>
5:13 pm - Thursday April 18, 7011

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ሊቃወመው የሚገባው አፓርታይዳዊ አሰራር ...!!! (መ/ር ታሪኩ አበራ)

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ሊቃወመው የሚገባው አፓርታይዳዊ አሰራር …!!!

መ/ር ታሪኩ አበራ
* ይህ ትውልድ ገዳይና ግልጽ የዘረኝነት አሰራር ይቁም!!

ማሳሰቢያ:- ትምህርትን በአፋን ኦሮሞ ተቀናጅቶ በሚሰጥበት ት/ቤት ካሉ ርእሰ መምህራን አንዱ  የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ መስማትና መናገር፤ ማንበብና መጻፍ የሚችልና መቻሉን በፈተና ማረጋገጥ ይኖርበታል
—-
የሁሉም ርዕሰ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ያውም በከተማዋ መሐል በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የኦሮምኛ ቋንቋ ብቻ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎችን በየትምህርት ተቋማት በማስገባት ሌሎች ምዑራንን ለመግፋት እየተሄደበት ያለው መንግሥታዊ አሻጥር እጅግ አሳፋሪና ትውልድ ገዳይ ሥርዐት ስለሆነ በፍጥነት መቆም አለበት።በቂ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን የሌላ ብሔር ተወላጅ  ትውልድ አሻጋሪ ምዑራንን ይህንን በመሰለ ዓይን ያወጣ መንግሥታዊ ሥርዓት አልበኝነት መግፋት የትውልዱን መጻዒ ሕይወት ማጨለም ነውና በፍጥነት ይቁም።ምዑራንም ይህ ሥር እየሰደደ የመጣውን  መንግሥታዊ ጋጠወጥነት አጥብቃችሁ ልትቃወሙ ይገባል። በዘረኛው የመንግሥት ዕዝና በትምህርት ሚንስቴር ይሁንታ እየተፈጸመ ያለው ይህ ዘመኑን የማይመጥን የትምህርት አስተዳደር በዓለም አቀፍና በአፍሪካ የትምህርት ጥራት ደረጃ እጅግ አንሶ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አካዳሚ ኳሊቲ የበለጠ የሚያዘቅጥና ትውልድን ከዕውቀት ውድድር ውጪ የሚያደርግ ነው። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም የልጆቻችሁን የወደፊት ሕይወት የሚያጨልመውን ይህንን መሰሪ አካሄድ አጥብቃችሁ ልትቃወሙ ይገባል።
Filed in: Amharic