>

አፋጀሽኝ፤ በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ (ጦቢያን በታሪክ)

አፋጀሽኝ፤ በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ

ጦቢያን በታሪክ

(ቴሌግራም)

ይቺ ድራማ ጣልያን ሊወር ሲር የተጻፈች ሕዝብን መቀስቀሻ ነበረች። አፋጀሽኝ የተሰኘችው ኢትዮጵያ ናት፡ ይህንን ስም ለምን እንደመረጡ ሲገልጹ ባይታይም መግቢያው ላይ እንዲህ ይላል:-

«አንባቢ ሆይ ይህቺን የጨዋታ መጽሐፍ ከነጊዜዋ ለጨዋታ ብቻ ሳይሆን፤ ለቁም ነገርም ወስነናታል፤ ግን በማንበብ ብቻ ሳይሆን በሥራዋ ብትመለከታት የራስህ ሥራው ምን እንደሆነ በራስህ መርምረህ ትደርስበታለህና ተመልከት ተመላልሰህም እንብብ። የአለፈውን አስገንዝብ ለሚመጣው የተሻሻለ ምክር እየሰጠች ታስጠነቅቃለች ። ለማንም ሰው ቢሆን የምትሰጠው ዋና ምክሯ ኢየሩሳለም ሰማያዊ፤ ጻድቃንን እያናደደች ወደ ገዳም፤ ሰማዕታትን እያናደደች ወደ ደም እንደምትጠራቸው፤ በዛሬው ጊዜም እሷ ወንዶችን እያናደደች ከመለያየት ወደ አንድነት ተራ፤ ሴቶችን እያናደደች ወደ ቀኝ ከወደ ግራ፤ እየመለሰች ታቃናቸዋለች ።»

ጨዋታው መካከል ላይ ሦስት የፋሺስት ጣልያን ተወካዮች አፋጀሽኝን ሊያነጋግሩ ይቀርቡና ውል ያቀርቡላታል። (ፎቶ ላይ አለ)። በደፈናው የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አቅም በመጥቀስ እናግዝሽ እናልማሽ፤ የምትኖሪበት ቤት የከብቶች ነው፣ መሬትሽ ለም ነው፣ እህል እንደልብ ይበቅላል፣ ጤናሽ የታወከውን እናክምልሻለን፣ መንገድ እንሰራልሻለን፣ ብቻ እሺ በይን እና ከዛ የኛን ጥቅም ደግሞ እንነግርሻለን ይላሉ።

ከዛ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተገናኝተው ይወያያሉ። እልጣማቸውም። አንዳንዶቹ «ሊረዱን ቢመስሉም አቅማቸውን እና ጉልበታቸውን ነው እያሳዩን ያሉት ይቅርብን» ይላሉ።

እኔን የመሰጠኝ ይህ ምላሽ ነው።

በአንድ የሃይማኖት አባት የተመሰሉ ገጸ ባሕርይ ናቸው የተናገሩት፡ «ገበሬም አርሶ ቄስም ቀድሶ ወታደርም ዘምቶ እንደ አባቶቻችን እንኖራለን እነሱም እዚአው ሐገራቸው ይበቃቸዋል ሐገራቸው ሰፊ ነው።»

በአጭሩ የማን ተቆርቋሪ ነኝ ነው? ነው ነገሩ። ፡)

ከዚህ በኋላ ሽለላ፣ ሙዚቃ፣ ለጦርነት መቀስቀሻ የዘመቻ ግጥም ነው የሚከተለው። አንዳንዱን ከሥር አያይዤያለሁ።

እቺም መዝሙር አብራ አለች፡

«ድንግል አገሬ ሆይ ጥንተ ተደንግሎ 

ሕፃናቱ ታርደው ያንቺም ልብ ቆስሎ

ልጅሽ ተሰደደ አንቺን ተከትሎ

የሕፃናቱን ደም አዘክሪ ኩሎ

አስጨነቀኝ ስደትሽ

እመቤቴ ተመለሺ።…»

ከጥንታዊ አማርኛ ትርኢቶች /ቴያትር/ ቁጥር 1 – የኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 1958 ዓ.ም. የተዘጋጀ፡፡

Filed in: Amharic