>
2:05 pm - Thursday March 30, 2023

በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ  ያነጣጠረ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ነው የተፈጸመው!!! (ታደለ ጥበቡ)

በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ  ያነጣጠረ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ነው የተፈጸመው!!!

ታደለ ጥበቡ

 * በተለይ በአማራ ላይ ያነጣጠረ የዘር-ማፅዳት ወንጀል ነው የተፈጸመው!!!
 
 አገዳደሉ ምናልባት ምድር ከተፈጠረች ጀምሮ ያልተፈፀመ፣ በታሪክና በመዝገብ ተጽፎ የማይገኝ ጭካኔ የተሞላበት ነው። የዘጠኝ ወር እርጉዝ እናት ሆዷን ጨፍልቀው ገድለዋታል። ምዕመናን ማተባችሁን በጥሱ  እየተባሉ አንገታቸውን በሰይፍ ተቀልቷል። ልባቸውን በጦር እየተወጉ፣ ወደ እሳት እየተጣሉ፣ በመጥረቢያ እጅና እግራቸው እየተቆራረጠ ተገድለዋል። በድንጋይ ጭንቅላታቸው  እየተጨፈለቀ ተሰውተዋል።
በጭካኔ መግደል አልበቃ ብሏቸው፣ ልጅ የአባቱን፣ አባት የልጁን ሬሳ እንዳያነሱ ተከለከሉ። አልቅሶ መቅበር “መብታችሁ አይደለም” ተባሉ። ሟች በገዛ ሀገራቸው ሁለት ክንድ የመቃብር ቦታ ተነፍጓቸው ሬሳቸው የጅብ እራት ሆኖ ቀረ።
የዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ መንግስታዊ ድጋፍ ያለውም ነው። የክርስቲያኖች ቤትና ንብረት ሲወድም፣ የሰውን ልጅ ጭንቅላት በመጥረቢያ  እንደ እንደ ዱባ ከሁለት ሲከፍሉት፣ እጅና እግሩን ታስሮ በመኪና ሲጎተት፣  የኦሮሚያ ፖሊስ ቆሞ ይመለከት ነበረ። አንዳንዴም ከግድያው ያግዛል፥ ከዘረፋውም ተሳታፊ ነበሩ።
ብልፅግና ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ ከ50 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል። በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በአሰቃቂ ሁኔታ እንደ በግ ታርደዋል።
ይሄ ሁሉ የዘር ጭፍጨፋ ተደበስብሶ መቅረት የለበትም። እያንዳንዷን በነቂስ እናወጠዋለን። ለታሪክም እንዲቀመጥ የሟቾችን ፎቶ እና የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን በትክክል አምተ ምህረቱና ቀኑ ተመዝግቦ በመጽሐፍ መታተም ይኖርበታል!
Filed in: Amharic