>
5:18 pm - Tuesday June 15, 2427

መሞቴን ለመናገር ከገዳይ አስገዳዮች ፈቃድ አልጠብቅም ! (ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ)

መሞቴን ለመናገር ከገዳይ አስገዳዮች ፈቃድ አልጠብቅም !

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

1) ሞት ቢደገስ እንኳ አንቀርም፣ የአማራ ልጅ አምባገነኖችን በታሪኩ ፈርቶ አያውቅም፣ ዛሬም በፍፁም አይፈራም!
2) የአባይ ግድብ ለአማራ የመቃብር ስፍራ ማድመቂያ እንዲሆን አስባችሁ እየገነባችሁት ከሆነ ጥሩ ነው። የአባይ ጉዳይ ከወገኖቻችን በህይዎት መኖር በታች ያለ አጀንዳችን እንጂ ከአማራ ነፍስ የሚቀድም ጉዳያችን አይደለም።
ለናንተ ለተላላኪዎች ከአማራ ህይዎት በላይ ያለ ቀዳሚ አጀንዳችሁ መሆኑን ግን አሳይታችሁናልና እናመሰግናለን!
3) ሰላማዊ ሰልፉ የክልሉን አለመረጋጋት ለሚፈልጉ ሀይሎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ለተባለው ጉዳይ፣ አንዱ ስራችሁና ግዴታችሁ ህዝቡን ከፀረ ሰላም
ሀይሎች መጠበቅ እንደሆነ መገንዘብ አለባችሁ። በክብር ስትጠየቁ ፈቅዳችሁ፣ አስፈላጊውንና የሚገባውን ጥበቃ ብታደርጉ እናንተም ቢያንስ ከ2008ቱ አጥፊ ስህተታችሁ መማራችሁን ታሳዩ ነበር። የአማራ ወጣት እናንተ ከልክላችሁት
ሰልፍ ከቀረ ገዳዮችን አበጃችሁ ብሎ እንደሸለመ እንቆጥረዋለን።
4) በ2008 አንገራግራችሁንም ሆነ ገድላችሁን ፈርተን እንዳልተመለስን አስታውሱ። በወቅቱ አማራው ሆ ብሎ ወጥቶ «ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ»፣ «ኮሎኔል ደመቀ የነፃነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይፈለም»፣ «በኦሮሞ ክልል የሚፈሰው የወገናችን ደም የኛም ደም ነው» ብለን የአማራን ጥያቄ ስናስተጋባ እናንተ ተላላኪዎች መለስን ስታመልኩና፣ “ታግሎ ነፃ ላወጣን ትህነግ
እንኳን ወልቃይትን ጎጃምን ብንሰጠው ምን ችግር አለ” ስትሉ ነበር።
ዛሬ የአማራ ደም በየቦታው እንደጎርፍ እየወረደ ከ2008ቱ ጭፍጨፋችሁ በፈጣሪ ተዓምር የተረፍን አማሮች የሀምሌና የነሀሴ 2008 ሰማዕታት
ወንድሞቻችን የወደቁለትን ዓላማ ይዘን ለአማራ ህዝብ ጥያቄዎች መመለስ የምንችለውን ካላደረግንና፣ በየቦታው የሚፈሰው የአማራ ደም ባስቸኳይ ይቁም ብለን ካልወጣን ከሞቱት በታች ሆነናል ማለት ነው።
5) በሌላችሁ ስልጣን ሰላማዊ ሰልፍ መከልከል ውስጥ ከገባችሁ ከህዝብና ከአምባገነኖች የማንኛው የበላይ እንደሆነ፤ ከህዝብና ከተላላኪዎችም ማን ፈሪ እንደሆነም እናያለን።
6) ጥበቃ እንድታደርጉለት ጥያቄ ባቀረብንባቸው በነዚህ ሰልፎች ላይ አንድ አማራ አንድ ነገር ቢሆን ትግላችን ወደምን እንደሚያመራ እናንተም
አይጠፋችሁም!
አማራ በልጆቹ ትግል ይከበራል!
Filed in: Amharic