>

አበበ ገላው አንተም አትቸኩል!  (ክፍል ፪ አቻምየለህ ታምሩ)

አበበ ገላው አንተም አትቸኩል!  ክፍል ፪

አቻምየለህ ታምሩ

ጋዜጠኛ አበበ ገላው የዐቢይ አሕመድን  Academic Achievement ለማጣራት ያደረገውን “ምርመራ” በሚመለከት ላነሳሁበት ትችት መልስ ሳይሰጥ የተነሳውን ዋና  ጉዳይ deflect በማድረግ ለማለፍ መርጧል። I mean either he missed the whole point or he wanted to miss the whole point.  But aversion and diversion of the issue at hand will take us nowhere!  The problem with Abebe`s approach of deflecting the issue hand, unfortunately, is not new. When one does not have a valid argument, reason to rebut and/or refute the issue at hand s/he goes to divert the issue. That is called Fallacy. And that is Logic 101.That is the ABC in Logic 101 classes. Please let us stick to the main issue here.
ሺፈራው ሽጉጤ ለፓርላማ ያቀረበው የዐቢይ አሕመድ Academic Achievement  ሺፈራው  ብቻ በፓርላማ ያቀረበው አይደለም። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን(EBC) እ.ኤ.አ. April 2, ቀን 2018 ዓ.ም. “የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሊ አጭር ግለ ታሪክ” በሚል ርዕስ በሰራው ዶክመንተሪም ደግሞታል። ምን ይሄ ብቻ! የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የዐቢይን  የሕይዎት ታሪክ  አስመልክቶ ያቀረበውን አጭር ግለ ታሪክ ባቀረበ በሳምንቱ ዐቢይ አሕመድ  በመቅቱ በቦርድ ሰብሳቢነት ይመራው የነበረው የኦሕደድ ልሳን የሆነው የኦሮሞ ብሮድካንቲግ ኔትዎርክም [OBN]  የሽፈራውን አቀረረብ ደግሞታል። ሁለቱንም ማስረጃዎች ከታች አያይዣቸዋለሁ።
አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ ራሱ በሽፈራው ሽጉጤ አማካኝነት እንዲቀርብ ያደረገውን የዐቢይን የትምህርት ማስረጃ  “ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው” እንዲሉ  ለመቀበል ያልፈለገው የዐቢይ አሕመድ የትምህርት ማስረጃ ውሸት እንዲሆን ስለማይፈልግ ይመስላል። ከዚህ ውጭ ዐቢይ አሕመድ ራሱ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ያቀረበውን  Academic Achievement  አበበ ገላው “ሽፈራው ሽጎጤ ያነበበውን እንደ መረጃ ማቅረብ ብዙም አያስኬድም” የሚል የምር ሙግት ሊከፍት የሚችልበት ምክንያቱ ሊኖር አይችልም።
ዐቢይ አሕመድ ራሱ በአንደበቱ ሩዋንዳ ለሰላም ማስከበር ሄድኩ ያለው  እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1985 ዓ.ም.  ነው።  አበበ ገላው ያናገራቸው የማይክሮ ሊንኩ ሰውዬ ደግሞ  ዐቢይ አሕመድ  በ1997 ዓ.ም.  የዲግሪ ትምህርቱን በማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ ጀምሮ በ2001 ዓ.ም. ጨረሱን፤ በመሀል ግን ለሰላም ማስከበር leave of absence ወስዶ እንደነበር ነግረውናል። በ1985 ዓ.ም. ሩዋንዳ ለሰላም ማስከበር  እንደሄደ ዐቢይ አሕመድ ራሱ የነገረንን አበበ ገላው ያቀረባቸው ምስክር ግን  ዐቢይ አሕመድ   የአንድ ሴሚስትር leave of absence ወስዶ ለሰላም ማስከበር የተሰማራው ከ1997 ዓ.ም. – 2001 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን ይነግሩናል። አልተገናኝቶም!
ምይ ይኼ ብቻ! አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ አፍሪካ በ1997 ዓ.ም. አገኘው ስለተባለው post graduate diplomaም  ምንም አላለንም። በአበበ ማስረጃ መሰረት በ1997 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪውን  ለመማር ማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ ተመዝግቦ መማር የጀመረው ዐቢይ አሕመድ በ1997 ዓ.ም. ከደቡብ አፍሪካ  በpost graduate diploma ተመርቋል።  አጃይብ ነው!
አበበ ገላው ከተሰነዘረበት ትችትና ከራሱ ጋር ተቃርኖ ውስጥ መግባቱን ለመከላከል ሲል “የአባዱላን የውሸት ዲግሪ ሳጣራ የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲን አንስቼ የአባዱላን ዲግሪዎች ሀሰት ነው አላልሁም”  ሲል ጽፏል። ይን ስህተት ነው። አበበ ገላው እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም. “Exposed: “Honorable” Speaker Abadula Gemeda has fake degrees” በሚል በጻፈው ጽሑፉ የ8ኛ ክፍል drop out ነው ያለውን አባ ዱላን  በፓርላማው ዊብ ሳይት ላይ የተለጠፉት የአባ ዱላ ዲፕሎማዎች የውሸት መሆናቸውን ሲጽ  እንዲህ ብሎ ነበር፤
“The damning evidence on Abadula’s bogus diplomas has also been discovered in the speaker’s biographies posted on the parliament’s website, his official Facebook page as well as Wikipedia. The almost identical biographies on the official pages claim: “Abadula has a rare mix of military and civilian education. His military education was obtained from the Defense University of China, a close ally of Ethiopia under the EPRDF, in Military Leadership in 1995.
“But Abadula seems to not stop there. His civilian education has taken him both ways across the Atlantic,” it claimed. “His education in the U.S. was focused on public administration. BSc in military science from the Defense University of China [nonexistent] in 1995, BA in Public administration from Century University of USA in 2001. MA in Public administration from Century University of USA in 2004 MA in International Relations from Greenwich University, UK, in 2009.” The same line of narration about the speaker with four degrees has been repeated by the state-controlled media.”
አበበ ገላው ይህንን ጽሑፍ እኔ አልጻፍሁትም ካላላ በስተቀር የ8ኛ ክፍል  drop out ነው ያለውን አባ ዱላን በሚመለከት በፓርላማው  ዊብሳት ላይ ተጸፋው የሚገኙ፤ ግን ውሸት ዲፕሎማዎች [በአበበ ቋንቋ bogus diplomas] ከተባሉት ውስጥ አባ ዱላ እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. MA in International Relations from Greenwich University ያለው ይገኝበታል። የ8ኛ ክፍል  drop out ባለው በአባ ዱላ ላይ  ይህን የጻፈው አበበ ገላው  ነው እንግዲህ ዐቢይ አሕመድ ከዚህ ተመሳሳይ ተቋም አገኘ ያለውን የማስትሬት ዲግሪ እውነተኛ ነው እያለ የሚከላከለው።
አበበ  ገላው ዳግማዊት ሞገስ የምትባል የነውረኛው ብአዴን ባለሟል ፈጸመችው ስላለው plagiarism እየነቀፈ አላጣራሁትም በማለት  እንዳላየ ሊያልፈው የፈለገው ሌላው ጉዳይ  ዐቢይ አሕመድ የፈጸመው plagiarism ነው። ዐቢይ የፈጸመውን plagiarism አበበ አላጣራሁም  የሚለው ምኑን ነው?  ዐቢይ አሕመድ plagiarize ያደረገውን ንግግር አበበ ገላው እጁ ላይ የለም?  ነው ወይስ ዐቢይ አሕመድ plagiarize ያደረጋቸው ሰዎች ጽሑፍና ቃለ ምልልስ ነው አበበ ገላው ላይ የሌለው? በእውነት ምኑን ነው አበበ ገላው አላጣራሁም የሚለው? ለመሆኑ ዐቢይ አሕመድ plagiarize  ያደረገበት ንግግርና ዐቢይ አሕመድ plagiarize  ያደረጋቸው ሰዎች ጽሑፍና ቃለ መጠይቅ ካለ አበበ ገላው ሌላ ምን ይፈልጋል?  አበበ ገላው ተስፋዬ ሀቢሶ plagiarize ያደረገውን ለማጋለጥ ተስፋዬ ሀቢሶ plagiarize  ካደረገው ጽሑፍና  plagiarize ከተደረጉት ጽሑፎች ውጭ ሌላ ምን ግብዓት ተጠቅሟል? ነው ለዐቢይ ሲሆን መስፈርቱ ተቀይሯል?
በመጨረሻ አበበ ገላው Fact Check አደረግሁ ብሎስለ ወርቅነህ ገበየሁ የጻፍሑትን በሚመለከት በሰጠው አስተያየት ላይ የኔን መልስ ስልጥና ልሰናበት።  ጽሑፉ የእርማት ስሕተት ነበረበት። በጽሑፌ ለማለት የፈለግሁት ወርቅነህ ገበየሁ IPSC ገብቶ ዶክትሬቱን አግኝቷል ለማለት አልነበረውም። ጽሑፉ “በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፊት ኢትዮጵያን ወክሎ ቀርቦ ባደረገው ንግግር እንግሊዝኛን ባፍጢሙ የደፋው uneducated and uneducable የሆነው ወርቅነህ ገበየሁ ሁሉ እንደ ዐቢይ አሕመድ አይነት የዶክትሬት ዲግሪ አግኝቷል” ነው የሚለው። አበበ ግን ይህንን የኔ ስሕተት አድርጎ ያቀረበውን ጉዳይ ሲተች  ወርቅነህ ገበየሁ ዶክትሬት ያገኘበትን University of South Africa እና ዐቢይ አሕመድ ዶክትሬቱን ያገኘበትን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን 5878 ኪሜ እንደሚርቁ ነግሮናል። ይህ የተሳሳተ ነው።
University of South Africa እነ ወርቅነህንና መሰል uneducated and uneducable  የሆኑ የወያኔ ካድሬዎችን ያሰለጠነው ደቡብ አፍሪካ ሳይሆን አዲስ አበባ ውስጥ ነው። University of South Africa የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ብሎ ማንም ሰው ጉግል ቢያደርግ ማሰልጠኛ ጣቢያው አዲስ አበባ ውስጥ  አቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ያገኘዋል። ባጭሩ አበበ ባደረገው Fact Check  እንደነገረን ወርቅነህ ዶክትሬቱን ለማግኘት  5878 ኪሜ  ተጉዞ ደቡብ አፍሪካ ድረስ አልሄደም። እና አቤ ወርቅነህ የተማረበት  “University of South Africa” የሚገኘው ከኢትዮጵያ 5878 ኪሜ  ርቀት ላይ ሳይሆን እዚያ አዲስ አበባ ውስጥ  አቃቂ ቃሊቲ ነው። እና አበበ  አንተም አትቸኩል 🙂 ወርቅነህ እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ወያኔ ባስቀመጠበት ቦታ ላይ የሙሉ ጊዜ ሰራተኛ ሆኖ ነው ይኸውህ “ዶክትሬቱ”ን ቀምጭሎ እንግሊዝኛን እንዲያ ባፍጢሙ ሲደፋው ያየኸው 🙂
Filed in: Amharic