>

ጳጉሜ 6 እና  7 መሆኗ እንዴት? ለምን?!? (ዶ/ር ዲያቆን ሮዳስ ታደሰ)

ጳጉሜ 6 እና  7 መሆኗ እንዴት? ለምን?!?

ዶ/ር ዲያቆን ሮዳስ ታደሰ

ዘመናት ሲቆጠሩ ዘመነ ማርቆስ፣ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ሉቃስ እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው።ሁልጊዜም ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር ጳጉሜ 6 ትሆናለች።ይህ እንዴት ሆነ?በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አውሻህር መፅሐፍ ላይ የዘመን አቆጣጠር አባቶች አስቀምጠውታል።3ቱ አመታት 365 ቀን ከ6 ሰአት ይይዛሉ።ስለዚህ የሶስቱ አመታት የ6 ሰዓታት ጥርቅም 18 ይሆናል።ከዛን ዘመነ ሉቃስ ተገባዶ ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር 18+6=24 ሰአት ይሆናል ስለዚህ በየአራት አመቱ ጳጉሜ 6  ሆናለች። በፈረንጆቹ leap year ይሉታል እሱም February ወር 29 ቀናትን ይይዛል ።በእኛ መጠነ ራብኢት ማለትም ዘመነ ዮሐንስ የሚውልበት።ቀደምት አባቶች ጳጉሜ 7 ቀናትን የሚይዝበት አመት እንዳለ ፅፈው አስቀምጠዋል።እሱም በ600 አመት አንዴ ይከሰታል።
በቀን ሰዓታት ውስጥ ተጨማሪ 0.4 ሰከንድ አለ።ስሌቷም በብራና መፃህፍት ላይ ተፅፏል።ሪና መአልትና ሪና ሌሊት የሚል ስሌት ነው።በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 365 እለት ከ15 ኬክሮስ ከ6ካልኢት ወይንም 365 ቀን ከ6 ሰአት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው።ስለዚህ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ተጠራቅሞ ጳጉሜን 7 ያደርጓታል።ካልኢት ማለት 24 ሰከንድ ነው።የ5 አመት 30 ካልኢት የ10 አመት 60 ካልኢት ነው።60 ካልኢት ደግሞ 24 ሰከንድ ነው።የ100 አመት 240 ሰከንድ ወይም 10 ኬክሮስ የ200 አመት 20 ኬክሮስ የ300 አመት 30 ኬክሮስ የ400 አመት 40 ኬክሮስ የ500 አመት 50 ኬክሮስ የ600 አመት 60 ኬክሮስ።60 ኬክሮስ 1440 ደቂቃ  ወይም 24 ሰአት ይሆናል።ስለዚህ በ600 አመት አንዴ ጳጉሜ 7 ይሆናል።ይህንን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና መፃህፍት ላይ ተፅፎ ይገኛል።
Filed in: Amharic