>
5:13 pm - Sunday April 18, 2202

ሹም፤ ሽር ----- ሕዝብ እና የአገዛዝ ሥርዓት  (ያሬድ ሀይለማርያም)

ሹም፤ ሽር —– ሕዝብ እና የአገዛዝ ሥርዓት 

ያሬድ ሀይለማርያም
ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ባልሆነበት አገር ሿሚም፤ ሻሪም ገዢው አካል ወይም የአገዛዝ ሥርዓቱ ስለሆነ ሰዎች ለምን እንደተሾሙ፣ ለምን እንደተሻሩ፣ መቼ እንደሚሾሙ እና መቼ እንደሚሻሩ የሚያውቀው እና ወሳኙ ገዢው አካል ብቻ ነው። በአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ሕዝብ እገሌ በድሎናል ስላለ ሰው ከሥልጣኑ አይወርድም፣ አይጠየቅም።
በተቃራኒውም ይሔ ሰው ይበጀናል ስላለ አይሾምም። ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት በሆነበት አገር ደግሞ አንድ ሰው ሲሾምም፤ ሲሻርም ለሕዝብ በሚረዳው መልኩ በቂ ምክንያት እና የተሿሚውን እውቀት፣ ልምድ፣ አቅም እና ጨዋነት መሰረት ያደረገ ማብራሪያ ይሰጣል። ከስልጣኑ ሲሻርም ባጠፋው ልክ ተጠያቂ ይደረጋል። ባለማውም ልክ ይወደሳል። እንደው በደፈናው እገሌ ከዚህ ተነስቶ እዚህ ቦታ ተሰይሟል፣ እገሌ በእገሊት ተተክቷል የሚል ሽፍንፍን ዜና ግራ ያጋባል። ሥልጣን እና ተጠያቂነት (accountability) ገና አልተገናኝቶም።
Filed in: Amharic