>
5:13 pm - Sunday April 18, 3982

አብን ከብልፅግና እና ከኦነግ ጋር  በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጋራ  ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሰ!!!  (ዘሪሁን ገሰሰ)

አብን ከብልፅግና እና ከኦነግ ጋር  በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጋራ  ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሰ!!! 

ዘሪሁን ገሰሰ

 

 በአብንና በኦሮሞ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል ፥ ላለፈው አንድ አመት ሲደረግ የነበረው ፖለቲካዊ ድርድር ዛሬ በሸራተን አዲስ በተደረገው የስምምነት ፊርማ ስነስርዓት  ተጠናቀቀ!
 
* <<  ይህ አስር የጋራ ነጥቦች የሠፈሩበት ስምምነት ፥ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያንና ያለፉት አማራን እንደህዝብ ያጠፉ የህዝብና ቤት ቆጠራዎችን ውጤት መሠረዝን የጋራ የሚያደርግና ያካተተ ነው!>>
አብን ከኦሮሞ የፖለቲካ ሐይሎች ጋር ፥ ከአንድ አመት በላይ ብዙ ውጣውረድ የታየባቸው ፥ የፖለቲካ ድርድሮችን ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሁሉም ሀይሎች መሠረታዊና በአቋም ደረጃ የያዟቸውን ነጥቦች ይዘው ሲከራከሩና ሲደራደሩባቸውም ነበር፡፡ አንዳንዶቹ አብን ፈፅሞውኑ ለድርድር የማያቀርባቸው አጀንዳዎች ፥ በሌሎች ሀይሎች ዘንድ ደግሞ የተለየ እይታ በመኖሩ በነዚህ ላይ ለመግባባት እልህ አስጨራሽ ጉዞዎች ተጉዟል፡፡
ከነዚህ መሠረታዊ ነጥቦች መካከል ደግሞ “የህገመንግስቱ ጉዳይና ያለፉት የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤቶች መሠረዝ ” ጉዳይ እጅግ አጨቃጫቂና ረዥሙን ጊዜ የወሠደ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አብን ለሁሉም የሀገራችን ህዝቦች ጠቃሜታ ያለውና ለሀገር ህልውና መሠረታዊ ነጥብ የሆነው ፅኑ አቋሙን ይዞ እስከመጨረሻው በመጓዝ  ሌሎችን ማሳመንና ሀሳቡን ገዥና ሁሉንም የሚያግባባ እንዲሆን አድርጓል፡፡
በዚሁም መሠረት በአብንና በኦሮሞ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል ፥ ከላይ የጠቀስኳቸውን ሁለት ነጥቦች ጨምሮ በአስር ስምምነት በተደረሰባቸው አጀንዳዎች ላይ ፥ የጋራ መግባባት መፍጠር የሚያስችል የስምምነት ሠነድ ፥ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተደራዳሪ ሀይሎቹ ተፈርሟል፡፡ ይህ በአብንና በኦሮሞ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል የተደረሠ ስምምነት ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያንና ያለፉት አማራን እንደህዝብ ያጠፉ የህዝብና ቤት ቆጠራዎችን ውጤት መሠረዝን የጋራ የሚያደርግና ያካተተ ናቸው፡፡
ፖለቲካ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ድርድርና ውይይት ለህዝብና ለሐገር የሚበጀውን ሀሳብ ገዢና አሸናፊ አድርጎ የጋራ መግባባትን መፍጠር እንደመሆኑ መጠን ፥ አብን ከአንዳንድ አመት በላይ የወሠደውን ፖለቲካዊ ድርድር ሁሉንም አሸናፊነት / Win win / መርህ ባደረገ መልኩ ከመጨረሻው ምዕራፍ መድረሱ ፥ እንደ ትልቅ ፖለቲካዊ ድል የሚቆጠር ነው!!!
ይህ ዘላቂ ሠላምንና በሠጥቶ መቀበል ላይ የተመሠረተ ተቀራራቢ ሀሳብ ማንሸራሸር የሚያስችል ፖለቲካዊ ድርድር ፥ እንዲፀናና ወደመሬት እንዲወርድ ደግሞ የእያንዳንዳችን አስተዋፅኦ የጎላ ነው!
// የጋራ ስምምነት ፈራሚ የፖለቲካ ሐይሎቹ መግለጫ እየተጠበቀ ነው! //
እጣፋንታችንን በእጆቻችን እንፅፋለን!
Filed in: Amharic