃወሙና አይሁዶችን በቤታቸው ደብቀው ለማዳን ሲሞክሩ ስለተደረሰባቸው እና የአይሁዶችን ባህል እምነት ተከትላችኋል ተብለው ጭምር ነበር ፡፡
አሁንም ተገደሉ የተባሉት ኦሮሞዎች የተገደሉት በክልላቸው የሚኖሩ አማራዎችና ሌሎች ብሔሮች ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃዎማቸው ፣ ቄሮ የሚባለውን ገዳይ ቡድን ባለመደገፋቸው አንዳንዶቹም አማርኛ በመናገራቸውና ‹‹የነፍጠኛ ሐይማኖት ›› ተከታይ ናችሁ ተብለው  ጭምር እንጅ እንደሚባለው ግድያው ብሔር የማይለይ ስለሆነ አይደለም !! አታስተባብሉት ….ኦሮሚያ ውስጥ  ቄሮ በተባለ ቡድን ያውም የፀጥታ አካላት እና የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ የክልሉ ሹሞች የተሳተፉበት የዘር ፍጅት ተፈፅሟል !!
በአለማችን ላይ ከተፈፀሙ የዘር ፍጅቶች የኦሮሚያው የሚለየው …በተገደሉት ሰዎች ቁጥር ብቻ ነው ! ይህን ነገር አሁንም በግልፅ አምኖ የድርጊቱን ፈፃሚዎች እንቅስቃሴ  በሽብር ድርጊት ካልተፈረጀ … ነገም ያው የሰዓት ቦምብ ነው ! አታድበስብሱ !! ጃዋር ተከበብኩ ሲል በተመሳሳይ የቁጥር ተዋፅኦ ለማድበስበስ ተሞከረ ይሄው አሁን ከባለፈው ብሶና አሰቃቂ ሁኖ ቀጠለ ! ዛሬም ይህንን ካድበሰበሳችሁላቸው ገዳዩ ቀን ጠብቆ ለባሰ ጥፋት ገጀራውን ስሎ ይወጣል ! አታድበስብሱ ! ውሸትና ማደባበስ ላይ የተመሰረተ አንድነት የእንቧይ ካብ ነው !!
Filed in: Amharic