>
5:16 pm - Tuesday May 24, 2033

ኦሮ አማራ:- ኦነጋዉያኑ እነ አቢይ የራሳቸዉን ብአዴኖች (አቤት ወዴት ባዮች) እያዘጋጁ ነዉ...!!! (ሸንቁጥ አየለ)

ኦሮ አማራ:- ኦነጋዉያኑ እነ አቢይ የራሳቸዉን ብአዴኖች (አቤት ወዴት ባዮች) እያዘጋጁ ነዉ…!!!

ሸንቁጥ አየለ

ከኦነጋዉያን 25 አመራሮች ለኦነጋዉያን ገባሪ ከሆኑ አማሮች 20 አመራሮች ተዉጣጥተዉ የኦሮ-አማራ አመራሮች የሚል ታፔላ ተለጥፎላቸዉ ደብረዘይት እየሰለጠኑ ነዉ የሚል ወሬ ደረሰኝ። እኔም ለምን የሚል ጥያቄ አስከተልኩ። ምላሹም አስደንጋጭ ነበር።ኦነጋዉያኑ እነ አቢይ የራሳቸዉን ብአዴኖች እያዘጋጁ ነዉ የሚል ሆኖ አገኘሁት።
 በቀጣይ ኦሮ አማራ ታደሰ የሚል ዘፈን ይለቀቅልሃል።አንተም አብረህ ትዘፍን ይሆናል። ወይም ጎበዝ ልብ ካለህ ጥያቄ ትጥይቃለህ። ጥያቄህም ኦሮሚያ በሚባለዉ የትግሬ ክፉ ወያኔ አማራን ለመጉዳት ብሎ የፈጠረዉ የተረት ተረት ክልል ዉስጥ የሚኖረዉ 20 ሚሊዮን አማራ ላይ የሚፈጸመዉን አፈና፡ ማፈናቀል፡ ወከባ እና የዘር ፍጅት ባልሰማሁም ባላዬሁም ላሽ የሚል የአማራ ፖለቲከኛ ኦሮ አማራ ብሎ ቢከሰት ወይም የአማራ ብሄረተኛ ብሎ ቢከሰት ወይም ኢትዮጵያዊ ብሄረተኛ ብሎ ቢያገሳ ለአማራ ህዝብ ምኑ ነዉ?
 ለማንኛዉም ህዝብ ጆረህን ከፍተህ ተከታተል።  የኦነጉ አቢይ አህመድ ፈረስ የሆነ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ወይም አማራ ድርጅት ወይም ምንም አይነት ስም የያዘ ድርጅት ሁሉ ጠላትህ እንደሆነ እወቅ።
ለማንኛዉም በዘፈን ታጅበዉ የሚከሰቱ የኦሮ አማራ አመራሮች የመጀመሪያ መግለጫ የሚሆነዉ ኦሮሚያ ዉስጥ አንድም አማራ አልተገደለም፡ ቤኒሻንጉል ዉስጥ አንድም አማራ አልተገደለም።
ይሄ ሁሉ የጠላት ፕሮፖጋንዳ ነዉ የሚል እንደሚሆን ይጠበቃል።
Filed in: Amharic