የመቀሌ ሁለት ቡድን!
አርአያ ተስፋ ማርያም
በመቀሌ ሁለት የህወሀት ቡድን እንዳለ ማረጋገጥ ተችሏል። በመስከረም “አደረኩት” ካለው የጨረባ ቅርጫ – ምርጫ በኋላ እነደብረፂዬን ከሚመሩት ህወሀት ሌላ ስብሃት የሚመራው እና “ዋና የበላይ ህወሀት” የሚል ስያሜ የተሰጠው ቡድን ይፋ ባልሆነ መንገድ ሲቋቋም፣ ሊቀመንበር ስዩም መስፍን፣ ምክትል አባይ ፀሀዬ፣ ፀሃፊ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ (ሚስቱ ቅዱሳን ነጋ የስብሃት እህት) ውሳኔ ሰጪ አባላት ስብሃት ነጋ፣ ኮ/ል አወል አብዱራህማን፣ ጌታቸው አሰፋ እንደሆኑ ከቅርብ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። “የበላይ ዋና” የተባለውና አብዛኛው አባል ሳያውቀው በነ ስብሃት የተዋቀረው ይህ ቡድን በአገሪቱ የሚፈፀሙ እልቂቶችን በመምራት፣ ጦርነት በማወጅ ወዘተ ከጀርባ የሴራው መሪና ቀያሽ ነው! የዚህ ቡድን አባል የሆነው ኮ/ል አወል ማንነት መጋለጥ አለበት! ብዙዎች ደደቢት ክለብ ፕ/ት ሆኖ ያውቁታል! ግን ከጀርባ በሙስና ሲበልፅግ የነበረ የነ ስብሃት መሰሪ አላማ አስፈፃሚ ነው!
ኮ/ል አወል በገርጂና ቦሌ እጅግ ዘመናዊ ሁለት ቪላዎች አሉት። በእሱ ስም የተገነባው 90 ሺህ ሲከራይ፣ በልጁ ሬድዋን አወል ስም የተገነባው ቪላ በወር 4 ሺህ ዶላር ይከራያል። የኮ/ል አወል ልጅ ሬድዋን በሽሬ ትልቅ ፋብሪካ አለው። “ሻንሃይ” (ሻንጋይ ለማለት ነው) የማዳበሪያ ፋብሪካ በመቶ ሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ የተገነባ ነው። ሬድዋን አንድም ስራ ሰርቶ አያውቅም። ትምህርት ጨርሶ ሚሊየነር የሆነ ነው። ኮ/ል አወል ከዝች አገር በዘረፈው ሀብት ሁለት ቪላ ገንብተው እያከራዩ፣ ኪራዩንም በወኪል እየወሰዱ ባንፃሩ በዚች አገር ላይ የጥፋት አዋጅ አውጀዋል! ኮ/ል አወል ልጆቻቸውን በዘረፋት ገንዘብ ሚሊየነር ካደረጉት አንዱ ሲሆኑ የትግራይ ድሃ ልጅ ለማስጨረስ ከነስብሃት ጋር ከፊት መስመር ተሰልፏል!