>

ያልተመለሱ ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች... ለከንቲባ አዳነች አቤቤ...?!? (ያሬድ ሀይለማርያም)

ያልተመለሱ ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች… ለከንቲባ አዳነች አቤቤ…?!?

ያሬድ ሀይለማርያም

የትላንቱ የካቢኔዎ ውሳኔ ‘ፍየል ከመድረሷ …’ ስለሆነበኝ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንስቻለሁ፤
+ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ፕሮጀክት መስተዳድሩ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስንት ሰዎች ተመዘገቡ?
+ ስንት ሰዎች ተመዝግበው እስከ ዛሬ ድረስ ቁጠባውን ሳያስተጓጉሉ ከፈሉ?
+ መስተዳድሩ ፕሮጀክቱን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስንት የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ሰራ?
+ ከቆጠቡት ሰዎች ውስጥ ስንት ሰዎች እጣ ወጣላቸው?
+ የእጣ አወጣጡ ሂደት ምን ይመስል ነበር? ስንት ጊዜስ እጣ ወጣ?
+ እጣ ከወጣላቸው ሰዎች ውስጥ ስንት ሰዎች ቤታቸውን ተረከቡ?
+ ስንት ሰዎች እጣ ወጥቶላቸው ነገር ግን ቤቱን ሳይረከቡ ቀሩ? በምን ምክንያት?
+ ቁጠባ ሳይቆጥቡ እና እጣ ሳይወጣላቸው ስንት ሰዎች የቤት ባለቤት ሆኑ? በምን ምክንያት?
+ አሁንስ ስንት የኮንዶሚኒየም ሕንጻዎች ተሰርተው ተጠናቀዋል? ለነዋሪዎች ያልተረከቡና ባዷቸውን የቆሙ ስንት ቤቶች አሉ? እነዚህን ለማን እና በምን ሁኔታ ሊሰጡ ታስቧል?
+ ትላንት ካቢኔዎች ባስተላለፈው ፍርደ ገምድል ውሳኔ ላይ፤ ተመዝግባችው ያልደረሳችሁ ቆጣቢዎች በማህበር ተደራጅታችሁ እራሳችሁ ገንቡ፤ መሬት እንሰጣለን ብለዋል። ማን ነው የሚያደራጃቸው? የት ተገናኝተው ነው የሚደራጁት? እንደ ገና ከዚህ በኋላ ስንት አመት ቤት ለማግኘት ደጅ ሊጠኑ ነው?
+ መስተዳድሩ ከቆጣቢዎች ጋር የገባው ውል ቤት ሰርቶ ሊያስረክብ ነው። ያንን ውል በእርሶ ካቢኔ ውሳኔ ድንገት ተነስቶ ማፍረስ ይቻላል ወይ? በውሉ መፍረስ መስተዳድሩ ሊጠየቅ አይችልም ወይ?
+ ዱሮውንም ሕዝብ መንግስት ላይ እምነት እንዳልነበርው እየታወቀ እና ሕዝቡም በግማሽ ልብ አምኗችሁ ከልጆቹ ጉሮሮ ነጥቆ ያጠራቀመውን ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን ተስፋውንም በዚህ መልኩ አመድ ስታረጉት ከሕዝብ ጋር ያላችሁን ግንኙነት እና አመኔታ ሙሉ በሙሉ አይበጣጥሰውም ወይ?
+  በአቶ ታከለ ኡማ ላይ ከኮንዶሚኒየም ቤቶች አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ በርካታ ቅሬታዎች እና የሞስና መሰል ቅሬታዎች እያሉ ያንን አጣርቶ እና ከላይ ያነሳዋቸውን ጥያቄዎች በሚመልስ መልኩ የምርመራ ሥራ ሰርተው ሪፖርት ሳያቀርቡ እንዲ አይነት የተቻኮለ ውሳኔ በካቢኔዎ በኩል ማስተላለፍዎስ ትክክለኛ አሰራር ነው ወይ?
የካቢኔዎት ውሳኔ ፍየል ከመድረሷ እንዳይሆን ነገሩን በጥንቃቄ መያዝ የሚበጅ እና ከላይ የተነሱትን እና ሌሎች ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በቅድሚያ ማጥራት እና በአግባቡ መመለስ አይሻልም?
Filed in: Amharic