>

ይድረስ ለፕሮፌሰር መረራ ጉዲና:- (አቻምየለህ ታምሩ)

ይድረስ ለፕሮፌሰር መረራ ጉዲና:-

«በመስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር በሌሎች ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ ወርዋሪ አይሆንም»

 [ክፍል ፩]
   አቻምየለህ ታምሩ

የዛሬን አያድርገውና «በመስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር በሌሎች ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ ወርዋሪ አይሆንም» የሚለው አባባል ከዛሬ 24 ዓመታት በፊት በጥር ወር 1988 ዓ.ም. በጦብያ መጽሔት ላይ ያሳተሙትንና  የኦነግን ተነግሮ የማያልቅ ጉድ  ለኦሮሞ ሕዝብ ያስረዱበት ባለ ሁለት ክፍል ጽሑፍ ርዕስ ነበር። ጽሑፍዎ ኦነጋውያን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ፈጸሙ ያሉትን ጥፋት የሚያጋልጥና የአንድ መንደር የፀሎት ቤት ኬክ ገማጮች ያሏቸውን ኦነጋውያንን  የነሱ መንደር [የወለጋ] ተወላጆች ባለመሆናቸው “የነፍጠኛ ሥርዓት አገልጋዮች”  እያሉ  ያወግዟቸዋል ያሏቸውን ነፍጠኞቹን  እነ ራስ ጎበናን፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስን፣ ራስ አበበን፣ ጀኔራል ጃገማ ኬሎን፣ ወዘተ የሚከላከል ነበር።
የጹፍዎን ርዕስ «በመስታወት ቤት የሚኖር በሌሎች ላይ ድንጋይ ለመወርወር የመጀመሪያው አይሆንም» ለማለት የተገደዱትም ኦነጋውያን ርስዎንና መሰሎችዎን  “ቀይ ጎበናዎች” እያሉ በሚያቀርቡባችሁ ክሶች ሊጠየቁ የሚገባቸው እናንተ ሳትሆኑ እነሱ መሆናቸውን ለማስረዳት ነበር።
እኔም ዛሬ «በመስታወት ቤት የሚኖር በሌሎች ላይ ድንጋይ ለመወርወር የመጀመሪያው አይሆንም» በሚል የርስዎ ርዕስ ለርስዎ ተደራሽ የሆነ ጦማር ለመጻፍ የተነሳሁት “በማምለጥ ላይ ያለ አዲስ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሙከራ” የሚል ርዕስ ሰጥተው  ባሳለፍነው ቅዳሜ ባፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን  የስብሰባ አዳራሽ ባቀረቡት ጭፍን አቋምዎ በዳግማዊ ምኒልክና በኢትዮጵያ ነገሥታት ላይ በዘረዘሩት የፈጠራ ክስና የጭካኔ ተግባር ሊጠየቁ የሚገባቸው የኢትዮጵያ ነገሥታት ሳይሆኑ የኦሮሞ አባገዳዎች መሆናቸውን ለማስረዳት ነው።
 በመሆኑን ማንነት በማጥፋት፣ የሰው ርስት በመቀማት፣ የራስ ያልነበረ ባድማን በመውረር፣ የሰው ቋንቋ በማጥፋት፣ ጡት በመቁረጥና ተነግሮ የማያልቅ የጭካኔ ተግባሮችን በመደርደር በኢትዮጵያ ነገሥታት ላይ ድንጋይ ለመወርወር እናንተ በመስታወት ቤት ውስጥ የምትኖሩት የኦሮሞ ብሔርተኞች የመጀመሪያዎቹ ልትሆኑ አይገባም።
የዛሬ የኢትዮጵያ ችግር የኢትዮጵያ ነገሥታት ወደ ኦሮሞ አገር ሄደው ማንነት ስላጠፉ፣ የሰው ርስት ስለቀሙ፣ የኢትዮጵያ ያልነበረ የሰው ባድማ ስለወረሩ፣ የነገዶችን ቋንቋ  ስላጠፉ፣ ጡት ስለቆረጡና ተነግሮ የማያልቁ የጭካኔ ተግባሮችን ስለፈጸሙ የተፈጠረ ሳይሆን ኦሮሞ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ማንነት ስላጠፋ፣ የሰው ርስት ስለቀማ፣ የኦሮሞ ያልነበረ ባድማን ስለወረረ፣ ከ28 በላይ የኢትዮጵያ ነገዶችን ቋንቋ  ስላጠፋ፣ ጡት ስለቆረጠና ተነግረው የማያልቁ የጭካኔ ተግባሮችን በኢትዮጵያ የጥንት ነገዶች ላይ ስለፈጸመ  የተፈጠረ ነው።
የርስዎን ርዕስ ተጠቅሜ የጽሑፌን ርዕስ  «በመስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር በሌሎች ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ ወርዋሪ አይሆንም» እንድልና  እርስዎ በኢትዮጵያ ነገሥታት ላይ፤ በተለይም በዳግማዊ ምኒልክ ላይ በሰነዘሯቸው ክሶች ከሁሉ በላይ ቀዳሚ ተጠያቂዎቹ የኦሮሞ አባገዳዎችና የመንፈስ ልጆቻቸው እንጂ ዳግማዊ ምኒልክና የኢትዮጵያ ነገሥታት አለመሆናቸውን ሁለቱን ያስጮኋቸውን የፈጠራ ክሶችዎን በማንሳት ላስረዳ።
የመጀመሪያው በዳግማዊ ምኒልክ ላይ የሰነዘሩት ክስ አኖሌ ላይ ጡት ቆርጠዋል የሚል ነው። ለዚህ የፈጠራ ክስ ግን አንድም የታሪክ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። ሆኖም ግን ኦነግ የኦሮሞን ጡት እንደቆረጠ የሽግግር መንግሥት ተብዮው ምክር ቤት  ያቋቋመው አጣሪ ኮሜቴ ያረጋገጠውንና የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት የነበሩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የሕይዎት ታሪካቸውን ባሳተሙበት  በጽሐፍት ውስጥ አረጋግጠውስ ይገኛል።  ዶክተር ነጋሶ ኦነግ ስለቆረጠው የኦሮሞ ሴቶች ጡት “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” በሚል ርዕስ በ2003 ዓ.ም. ባታተመው ግለ ታሪካቸው ገጽ 150 ላይ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል፤
“ሁኔታው እኮ መስመሩን የሳተ ነበር። የኦሕዴድ ሴት ታጋዮች ጡት ይቆረጥ ነበር። ወንዶች ደግሞ የጭናቸው  ስጋ እየተቆረጠ ብሉት ይባሉ ነበር። በነዚህ ላይ የኦነግ አመራር እርምጃ አይወስድም ነበር።”
ለምን በጎ አላማ እታገላለሁ እንደሚሉ ራሳቸውም የማያውቁት ፕሮፈሰር መረራ ጉዲና ግን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባቋቋሙት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ውስጥ ያን ሁሉ ልብ ወለድ ተረት በዳግማዊ ምኒልክ ላይ ሲደረድሩ እንዲህ አይነቱን  የተረጋገጠ ኦነግ  የቆረጠው የኦሮሞ  ሰቶች ጡት ታሪክ ሲያስታውሱ አልፈለጉም።
ከዚህ በተጨማሪ አርሲ  ሴት ገድሎ ጡት የመቁረጥ ባሕል እንዳለውና በዚህም ሴት ገድሎ  ጡት የመቁረጥ ባሕሉ በጉጂዎች ዘንድ እንደሚፈራ የፕሮፈሰር መረራ የነገድ ወንድም የሆኑት  ኦሮሞው የታሪክ ምሑር ፕሮፈሰር ታደሰ በሪሶ በ1980 ዓ.ም.  በሚችጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ  ዲግሪቸውን ሲያጠናቅቁ  ባቀረቡት ጥናት ላይ አመሳክተዋል።
ፕሮፌሰር ታደሰ በሪሶ “Traditional Warfare among the Guji of Southern Ethiopia”  በሚል ርዕስ ባቀረቡት የሁለተኛ ዲግሪ ጥናታቸው ገጽ 31 ላይ ጡት የመቁረጥ ባሕል የአርሲ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ጥናታቸውን አቅርበዋል፤
“… Arsi used to kill women and take their breasts as a trophy. For this reason they were the most feared group aaong the neighbors of Guji.”
ከዚህ የፕሮፌሰር ታደሰ በሪሶ ጥናት ጡት የቆረጠና ጡት መቁረጥን ባሕሉ ያደረገው አርሲ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን በጡት መቁረጥ የሚከሱት ሴት እየገደለ  ጡት ሲቀርጥና የቆረጠውን ጡት  ወደ ጎጆው ይዞ ሲመለስ በኖረው በአርሲ ባሕል ነው። ዳግማዊ ምኒልክን በጡት መቁረጥ  የሚከሱትን እነ ፕሮፈሰር መረራን «በመስታወት ቤት የሚኖር በሌሎች ላይ ድንጋይ ለመወርወር የመጀመሪያው አይሆንም» የምለው።
ምህ ይኼ ብቻ። በኦሮሞ ጥናት ጥርሱን የነቀለው እንግሊዛዊው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ጆርጅ  ሐንቲንግፎርድ  “The Galla of Ethiopia; The Kingdoms of Kafa and Janjero” በሚል ርዕስ  በ1948 ዓ.ም. ባሳተመው ጥናት ውስጥ የኦሮሞ የገዢ  መደብ ድርጅት የሆነው የገዳ ሥርዓት ከሌሎች ወታደራዊ ሥርዓቶች የሚለይበትን በምርኮኞች ላይ ሳይቀር እንዲፈጸም  የሚፈቅደውንና ተቋማዊ ያደረገውን ritualized የሆነው culture of violence  “Murder as an institution” በሚል  ንዑስ ርዕስ ገጽ 64 ላይ እንዲህ  አቅርቦታል፤
“… The desire of the Galla to kill seems to have horrified even the Abyssinians; and a man was not considered a full man till he had killed a human being – very Galla claimed “the right to kill”. Even so, the rest of the Galla themselves looked up on Arusi as especially ferocious, for them to murder at the time of great festivals is both an honor and a social necessity, though if an Arusi kills a fellow-tribesman it is believed that he will get leprosy; but inter-tribal murders are allowed without penalty, particularly at the end of each Luba period. Before setting out to commit a “murder for honor” the Arusi drinks large quantities of blood, which produces a condition of frenzy. Since the murder nearly always a cowardly one, they hide and kill unsuspecting wayfarers, emasculating them and taking home the genitals a trophy. On their return the murderers enact the scene, with cries of triumph and derisive imitation of the victim’s anguish. Only after such a murder may a man wear a copper ring in his ear. When several men take part in a murder, the honor goes to him who strikes the first blow. Hence there is often much quarreling. A man who sets out before a festival to kill and returns unsuccessful is not only ridiculed but is branded on the forehead and given a small jar of milk which he has to make into butter as a sign that he is not a man. No man could hold a position in the gada-government unless he had killed a man or a large animal.”
ትርጉም፤
“የተቀሩት የኦሮሞ ጎሳዎች ሳይቀሩ አርሲዎች የተለየ ጭካኔ እንደነበራቸው ያምኑ ነበር፡፡ለነሱ እያንዳንዱ ክብረ በአል መጨረሻ ላይ ሰው መግደል የክብር ምልክት እና ማኅበራዊ ግዴታ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡አንድ አርሲ ሌላውን አርሲ ከገደለ በለምጽ ይመታል የሚል እምነት አላቸው፡፡ ይሁን እንጂ አንድ አርሲ የሌላውን ጎሳ አባል እንዲገድል ተፈቅዶለታል፡፡ አንድ አርሲ ለግድያ ከመሰማራቱ በፊት ለወኔው ማነሳሻ ብዙ ደም ይጠጣል፡፡ ከዚያም አገር አማን ነው ብሎ የሚሄደውን መንገደኛ አድብቶ ይገድልና ብልቱን ቆርጦ ወደ ጎጆው ይመለሳል፡፡ ሲመለስ ፉከራ ያሰማል፡፡ እንዲሁም የተገደለው ሰውየ ያሰማውን የጣእር ድምጽ አስመስሎ በመጮህ ያፌዛል፡፡ አንድ ወንድ ይህንን ማድረግ ከቻለ ብቻ ነው በጆሮው ላይ የብር ሎቲ ማንጠልጠል የሚፈቀድለት።  ግድያው የተፈጸመው በቡድን ከሆነ፣ የመጀመርያውን በትር ያሳረፈው የገዳይነቱን ክብር ይቀዳጃል፡፡ በቡድን ሆነው በሚገድሉበት ጊዜ እኔ ነኝ ቀድሜ የገደልሁ፤ እኔ ነኝ ቀድሜ የገደልሁ በሚል ፉክክር ጠብ የሚቀሰቀስበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ከክብረ በዓሉ በፊት ሰው ገድሎ መመለስ ያልቻለ ሰው ውርደት ይከናነባል፤ በግንባሩ ላይ ምልክት ይደረግበትና ወንድ አለመሆኑ ለማሳየት በትንሽ እቃ ወተት ተሰጥቶት ቅቤ እስኪወጣ ድረስ እንዲገፋው ይደረጋል። አንድ ሰው ትልቅ አውሬ ወይም ሰው ካልገደለ በቀር በገዳ ስርዓት ውስጥ ቦታ አይኖረውም፡፡”
ዳግማዊ ምኒልክን በተረት ላይ ተመስርተው በጨካኝነት የሚከሱት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዲህ አይነቱን ቀደምት አርሲዎች ለክብራቸው ሲሉ  በወጡበት በሚያስቀሯቸው ሰላማዊ  የሌላ ነገድ ተወላጆች ላይ ሲፈጸሙ የኖሩትን ተቋማዊ ግፍ ሁሉን የሚዳስሱ   ጉዳዮች በሚቀርቡበት ብሔራዊ መግባባት የሚል የዳቦ ስም በተሰጠው መድረክ አንዱንም እንኳ ለማስታውስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ነው። ልብ በሉ! አርሲዎች ለክብራቸው  ሲሉ  ጡት  ሲቆርጡና ደም እየጠጡ በሌሎች ነገዶች ላይ ተነግሮ የማያልቅ ግፍ ሲፈጸሙ የኖሩት በአውደ ውጊያ ጦርነት በገጠሟቸው ባላንጣዎች ላይ ሳይሆን አገር ሰላም ብለው ከቤት በወጡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው።  በታሪክ ደረሰብኝ የሚለውን በተረት የፈጠረው ግፍ የሚደረድር ሰው የተመዘገበ ታሪክ ያለውን የኦሮሞ ወረራ ያደረሰውን ጥፋትና በተለይም አርሲ ሴት እየገደለ ጡት በመቁረጥ የቆረጠውን ጡት ወደ ጎጆው ወስዶ ይዝናናበትና የክብሩ መገለጫ ያደረገው እንደነበር አብሮ ለማስታወስ  ወኔውን ያጣ ሰው  የኔ የሚለው ሕይዎት ከሌላው  የበለጠ ዋጋ አለው የሚል ጨካኝ ፍጡርና ያገጠጠ ዘረኛ ብቻ ነው።
በመሆኑም ቀደም ሲል በማስረጃ የቀረበው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጭካኔ እየፈጸሙ ይዝናኑና ለክብራቸው ሲሉ የሰት ጡት እየቆረጡ ወደ ጎጇቸው መውሰድን ባሕላቸው ያደረጉ ሰዎች የመንፈስ ልጆችና የዚያ የጭካኔ ባሕል ባለቤት የሆኑት የኦሮሞ ብሔርተኞች ዳግማዊ ምኒልክን በጡት ቆራጭነትና በጭካኔ ለመክሰስ የመጀመሪያዎቹ  ሊሆኑ አይገባም።  ለዚህ ነው ይህንን ጽሑፌን «በመስታወት ቤት የሚኖር በሌሎች ላይ ድንጋይ ለመወርወር የመጀመሪያው አይሆንም» ያልኩት።
ይቀጥላል. . .
Filed in: Amharic