>

አማራን ለማጥቃት ተብሎ የሚሰራ ሴራ ዉሎ አድሮ ሁሉንም ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም!!! (ሚኪ አምሀራ)

አማራን ለማጥቃት ተብሎ የሚሰራ ሴራ ዉሎ አድሮ ሁሉንም ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም!!!

ሚኪ አምሀራ

…ትህነግ የጦርነት ዝግጅት ሲያደርግ “አማራን ነዉ የሚ,ወጋው” ተብሎ እጅ አጣጥፎ የተቀመጠ መንግስት ለሀገሪቱ ትልቁ የመከላከያ እዝ (የሰሜን እዝ በአስር ሽህ የሚቆጠሩ የሰለጠኑ  ወታደሮችን በግድያና በተለያየ መንገድ ማጣት፣ ለቁጥር አዳጋች የሆነ መሳሪያ መዝረፍ ብሎም የተቋም መፍረስ አደጋ ተደቅኖበታል!
 
ይሄ መንግስት ተብየ የማይገባዉ ነገር አለ፡፡ መተከል ላይ አማራ ሲጨፈጨፍ እያድበሰበሰ ባለፈ ቁጥር አካባቢዉ ከቁጥጥሩ ዉጭ እየሆነ መሄዱን አያዉቀዉም፡፡ መቼም ለሰዉ ነብስ ደንታ እንደሌላቸዉ እናዉቃለን፡፡ ቢያንስ ግን ነጋ ጠባ ድርድር ምናምን እያሉ የሚያላዝኑበት የሀገሪቱ ስትራቴጅክ ንብረት በዚህ ዞን ዉስጥ ነዉ ያለዉ፡፡ ይሄን ያህል ሃብት የፈሰሰበት ፕሮጀክት ያለበትን ዞን የሰዉ ነብስ አይደለም የአዉሬ ነብስ እንኳን እንዳያልፍ አድርጎ መቆጣጠር እንዴት ያቅታል፡፡ አካባቢዉን መቆጣጠር አለመቻል ለዉጭ ሃይሎች የሚያስተላልፈዉ የድክመት መልክት ዘግይቶም ቢሆን ዋጋ እንደሚያስከፍለዉ የሚያዉቁ አይመስለኝም፡፡
እያንዳንዷ አማራን ለማስከፋት ተብሎ የሚሰራ ነገር ዉሎ አድሮ ሁሉንም ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም፡፡ ክንዳችንም መቅመሱ አይቀሬ ነዉ፡፡ ትህነግ የጦርነት ዝግጅት ሲያደርግ አማራን ነዉ የሚዎጋ ተብሎ እጅ አጣጥፎ የተቀመጠ መንግስት ለሀገሪቱ ትልቁ የመከላከያ እዝ (በአስር ሽሖች ወታደር እና ለቁጥር አዳጋች የሆነ መሳሪያ) መፍረስ እና አሁን ላይ ብቻ አይደለም ለረዥም ጊዜ ሀገሪቱን ዋጋ የሚያስከፍል ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የሚገርሙኝ ደግሞ ባህርዳር ላይ ያሉት ገልቱዎች ናቸዉ፡፡ አልተፈቀደልንም አላስፈቀድንም ይላል፡፡ ያለዉ መፍትሄ ማስፈቀድ ብቻ የሚመስላቸዉ ከንቱዎች ናቸዉ፡፡
አንዳንድ የቤንሻንጉል አመራሮች ናቸዉ እየተባለም ምክንያት ይሰጣል፡፡ የአማራ ክልል ፕሬዝደንት የነበረ ነዉ እኮ የደህንነቱ መስረያ ቤት ሃላፊ፡፡ እኒህ የሚባሉትን ሰዎች በደህንነቱ በኩል አንቆ ካላመጣ እዛ ምን ይሰራል፡፡
Filed in: Amharic