>

ጋዜጠኛ ተመስገን እና ጋዜጠኛ ውብሸት እንኳን ደሳላችሁ

ጋዜጠኛ ተመስገን እና ጋዜጠኛ ውብሸት እንኳን ደሳላችሁ

ህብር ራዲዮ
የፍትህ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና የኢትዮጵያ ዳይጀስት ዋና አዘጋጅ  ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ የአመቱ የ2020 “Pen2Pen Örebro – Freedom of Expression Award”. ተሸላሚዎች ለመሆን በቅተዋል።
ሀሳብን በነጻ   ለመግለጽ ለሚደረገው ትግል አስተዋጽዎ በማድረጋቸው የአመቱ ተሸላሚዎች የሆኑት ጋዜጠኛ ተመስገን እና ጋዜጠኛ ውብሸት በተለያዩ ጊዜያት ለእስራት ቢዳረጉም ሙያዊ ኃላፊነታቸውን  ለአንድ አፍታም ባለማቋረጣችው   የአመቱ ተሸላሚዎች ሆነዋል።
እኤአ ከ1960ዎቹ  ጀምሮ  ለጋጋዜጠኞች የሚሰጠው ይህ ታላቅ ሽልማት ባለፈው አመት ለደ/አፍሪካ ጋዜጠኛ እና ለቱርክ ጋዜጠኛ ተሰጥቷል።  የስዊድን ዜግነት ያለው  ትውልደ ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ዳዊት ይሳቅም ሽልማቱ እንደተሰጠው ከደርጅቱ የገኘው  መረጃ ይገልጻል።
የህብር ራዲዮ ዝግጅት ክፍል በዚህ አጋጣሚ ለሙያ ወንድሞቻችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ  በመላው አለም በሚገኙ የ ነጻ ፕሬስ  ቤተሰቦች ስም እንኳን ደስሳላችሁ፣እንኳን ደሳላን ለማለት ይወዳል።
•••
በዚሁ አጋጣሚ ኢትዮ ሪፈረንስ ዝግጅት ክፍልም ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና ውብሸት ታዬ የተሰማንን ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን።
Filed in: Amharic