>

ጽንፍ የረገጠ ነውጠኝነትና ሰብዓዊ ደህንነት በአፍሪካ ( ደረጀ መላኩ - የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

ጽንፍ የረገጠ ነውጠኝነትና ሰብዓዊ ደህንነት በአፍሪካ

ደረጀ መላኩ ( የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

Tilahungesses@gmail.com


ክፍል ሶስት

ሶማሊያ፣ኬኒያ፣ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2016 ራሳቸውን ‹‹ የምስራቅ አፍሪካ ጃብሃ ›› በማለት የሚጠሩ ( ወይም በእንግሊዝኛ ስማቸው ( ISSKTU), or Jabha East Africa )  ለአል ባግዳዲ  (al-Baghdadi ) ታማኝነታቸውን አሳይተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በኬኒያ፣ታንዛኒያና ኡጋንዳ የሚገኙት ጽንፈኛ ቡድኖች ራሳቸውን ከአልሻባብ በመለየት ሌላ የጽንፈኛ ቡድን እንደመሰረቱ የአፍሪካው ቀንድ የፖለቲካ ጠበብቶች ከአሰናዷቸው ጥናታዊ ጽፎች መረዳት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ ቡድን መስራች ኬኒያዊው የህክምና ተማሪ የነበረው ሞሀመድ አብዲ አሊ ነበር፡፡ ይህ ግለሰብ በኬኒያ ናይሮቢ በሚገኝ ትልቅ የገበያ አዳራሽ (Westgate Mall ) እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2013 ለደረሰው የሽብር ጥቃት በአቀናባሪነት ተጠርጥሮ ስለመታሰሩ በወቅቱ የአለም የመገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ቡድን እምብዛም የማይታወቅ ቢሆንም ለተጠቀሱት ሀገራት ግን የጸጥታ ስጋት መሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለውም፡፡ በሶማሊያ የሚንቀሰቃሰው አልሸባብ ግን ዛሬም ድረስ ለሶማሊያ ሞቃዲሾ መንግስት የጎን ውጋት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ በአራቱም ሀገራት የጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች በመኖራቸው በአካባቢው የህዝብ ደህንነት ስጋት ላይ ወድቋል ተብሎ ቢጻፍ ስህተት አይመስለኝም፡፡

አል- ሸባብ ( Al-Shabaab )

ይህ የሙስሊም ነውጠኞች ቡድን የጥቃት አድማሱን ከሶማሊያ ግዛት ውጪ ለማስፋት አቅም እንዳለው የሚነገር ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የአሸባሪ ድርጅት ነው፡፡ ከዚህ ባሻግር የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን የቀጠፈ ድርጅት ነው፡፡ ለአብነት ያህል እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 2017 በሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ ህዝብ በተሰበበበት ቦታ ላይ በጭነት መኪና የተጫነ ፈንጂ በመፈንዳት ከ500 በላይ ንጹሃን ዜጎችን እንደፈጀ በአለም የመገናኛ ብዙሃን ተዘግቧል፡፡ እንዲህ አይነት የሽብር ጥቃት ሲፈጸም፣ በአንድ ቀን ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ንጹሃን ዜጎች( ሰዎች) ሲፈጁ ከመስከረም 11ዱ 2011 የኒውዮርኩ ጥቃት በኋላ የመጀመሪየው ነበር፡፡  ይሄው ነውጠኛ ቡድን በቅርብ ግዜ ውስጥ ደግሞ ኬኒያ ናይሮቢ በሚገኝ እና የምእራብ ሀገራት ዜጎች አዘውትረው በሚጎበኙት ዘመናዊ ሆቴል በፈጸመው የሽብር ጥቃት ከሃያ (20) በላይ ንጹሃን ዜጎች ህይወት እንደተቀጠፈ የሚታወስ አሳዛኝ ዜና ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ወይም እንደ ነጻ ህሊናና መንፈስ እንዳላቸው የምርመራ ጋዜጠኞች ጥልቅ ዘገባዎች ከሆነ በተስፋ መቁረጥና ችጋር ምክንያት የተነሳ በርካታ የኬኒያ ዜጎች ድንበር እያቋረጡ ከአልሻባብ አሸባሪ ቡድን ጋር ይቀላቀላሉ፡፡

ባለፉት አስር አመታት አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ስዋሃሊ ዳርቻ የሚገኙ ፣ የተገለሉና፣ ከእስልምና ሃይማኖት ታሪክ እና ባህል ጋር ግንኙነት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ዘዴዎች፣ በተለይም በጥንት ዘመን የነበሩ ግንኙነቶችን  በማሳለጥ ወይም በመቅረብ መርዙን ሲረጭ እንደነበር የሚሳዩ ጥናቶች አሉ፡፡

መሰረቱን በኬኒያ የወደብ ከተማ ሞምባሳ ባደረገው ‹‹ የሙስሊም ሰብዓዊ መብቶች ›› አስከባሪ አቀንቃኝ የሆኑት ሀሊፋ፣ሀሊፋ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ መሰረት በኬኒያ የኢኮኖሚ ድቀት በፈጠረው የስራ እጥ ቁጥር መጨመር ወጣቶች ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል፡፡ የወደፊቱ ህይወታቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ የተቸገሩት ተስፋ የቆረጡ ወጣቶች ደግሞ የአልሻባብ ተዋጊ ሚሊሻ አባል ለመሆን ይመዘገባሉ ብለዋል፡፡

Khelef Khalifa, a veteran human rights campaigner and  Chairman of Mombasa-based Muslims for Human rights (MUHURI) told TRT  World that Kenya’s raging financial turmoil and erratic economy is “causing  unemployment and pushing desperate youth to join militant group Al Shabab

ከዚህ በተጨማሪ በኬኒያ ምድር ስር የሰደደው ሙስና፣ የፍትህ እጦት፣ የተፈጥሮ ሀብት በጥቂቶች መመዝበር ወዘተ ወዘተ ወጣቶች ለአልሻባብ ስብከት ልባቸው እንዲሸፍት የሚያደርጉ ተጨማሪ ነዳጆች ናቸው፡፡ የአልሻባብ አመራሮች በበኩላቸው ወደ ጽንፈኛው ቡድን አባል ለመሆን ለሚመጡ ወጣቶች ከፍተኛ ደሞዝ እንደሚከፍሉ በየጊዜው ይሰብካሉ፡፡ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኙ እንደሚሉት ከሆነ አልሻባብ ኢላማ የሚድረገው ከኬንያ አጠቃላይ ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስራ ፈት ወጣቶችን ነው፡፡ 

በነገራችን ላይ በኬንያ ምድር በየጊዜው ለሚከሰቱ ወይም ለሚፈጸሙ የሽር ጥቃቶች የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው አልሻባብ እንደሆነ ሀሊፋ ይናገራሉ፡፡ ሀለሊፋ የአለም አቀፍ ድርጅቶችን የጥናት ውጤት ጠቅስው እንደሚናገሩት ከሆነ ከኬንያ አጠቃላይ የወጣቶች ቁጥር ውስጥ 22 ፐርሰንት የሚሞሉት ሥራእጥ ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለሆነም የአልሻባብ የጥቃት ሰበዝ የሚመዘዘው የሥራ እጥ ወጣቶች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ በሚገኝባቸው ሀገራት ነው፡፡  ለምንድን ነው አልሸባብ በስራ እጥ ወጣቶች ላይ ትኩረቱን ያሳረፈው ? አረ ለመሆኑ ከሀገራችን አጠቃላይ የወጣቶች ቁጥር ውስጥ ምን ያህሉ ናቸው ? ሥራ አጥተው በኢትዮጵያ አውራ ጎዳናዎችና ገጠሮች የሚንከራተቱት እስቲ የምታውቁ አስረዱን፡፡

ኢትዮጵያ

በሶማሊያ የአክራሪው ጽንፈኛ ቡድን ከወራቶች በፊት ባሰራጨው የሶስት ደቂቃ መልእክት መሰረት ከሆነ የጽንፈኛ አስተምህሮ በአማርኛ ቋንቋ የተጻፉ የጽንፈኛ አስተምህሮ ለማሰራጨት እቅድ እንደተያዘ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ተሰምቷል፡፡

በነገራችን ላይ ከአፍሪካ ሀገራት ሁሉ ከናይጄሪያ በመለጠቅ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባላት ኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ተገን አድርገው የአክራሪ ሙስሊም ጽንፈኞች መርዛቸውን አይረጩም ብሎ ማሰብ ተላላነት ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ ጊዜያት ከመገናኛ ብዙሃን ከሚተላለፉ ዜናዎች እንደሚሰማው ከሆነ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም ሲዘጋጁ በጸጥታ ሀይሎች እጃቸው ተያዘ የሚሉ ዜናዎች መስማት ብርቅ አይደሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የታዋቂውን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጽንፈኛ አስተሳሰብ ባበዱ ጨካኞች መገደላቸው የቅርብ ግዜ መሪር ትዝታ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በይፋ የሚንቀሳቀስና የሚታወቅ አክራሪ የሙስሊም ጽንፈኛ  ቡድን ባይኖርም ፣በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች ( በተለይም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች) በግፍ እንደሚገደሉ ከመገናኛ ብዙሃን መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ የሙስሊም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችንን የጥቃት ኢላማ የሚያደርጉ እኩያንም አይጠፉም፡፡ አንደ ዶክተር ሻለቃ ዘውዴ ጥናት ውጤት ከሆነ ባለፉት ሰላሳ አመታት በኢትዮጵያ የውሃቢዝምን አስተምሮ ለማድረጽ በተለይም በሰኡዲአረቢያ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ በነገራችን ላይ የክርስትና ሆነ የእስልምና እምነት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከረጅም ዘመናት በፊት ማለትም በመሃከለኛው ምስራቅ፣ በሰሜን አፍሪካ፣ አውሮፓ እና በቀሪው አለም ከመግባቱ በፊት እንደሆነ የታሪክ ሰዎች የጻፉት ጉዳይ ነው፡፡ የሁለቱም ሃይማኖት ( የክርስትና እና እስልምና ሀይማኖት ተከታዮችን  ማለቴ ነው፡፡) ለዘመናት በፍቅር ፣ ሰላም እና አንድነት ኖረዋል፡፡ ዛሬም እየኖሩ ነው፡፡ አክራሪ ጽንፈኞች በኢትዮጵያ ምድር ችግር ለመፍጠር ቢሞክሩም ያሰቡት አልተሳካም፡፡

ፕሮፌሰር ደስታ ሀሊሶ የስነመለኮት ሊቅ ሲሆኑ በኢትዮጵያ አክራሪ የአስልምና ቡድኖች በኢትዮጵያ መርዛቸውን ለመርጨት እንደማይሳከላቸው  በተለይም በፖለቲካው አለም እንደማይሳከላቸው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ እጠቅሳለሁ፡፡

‹‹ የአክራሪ ጽንፈኛ ቡድኖች ህልም በኢትዮያ ምድር እውን ሊሆን አይቻለውም፡፡ ኢትዮጵያ ያወረዷትን አዋርዳ፣ ያንኳሰሷትን አንኳሳ፣ ሊጠፏት የመጡትን አጥፋታ የምትኖር ሀገር ናት፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የአክራዎች እንቅስቃሴ በሃይማኖት መሃከል ግጭትን ሊቀሰቀሰው ያስችለዋል፡፡

አባስ ሀጂ ጉናሞ የተባሉ ምሁር በበኩላቸው ‹‹ እስላም፣ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና የኦሮሞ ብሔርተኝነት ›› በሚል ርእስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ እንደገለጹት  በኢትዮጵያ የሚኖሩ የተለያየ እምነትና ሀይማኖት ያላው ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ተከባረው ኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ሀይማኖት እምነት ቢኖራቸውም ለዘመናት በፍቅር አንድነት እና ሰላም ለዘመናት ኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንን መለየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ጤፍ ናቸው፡፡ አንዱን ከአንዱ መለየት አዳጋች ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ተደበላልቀዋል፡፡ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ በቀላሉ የሚፈታ  አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው፡፡ ደርቡሽ መጥቶ ያላሸነፈው፣ ቱርክ መጥቶ ምንም ያላደረገው፣ ግራኝ መሀመድ፣ ዮዲት ጉዲት፣ ጣሊያን፣ ወያኔ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልማሱት ስር የለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ግን አልጠፋም፡፡ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው፡፡ አባስ ሀጂ በእንግሊዝኛ የጻፉት የበለጠ ገላጭ ስለሆነ እጠቅሳለሁ፡፡ 

In his very profound research work under the title “Islam, the Orthodox Church  and Oromo Nationalism” Abbas Haji Gnamo defines the historical roots of both  religions and the dynamics between people of various religions in Ethiopia and concludes that these relationships have been based on tolerance and a full sense  of belongingness to one country with mutual aspect and equality. I hope such  sincere intellectual voices would prevail and prevent Ethiopia from descending  into the chaos of ethnic conflict that we have seen in so many other African  nations.  

በሌሎቹ የአፍሪካ ክፍሎች እውን እንደሆነው በኢትዮጵያም ችጋር፣ ስራፈትነት ካልጠፉ ኢትዮጵያም ለአክራሪ ጽንፈኞች ቡድኖች ለም መሬት ለመሆን ትችላለች፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ተቻችለውና ተፋቅረው ለዘመናት ቢኖሩም ችጋርና የሥራ ማጣት ለጽንፈኞች መሰሪነት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ በተለይም ወጣቱ ትውልድ የሥራ እድል ሊከፈትለት ይገባል፡፡ በብዙ የአፍሪካ ክፍሎች ጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈነጩት ስራ የሌላቸውንና ተስፋ ቢሶችን በማሰባሰብ ጉልበታቸውን በማሳበጥ ነው፡፡

እንደመደምደሚያ

ምንም እንኳን  የኢትዮጵያ ህዝብ በፍትህ አደባባይ ቀርበው ፍርዳቸውን እንዲቀበሉ በጉጉት የሚጠብቃቸው የወያኔ የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች በመእከላዊ መንግሰት ቁጥጥር ስር ባይወድቁም ( ቢያንስ አሁን ድረስ እጃቸው ስለመያዙ በይፋ አልተነገረም ) የወያኔ ሀይልና ክንድ ላይመለስ ተሰባብሯል፡፡ የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግስት ጠንካራ መሆን አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት የፈጸሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የዚችን ታካዊትና ምስኪን ሀገር ሀብትና ንብረት ያለ ይሉኝታ፣ ለከት በሌለው ባህሪ የዘረፉ ወንጀለኞች እና የከንቱ ከንቱዎችን በህግ ፊት ማቅረብ ይገበዋል፡፡ አንድ ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት የሌላት ሀገር እንደ ሀገር አትቆጠርም፡፡ ስለሆነም የወያኔ ፊትአውራሪዎችን ወታደራዊ ሀይል አክርካሪ የሰበረው የማእከላዊ መንግስት፣ እነኚህን ግፈኞች እጃቸውን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ ማለት የማእከላዊው መንግስትን ጠንካራነቱን ማሳያ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የተዳከመች በመሰላቸው ጊዜ የኢትዮጵያን ድንበር የሚገፉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሳይቀር አደብ ይገዛሉ፡፡ አደብ የሚገዙት ግን በሀገር ላይ በደል የፈጸሙ ፣ የሀገርን ሀብት የዘረፉ የቀን ጅቦችን ሁሉ ለፍርድ የሚያቀርብ ማእከላዊ መንግስት መኖሩን ሲገነዘቡ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያን የደፈሩ የውጭ ሀይሎችንና የውጭ ቅጥረኞችን የሚቀጣ፣ የሚያሸንፍ ማእከላዊ መንግስት ይሻሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የኢትዮጵያ መንግስት የሚጠይቀውን ሁሉ ለማሟላት ወይም ህይወቱን ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነው ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስትም የህዝብን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ ጽንፈኞችን ሁሉ መከላከል መንግስታዊ ግዴታም ነው፡፡ ከዚህ ባሻግር ኢትዮጵያን ዲሞክራቲክ ሀገር አንድትሆን የፖለቲካ አውዱን ማስፋት፣ የጎሳ ፖለቲካን ማምከን፣ የህግ የበላይነትን ማስፈን፣ የኢትዮጵያን ህገ መንግስት በሰለጠነ መንገድ ማሻሻል፣ የጎሳ ፌዴሬሽንን በህግ መሰረት ላይ ሆኖ ማምከን የቅንጦት ሳይሆን የህልውና መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

 ኢትዮጵያውያን በጎሳ ማንነታቸው ሳይሆን በሰውነት ደረጃቸው መብታው ሊከበር ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛቶች የሰውነት ክብራው ከተጠበቀ ሰላም ይሰፍናል፡፡ የህዝብ ደህንነትም እውን ይሆናል፡፡ በእውነት መሰረት ላይ የሚደረግ ብሔራዊ እርቅ፣ የእውነተኛ ታረክ መጻፍ፣ ታሪክ ማወቅ ኢትዮጵያን የነጻት ምድር ለማድረግ ይረዳል፡፡

ጽንፍ የረገጠ ነውጠኝነት የሚጠፋው ወይም የሚቀንሰው ሰላምና አንድነት ሲኖር እንደሆነ መታወቅ አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጊዜው ሳይረፍድ የኢትዮጵያን አንድነት በአስተማማኝ መሰረት ላይ ማቆም አለበት ብዬ ሳስታውስ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የአፍሪካው ቀንድ በአለም ላይ ካሉት አካባቢዎች ሁሉ በበለጠ ሁኔታ ከፍተኛ አለም አቀፍ ወታደራዊ ሀይሎች የሚርመሰመሱበት ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት፣ በኢትዮጵያ አንድነት ጽ እምነት ያለው፣ በሀገር ፍቅር ስሜት የተቃጠለ ወታደራዊ ሀይል መመስረት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የሰላምና አንድነት ጠላት የሆነውን ወያኔን ሀይል አከርካሪውን እንደሰበረው ሁሉ ለኢትዮጵያ አንድነት የሚደማ ልብ የሌላቸውን ጽንፍ የረገጡ ሀይሎችን በፍትህ አደባባይ ማቅረብ አለበት የሚለው የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡

በነገራችን ላይ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ሰኔ 15 2014 የአሜሪካን የኢምጊሬሽን አገልግሎት ባወጣው ጥናት መሰረት የወያኔ ድርጅትን በአሸባሪነት መዝገብ ውስጥ አስፍሮታል፡፡ ስለሆነም ይሄ ድርጅት ለወደፊቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድ ውስጥ ስለመሳተፉ አለመሳተፉ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት በእውነት መሰረት ላይ ሆኖ በይፋ ማሳወቅ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንደላ ከወያኔ መውደቅ በኋላ ጽንፍ የረገጡ ነውጠኞች ለኢትዮጵያ የሕዝብ ደህንነት ስጋት እንዳይሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት በብርቱ መስራት ያለበት ይመስለኛል፡፡ የዒትዮጵያ ህዝብ ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ የአንበሳው ድርሻ የመንግስት ነው፡፡ ሰላም፡፡

(According to the policy memorandum of US Immigration  Services of June 15, 2014: “the TPLF qualifies as a Tier III terrorist  organization prior to May 1991”, that is, until it became the government. )

ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም.

 Conclusion 

Though the TPLF leaders whom most Ethiopians have demanded that they  be brought to justice have not yet been captured, the TPLF force has been  irreparably crushed. The center has asserted its power as it should have done  from the get go. There cannot be a country without a center. TPLF defied  this basic commonsense. Ethiopians want to see a center that crushes all  those who resort to violence and that addresses the central issue of democratizing Ethiopia, where ethnicity does not infringe on the inalienable  rights of people to be equal under the law. This would mean changing the  constitution, delegitimizing ethnic federation, and electing its leaders through  a fair and free election under a transitional government that would not  interfere in the shaping of the constitution and running of the election.

For once, let the people speak! What is needed in Ethiopia is a devolution of  power under a non-ethnic based federal system which will assure people  that, despite their ethnic backgrounds, they will all be Ethiopians first, and  own the country together. Genuine “Truth and Reconciliation“ and the  eradication of distorted history through dialogue and education would slowly  but surely bring back Ethiopia where it belongs — the “Hope and Vanguard of  Freedom”, as it has always been and told by blacks and other oppressed  people across the globe for centuries. 

Violent extremism can be fought back and the challenge of “Human Security”  can be addressed successfully only in peace and unity. Ethiopians should  remember that they have a country that is extraordinarily beautiful and having  an unparalleled history, but a country in one of the most complex security and  militarized zones in the world. Being seen as a weak state will invite many  kinds of enemies. Let our leaders be bold enough to pave a path to a strong  Ethiopia by making the necessary fundamental changes now before it is too  late. If the Ethiopian leadership can crush one of the staunchest enemies of  peace and unity in our history, then it can easily crush the OLF and other  extremists. Both OLF are TPLF fulfill the requirements of being designated as  terrorist organizations, dangerous not only to peace and security in Ethiopia  but to the region. According to the policy memorandum of US Immigration  Services of June 15, 2014: “the TPLF qualifies as a Tier III terrorist  organization prior to May 1991”, that is, until it became the government. Now  that it is waging war against its own people it should be re- designated as a  terrorist organization. Oromo nationalists have inherited the ideology and  practice and implementing it more intensely and aggressively than the TPLF.  There will be no sustainable peace unless it too is crushed in the same kind  of determination. Amharas have proved once again that they will be with any  government and any leader that has the interest of a united, equal, just and  free Ethiopia first

Listen to this : https://www.youtube.com/watch?v=LgoW4GMlftA 

END 

 Join the conversation. Like borkena on Facebook and get Ethiopian News updates regularly. As well, you may get Ethiopia News by following us on twitter @zborkena

Filed in: Amharic