እናመሰግናለን ……
ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን
ለከፈልከው መስዋዕት ለዋልከው ውለታ፣
ምስጋና ነው ያለን – ታላቅ ሰው የኔታ!
.
ባልታጠፈ ግንባር፣ በነደደ ወኔ – ፍልሚያ የገባኸው፣
በብዕር ወረንጦ – አምባገነኖችን – ያብረከረካቸው፣
አንተን ጀግናችንን – አንሸኝህም በዕንባ፣
በድል ዝማሬ ነው – በጉሮ ወሸባ፤
በሆታ ምንሰድህ – ወደፈጣሪ አምባ።
ያውም በምስጋና!!!
ካለአንዳች ፍርሃት – በአምባገነኖች ፊት – የኖርክ ነህና!!!
.
ለከፈልከው መስዋዕት ለዋልከው ውለታ፣
በስተመጨረሻ – እነሆ ምስጋና – ታላቅ ሰው የኔታ