>

ለኢትዮጲያ የተዋደቁ አፍረው አያውቁም !! (ታምራት ነገራ)

ለኢትዮጲያ የተዋደቁ አፍረው አያውቁም !!

ታምራት ነገራ

የአገር ዳር ድንበር ለማስከበር ዘብ በቆማችሁበት፣ ከጠላት ጋር በገጠማችሁት  የሞት ሽረት ፍልሚ መካድን ቀኖናው ባደረገው ወያኔ ከጀርባችሁ አዲስ ግንባር ተከፈተባችሁ። የፊተኛው ውጊያ ሳያንሳችሁ በኋለኛው ግንባር ክህደት በየበረሃው ለተዋደቃችሁ፣ ለ27 ዓመታት በወያኔያውያንና አበሮቹ ኦነጋውያን የማያባራ የፕሮፖጋንዳም የመዋቅርም ዘመቻ ለወረደባችሁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አባቴ ነገራ ፈይሳን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት ከጀርባችሁ የክህደት ግንባር የከፈተባችሁ ወያኔ ከጀርባው ተከድቶ  ይሄው ዛሬ የማይወጣው ማጥ ውስጥ ወድቋል።
  ኢትዮጵያም መዋቅሮቿም  የእናንተን ስም ከማንቋሸሽ፣ መስዋዕትነታችሁን ከማጣጣል ፣ ስማችሁን ወደማክበር ፣ ትውስታችሁን ወደማወደስ ቀና ቀና ማለት ጀምራለች። የወያኔንና መሰሎቹን አገር ከሃዲዎች ቀብር በቶሎ እንደሚጠናቀቅ የእናንተም የእናት አገር ዳርድንበር የማስከበር ዓላማ በእኛው ትውልድ እውን እንደሚሆን እናምናለን።
ለኢትዮጵያ የወደቁ አፍረው አያውቁም!!!! 
#Ethiopia
#EthiopiaForever
#DismantleEthnicFederalism 
#ለሀገር ለመከላከያ ክብር እቆማለሁ!
Filed in: Amharic