>
5:21 pm - Wednesday July 21, 9548

በአዲስ አበባና በመቐለ የመሸጉ ህገወጥ  ግልገል  ንጉሶች ሰጣ ገባ እስከ መቸ ?ወዴትስ ያደርሳል ?!? (አስገደ ገብረስላሴ- መቐለ ) 

በአዲስ አበባና በመቐለ የመሸጉ ህገወጥ  ግልገል  ንጉሶች ሰጣ ገባ እስከ መቸ ?ወዴትስ ያደርሳል ?!?

አስገደ ገብረስላሴ – – 

*  እረ ባካቹሁ በሁለት አመት ተኩል ያለቀ ህዝብ የወደመ ሀብት የተፈናቀሉ ህዝቦች ይብቃን…!!!
በፈደራል የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት፤በፈደረሽን ምክር ቤት እና በትግራይ ክልል ምከርቤት ስራ  አስፈጻሚ መካከል ያለው ሰጣገባ በሁለቱ አካላት እየተፈጸመ ያለው  ኢህጋዊ ድርጊት ለሀገራችንና ህዝቦቻ ወደ የማያባራ ግጭት የሚያመራ ያለ   ህዝብም የሚጎዳ ሆኖ ይታየኛል። በመሆኑም ለነዚህ ህገወጥ ሽፍቶች ህዝብ ማስታገሻ ያድርግባቸው ።ዝምታ እና መንበርከኩ እስከ መቸ?
የዚሁ ጠንቆች ደግሞ በዋናነት የሚጠቀሱ  በአዲስ አበባ የመሸገው ራሱ ብልጽግና ፓርቲ ብሎ የሰየመ  እና መቐለ መሸገው የሚገኙ የህዋሓት አማራር እንዲሁም የነሱ ታማኝ ካድሬዎቻቸው ናቸው ። የነዚሁን አንባገነኖች  ሽፍቶች አካየድ የኢትዮጱያ ህዝቦች ተቃውሞ ያሰማ ፣
 1ኛ   በአሁኑ ጊዜ አዲስአበባ የመሸገው ራሱ ህዋሓት ኢህአደግ በአምሳሉ ቀርጾ  አሳድጎ  አሰልጥኖ ያስቀመጠው በኢህአደግ ሸፍጥ  ፣ውሼት ሙያ የተካነው በኢህአደግ ታማኝ ካድሪዎች የተገነባ  ራሱ ብልጽግና ፓርት ብሎ የሰየመ  ከነባሩ ህዋሓት ኢህአደግ  ህገወጥ ቡዱን ከመሆኑም በላይ የሚሊዮኖች ውድ ኢትዮጱያውያን ፣ ሙሁራን ፣ ተማሪዎች ፣ወዛደሮች ፣አርሶ አደሮች የትግልና መስዋእቲ  የተከፈለበት ውጤት የጸደቀው  ህገመንግስት በማፍረስ ሁሉም በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎች መብቶች የሚያስጠብቁ  አፍርሶ የቀበረ  ከመሆኑም አልፎ  ህግ ሽፋን አድርጎ ዘመናዊ የአዲስ አበባ የረጋ የበሰበሰ   ሽፍታ (ስተግናንት ላንፐን)   ሀገርና ህዝብ እያታራመሰ ያለው የሌቦች ስብስብ ቡዱን በህዝባችን ሲቀልድ ምንኛ ያሳዝናል ።እዳው በሀገር ለዚሁ ስድ ስርአት  ማስታገሻ የሚያደርግ  በዚህ ሀገር ህዝብ የለም ወይ ያስብላል ።
 2ኛ 27 አመት ሙሉ ስልጣን በማያዝ ህዝቦች የታገሉበት አላማ ወደ ጎን በመጣል  በስልጣን የባለገ ፤ በ17 አመት ጸረ ፋሽሽት ደርግና የዘውዳዊ ስርአት ርዝራዥ ጨቋኖች  ለማስወገድ የተደረገው ትግል 200 000 ወጣቶች የተሰውበት ፣በሞቶ ሽዎች  የሚቆጠሩ ወገኖች የቆሰሉበት አካላቸው የጎደሉበት  ፤እሱን በቀሰቀሰው ህዝባዊ ትግል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንደ ቅጠል የረገፉበት ፣ሰላም አጥተው የተሰደዱበት ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ሀፍት የወደመበት የትግል ውጤት ሊፈጽምና  ለማስፈጸም የተሳነው   ህዝብ የሰጠው ሀላፍነት  ፍጹም በመካድ የህዝብ የትግል መስዋእት ውጤት ለራሱ ፣ለልጆቹ ፣ለዘመድ አዝማዱ ፣የሙሱና  ሸሪኮቹ በማስቀደም 27 አመት ሙሉ ተንደላቅቆ ኖሮ ከከዛ ከመዘበረ በኃላ በራሱ ውስጣዊ ብስባሴና በመላው የኢትዮጱያ ህዝቦች ትግል ተሸነፎ  ከአዲስ አበባ ተነቅሎ ተባርሮ  27 አመት ክድቶት ወደ  ኖረው  ትግራይ ክልል ህዝብ  በተልይ  መቐለ ከተማ በመምጣት እኖሆ 2 አመት ተኩል ተቀምጧል ።
           በነዚህ  ሁለት አመትም ተኩል ትግራይ ሲቀመጥ  ያለፈው ገመናዬ ይበቃል  ብሎ አርፎ እንደ መቀመጥ  ፈንታ የትግራይ ህዝብ ከጨቋኞች ነጻ ለማውጣት 17 አመት ታግሎ ያጸደቀው ህገመንግስት በመናድ እሱን የሚመስሉ የውሼት ተቃዋሚ ፓቲዎች በመፍጠር ( ራሱ ህዋሓት ራሱን የሚመስሉ እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ በመስራት )  ኢህጋዊ ምርጫ በመካየድ የተግራይ ህዝብ ገንጥሎ የክልሉ ደ ህገወጥ ዲፋክቶ  ንጉስ  ለመሆን የራሱ ጠንካራ ሰራዊት በማሰልጠንና በማደራጀት ከፈደራል  መንግስት ለመፋለም    ስልጣን አይጠገብምና 17 አመት  መራራ ትግል ታግሎ ከባድ መስዋእት ከፍሎ  ወደ ስልጣን  ላወጣው የትግራይ ህዝብ  መልሶ ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ለማስገባት የክልላችን  የመንግስት ባጀት ፣የህዝባችን ገንዘብ ቁሳቁስ የአርሶ አደርም እንጀራ ሳይቀር  ከእለት ጉርሱ እየቀነሰ  ለወታደሩ እንዲሰጥ በማድረግ  ለአማራች ወጣቱ ስራ በመፍጠር ወደ ልማት እንደማዝመት ፈንታ ወደ ጦርነት ለማክተት  ቁጥር ስፍር የሌለው ወጣት ወደ  ወታደራዊ ማሰልጠኛ  ሲያስገባ ይታያል ። ይህ የህዋሓት ከክልሉ አቅም በላይ ወታደር ማሰልጠን የሁሉም የሀገራችን ክልሎች ንጉሶች በሽታ እንኳን  ቢሆንም በትግራይ ያለ የጥፋት ጦርነት ዝግጅት ግን ለየት ያለ ነው ። በመሆኑም  ይህ አደገኛ ሂደት መላው የትግራይ ህዝብ በተለይ ይህ ህዝብ ሳይማር አስተምሮ እውቀት ሸምታችሁ ሀገር ለመምራት የሚያስችል ደረጃ ያደረሳችሁ ድሀወ የትግራይ ህዝብ  ሙሁራን ተማሪዎች ይህ የህዋሓት ህገ ወጥ ቡዱን  ልጆቹና ዘርመንዘሩ ፣ከሀገራችን  ውጭ አገር አስፍሮ ላልወለደው ወጣት ወደ ጦርነት እሳት ለመማገድ ሽርጉድ እያለ ያለው ህዋሓት ለሚያደርገው ሁሉ ተቃውሞዋቹ ታሰሙ ዘንድ ጥሬን አቀርባለሁ ።
            የተከበርከው መላው የኢትዮጱያ ህዝብ ሆይ በተለይ በሀገራችን የምትገኙ በአስር ሚሊዮን የምትቆጠሩ ሙሁራን ተማሪዎች ፣ባለሀፍቶች ነጋዴዎች ፣ሰራተኞች አርሶ አደሮች  በአሁኑ ወቅት  በአዲስ አበባ የመሸገው ኢትዮጱያዊ ግብረገብነት የሌለው ጭራሹም  ለሽታም የሌለው በአብይ አህመድ የሚመራ ብልጽግና ፓርት ተብዮው የሽፍቶች ስብስብና  በመቐለ ፣በሌሎች ከተሞች የመሸገው  የተንኮል ልምድ ያለው የህዋሓት ሽፍቶች ቡዱን  እኔ ነኝ ንጉስ አይደለም እኔ ነኝ ንጉስ በማለት በመነታረክ እቺ ውብ  ሀገራችን  በተነጻጻሪ ቡሩህ ተስፋ የነበራት እነዚህ ሽፍቶች ወደ ጨለማ እያስገቡዋት ናቸው ። ጭራሹም ኢትዮጱያ የምትባል ሀገርም  እያጠፏት ነው ። ለመሆኑ እነዚህ ለጠቅማቸው ብቻ  በማሰብ አገር  ለማጥፋት እየተራራጡ ላሉ የቀን ሽፍቶች እንደ ባእድ የሩቅ ተመልከች መሆን አለብን ?  እንዴት ልጆቻ እያለን ሀገራችን ትጠፋለች አይሆንም ። መፍትሄ መድሀኒት ለማምጣት  ከቻልን መጀመሪያ ከሁለት አመት በፊት ፣ሁለተኛ ከስድስት ወር በፊት ያቀረበው ፣አሁንም በየመድረኩ ሚዲያ ባገኜው ቁጥር የሰላም ጥሪ ያቀረበ ያለው ፤ የኢትዮጱያ ዲሞክራሲያዊ  ፈደራላዊ የአንድነት መድረክ ፓርት ባዛጋጀው አገር እና ህዝብ የማዳን መፍትሄ መሰረት አድርገን አገር እናድን ፤ወይ የህዝብ  ሀሳብ በመያዝ ሁላችን ህዝቦች ከውስጣችን የእርቅ ሽማግሌዎች በመቋቋም ሀገራችን እናድን ከለበለዝያ እነዚህ ሽፍቶች ሀገራችን ለመበታተን ብሎም  ለባእድ አሳልፈው መስጠታቸው አይቀሬ ነዉ ። አንቀበልም ካሉ መፍቲሄው በቡዙሀኑ እጅ ስለሆነ እናስወግዳቸው ! ! ! ! ! ! ! !
Filed in: Amharic