የሁለት ኦሮሞዎች ወግ…!!!
አቤል ዋበላ
በዛሬው ዕለት ሽመልስ አብዲሳ በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንፃን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል። በጀቱም 1.8 ቢሊዮን እንደሆነ ተገልጿል። መዐዛ አሸናፊ እና ሌሎች ሰው መሳይ በሸንጎዎች አጅበውታል። ወሬው በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ጋር ደርሷል።
ሌላው ኦሮሞ ታምራት ነገራ አንደነገሩ ካበጃት Terara Network ከተሰኘው ስቱዲዮ ሆኖ ኦሮሚያ የሚባል ክልል ይፍረስ ብሎ ይናገራል።
ልዩነቱ mind blowing የሚያስብል ነው። ተቃርኖው በግልጽ ይታያል። በእርግጠኝነት ከሁለቱ አንዱ ተሳስተዋል ወይም አንዳቸው ለኦሮሞ ህዝብ የሚበጀውን ነገር እያደረጉ አይደለም ማለት ይቻላል።
በባለጊዜነት ካየነው ሽመልስ እንደፈጣሪ ነው። የፓለቲካ ስልጣንን ተጠቅሞ ያሻውን ያደርጋል። ተራራ ይከምራል ተራራ ይንዳል። አበጀህ የሚለው ብዙ ነው አድርባዩ እልፍ ነው። ሌላው ይቅርና በዜጎች ስም የሚነግደውም ከታምራት ይልቅ ሽመልስን የሚያስቀድም የዘውጌ ካዳሚ ነው።
ታምራት ግን እውነትን ይዟል። ለኦሮሞ ወገኖቹ ወገኖቻችን ከልብ መቆርቆሩን በነጠረ ሀሳቦቹ አሳይቷል። ሽመልስ በአደባባይ የሚሸጠው ሀሳብ ሳይሆን ጥላቻ ነው። ሽመልስ በአካዳሚ የቀሰመው እውቀት የህይወት ልምዱ ከትንሽነት አያድነውም። እሱን ከፍ ያደረገው ስርዓት በወያኔ የተገነባ ውንብድና ነው። ከዚህ ውንብድና ወጥቶ ወደራሱ ወደሰውነት ለማደግ መንገድ እንዳልጀመረ ደጋግሞ አስመስክሯል። ታምራት እውነቱን ይዞ በስደት/በግዞት ቆይቶ ከእውነቱ ጋር ተጣብቆ ይኖራል። ሀሳቡ ተራራ ነው። ልባም ብቻ የሚወጣው።