>

የአማርኛ ቋንቋ እና አክራሪ ብሄርተኞች (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

Dr. Bekalu Atnafu

የአማርኛ ቋንቋ እና አክራሪ ብሄርተኞች

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ


ከ 1960 በፊት በነበረው እሳቤ የአገር ግንባታ ወይም ምስረታ ታሪክ  ከአንድ ቋንቋ ጋር የተሳሰረ  ስለነበር   አገርን ለመገንባት፣ መንግስታት የአንድ  ቋንቋ ፖሊሲ ይከተሉ ነበር፡፡ በርካታ ቋንቋዎች በሚነገሩበት ማህበረሰብ ውስጥ ከበርካታ ቋንቋዎች መካከል አንድ ቋንቋ ለመደበኛ ቋንቋነት(Official Language) የሚመረጥበት ዋናው ምክንያት የህዝቡን እና የአገርን አንድነት ከመጠበቅ እንፃር  እንደሆን በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች ያሰረዳሉ(Archibugi,2005) ፡፡ ይህም ክስተት በርካታ የቋንቋ ብዝሀነትን በያዘችው አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአውሮፓ አገሮችም የነበረ እውነታ ነው( Michael, 2007; Jong, 2011)፡፡ ቋንቋ የማህበረሰቡ የአንድነት መገለጫ(unifying agent) ተደርጎ  ሰለተወሰደ የአገር ውህድት ወይም አንድነት የሚመጣው ማህበረሰቡ አንድን  ቋንቋ ሲጠቀም ነው  የሚል እሳቤ ስለነበር (Spolsky & Shohamy, 2000) አብዛኛዎች የዓለም ሀገራት አንድን  ቋንቋ እንደ መደበኛ(national official language ) የመግባቢያ መሳሪያ አድርገው ይጠቀሙ ነበር፡፡

ከ20ው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የቋንቋ ብዝሀነት በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እያገኘ በመምጣቱ(Garcia, 2007፤Fishman, 1981) በተለያዩ አህጉራት እና በበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የቋንቋ ብዝሀነት የትኩረት አቅጣጫ ሊስብ ችሏል፡፡ በመሆኑም የደርግ መንግስት ሊጠፉ የሚችሉ ባህሎችን፣ማንነቶችን እና ቋንቋዎችን ግምት ውስጥ በመስገባት እና እነዚህ ማህበራዊ እሴቶች ይጠበቁ ዘንድ የኢትዬጲያ ብሄረሰቦች ጥናት ኢንስቲትዩትን አቋቁሞ ነበር፡፡ በመቀጠልም የኢህአዲግ መንግስት የቋንቋ ብዝሀነትን ሊያስጠብቅ ችሏል፡፡

የአማርኛ ቋንቋ የበላይነት ከአማራ ህዝብ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ ፣ እና የማህበራዊ የበላይነት ጋር እንደማይዛመድ እየታወቀ የተሸናፊነት እና የበታችነት ስነ-ልቦና(victim mentality and low self-esteem) የተጠናወታቸው ጥቂት የህወሓት ሊህቃን በሚተርኩት የሀሰት ትርክት እና የእነሱን ትርክት በሚያራግቡት አክራሪ ኦነጋውያን የአማራ ህዝብ  የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የማህበራዊ የበላይነት እንዳለው በማሰብ  በማንነቱ ላይ የጥቃት ዘመቻዎች ሲሰነዘሩበት ቆጥቷል፡፡ 

በሰላሳ ዓመታት ከተፈፀሙት ግፎች መካከል በአርባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ በአርሲ፣በባሌ ፣በጋምቤላ፣በሀረር፣ኢሊባቡርና፣ጅማ፣ወለጋ፣ በቤንች ማጅ ዞን በጉራፋርዳ ወረዳ ከፍተኛ ጭካኔ በአማራ ገበሬዎች፣ሴቶች፣ነፍሰጡር ሴቶች፣ ህፃናትና ሽማሌዎች ላይ ጭፍጨፋ፣ማፈናቀል እና ዘር ማፅዳት ተፈፅሟል፡፡ እንዲሁም በአለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በቤኒሻንጉል፣ በኦሮሚያ ክልልዊ መንግስት፣በጉራ ፈርዳ የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት ዘመቻ የተከፈተበት ሲሆን የተፈፀሙት ግፎች በበርካታ ምስሎቹና እውነታዎች ለታሪክነት በማስረጃ ተመዝግበዋል።

ዛሬ ግን በቃ ሊባል ይገባል፡፡ ስለዚህ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚቆረቆር ማንኛውም ኢትዮጲያዊ እና የአማራ ወጣት በሰላማዊ መንገድ ትግልን ከሚያራምዱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጎን በመቆም የግፍ ስርዓትን ልንገረስሰው ይገባል፡፡

References

Archibugi, Daniele (2005). The Language of Democracy: Vernacular or Esperanto? A Comparison between the Multi-culturalist and Cosmopolitan Perspectives. Italian National Research Council: Political Studies, 53, 537–555.

Fishman, Joshua A. (1981). Language and Ethnicity in Minority Sociolinguistic Perspective. Philadelphia publisher: Multilingual Matters.

 

Garcia, Ofelia (2007). “Bilingual Education.”.Coulmas, Florian (ed). The Handbook of Sociolinguistics. Blackwell Publishing, Retrieved in 28 December 2007 <http://www.blackwellreference.com/subscriber/tocnode? 

Jong, Ester J. de (2011).Foundations for Multilingualism in Education from Principles to Practice.University of Florida, Gainesville:Caslon Publishing. 

Michae,lClyne (2007). Multilingualism. Coulmas Florian (ed.) The Handbook of Sociolinguistics Blackwell Publishing Reference Online, Retrieved from: <http://www.blackwellreference.com/subscriber/tocnode? 

Spolsky Bernard and ElanaShohamy (2000) Language Practice, Language Ideology, and Language Policy: In Richard D. Lambert Nflc, and Elana Shohamy (eds.) Language Policy and Pedagogy. Amsterdam.  John Benjamins Publishing. pp 1-42

Filed in: Amharic