>

ምርጫው ይቆየን:- ከዛ በፊት የመታረጃ ሜንጫና ገጀራው ፤  ቀስትና ቢላው  ይሰብሰብ!!! (ፂዮን ዘማርያም)

ምርጫው ይቆየን:-

ከዛ በፊት የመታረጃ ሜንጫና ገጀራው ፤  ቀስትና ቢላው  ይሰብሰብ!!! 

 ፂዮን ዘማርያም

ይድረስ ለሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በወያኔ ኢስብአዊ ጭፍጨፋ በግፍ የታረዳችሁ የኢትዮጵያ ሠማዕታት የአማራ  ልዩ ፖሊስና ሚሊሽያ እንደደረሰላችሁ  ምስክርነታችሁን በመስጠታችሁ  እናመሰግናችኃለን፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ወረዳ በጉሙዝ ፓርቲና በኦነግ ሸኔ በግፍ ለሚታረዱ አማራዎች የሰሜን ዕዝ ሠራዊት እንዲደርስላቸው የአማራ ህዝብ ጥሪ ያቀርብላችኃል፡፡ የጦር መሣሪያው ለማን ነው የሚወለወለው!!! ‹‹በእራስህ ላይ እንዲደረግ የማትፈልገውን በሌሎች ላይ አታድርግ›› መፅሃፉ ይላልና!!!
ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ወይ በሜንጫ ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማሸነፍ ቆርጦ ተነስቶል፡፡ ህዝቡ ግን  ምርጫው ይቆየን፣ የመታረጃ ሜንጫው፣ ገጀራው፣ ካራው፣ ጦሩ፣ በፊት እንዲሰበሰብለት ይማፀናል!!! በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሁንም ብዙ ህዝብ እየታረደ ሲሆን መቶ ሰባ አምስት ሽህ  ህዝብ ከቀየው ተፈናቅለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ስድስተኛው ዙር ምርጫ ይቆየን፣ በሃገሪቱ የተሠራጨው ህገወጥ የጦር መሳሪያ የመታረጃ   ገጀራው፣ ሜንጫው፣ ካራው፣ ጦሩ፣ በፊት ይሰብሰብልን ብሎ ይማፀናል፡፡ ደህና ቀን እስኪመጣ የህዝብ የፀጥታና ደህንነት ሁኔታ እስከሚረጋገጥ ዶክተር አብይ አህመድ ሁሉንም ዜጋ በእኩልነት፣ በወንድማማቸነት፣ በሠላምና በፍቅር ያለ አንዳች አድሎ እንዲያስተዳድር ለህዝብ ቃል ኪዳኑን ያፅና፡፡ በምርጫ ስበብ ሌላ የዘር ማጥፋትና ግጭት ሊነሳ እንደሚችል ከተለያዩ ማስረጃዎች ተነስተን ስጋታችንን እንገልፃለን፡፡
* በኢትዮጵያ ህገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ዶክተር አብይ ስልጣን ከጨበጡበት መጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ በከፍተኛ ዓይነትና ብዛት መጨመሩ መረጃዎች ይጠቆማሉ፡፡ ‹‹የዶክተር አብይ መንግስት በዘገበው መሠረት በአለፈው አመት በአፍሪካ ቀነንድ አገሮች ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የተያዙ የጦር መሣሪያዎች ውስጥ 21 መሽን ጋንስ፣ ሠላሣ ሦስት ሽህ ሺጉጦች፣ሁለት መቶ ሰባ አምስት ጠመንጃዎችና ሦስት መቶ ሽህ ጥይቶች መያዛቸው ታውቆል፡፡››1 Prime Minister Abiy Ahmed’s government said last April that it had seized 21 machine guns, more than 33,000 handguns, 275 rifles and 300,000 bullets in different parts of the Horn of Africa country over the previous year. In October security forces confiscated a further 2,221 handguns and 71 Kalashnikov assault rifles in Gonder in the Amhara region, one of the areas particularly affected by ethnic strife, domestic media said. The rifles had been smuggled into the country in oil trucks from Sudan, they said. The spread of small arms has been partly blamed for hundreds of killings in various ethnic conflicts over the past two years that have displaced more than 2.7 million people.
* የአዲስ አበባ ፖሊስ አስራስምንት ቦንብ፣ ሰባት መቶ መሣሪያዎች በቁጥር ሥር አደረገ፡፡ NEW BUSINESS ETHIOPIA/By BEHAK Multimedia – Business & Investment Stories Since 2009/Addis Ababa Police seizes 18 bombs, over 700 weapons (newbusinessethiopianews November 12, 2020) In collaboration with the national intelligence and the Addis Ababa Police Commission has seized over 700 illegal weapons including 18 bombs and explosives.
* በብዙ ሽህዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ ገጀራዎች፣ ሜንጫዎችና፣ ቢላዎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ በድብቅ ሊገቡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡ Thousands of illegal machete, assault knives seized while heading to Addis Ababa (September 21, 2019) Over 2200 machete, and bolo, among other things, are reportedly seized at Debre Berhan checkpoint while heading to the capital Addis Ababa.
* የህገወጥ የመሣሪያ ንግድ ዝውውር የሚያካሂዱ ሰዎች በኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበሮች በኩል በሚያዋስኖት ወሰን አንደኛው  የህገወጥ ንግድ ዝውውር  መዳረሻ መሆኑ ታውቆል፡፡  የተያዙት ብዙዎቹ ሽጉጦች ቱርክ ሠራሽ ስሪቶች እንደሆኑ ታውቆል፡፡ Ethiopia’s border with the Sudan is often mentioned as one of the major route for the people engaged in illegal arms trade. While most of the pistols captured so far are made in Turkey.
* ማጠቃለያ ከዶክተር አብይ መንበረ ሥልጣን ዘመን፣ የህገወጥ የመሣሪያ ንግድ ዝውውር ምክንያት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተለያዩ ክልሎች፣ በብሄር ግጭቶች የተነሳ ሞተዋል፣ እንዲሁም ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሽህ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡The spread of small arms has been partly blamed for hundreds of killings in various ethnic conflicts over the past two years that have displaced more than 2.7 million people. ምንጭ (Ethiopia passes gun control law to tackle surge in violence/The Thomson Reuters Trust Principles.)
* የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አገራዊውን ምርጫ ግንቦት መጨረሻ ወይም ሰኔ መጀመሪያ አካባቢ ለማካሄድ እቅድ የያዘ ሲሆን፤ 50 (ሃምሳ) ሚሊዮን ያህል መራጮች ድምጽ ይሰጡበታል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ 50 ሺህ 900 (ሃምሳ ሽህ ዘኝ መቶ) የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚኖሩ ተነግሯል።
በ2013ዓ/ም ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መምጫ ቦርድ ከሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ እስከ ሦስት መቶ ሽህ ሰዎች በምርጫ አስፈፃሚነት የሚሳተፉ በመሆኑ ይህ በሃገሪቱ ያለው የህገወጥ የመሣሪያ ንግድ ዝውውር ከምርጫው በፊት፣ የመገደያችን ሹጉጦቹ፣ ጠመንጃዎቹ፣ ቦንቦቹ፣ የመታረጃችን ሜንጫው፣ ገጀራው፣ ካራው፣ ቀስቱ ወዘተ ከወዲሁ ያልተያዘው ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች እንዲሰበሰብ ምርጫ አስፈፃሚዎች ምርጫ ቦርዱን ብትጠይቁ ለእራሳችሁና ለህዝብ ፀጥታና ደህንነት ትተርፋላችሁ!!! ካለዛ ግን እንኳን መከላከያ ሠራዊት ወፍ አይደርስላችሁም!!!
* በሌላ በኩል ከትግራይ ክልል የጦር አበገዞች የተማረከ ልዩ ልዩ የመከላከያ የጦር መሣሪያዎች በአርባ አንድ የጭነት መኪናዎች ከነታሳቢያቸው፣ የተጫኑ መኪኖች ከትግራይ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል አንቦ ከተማ እንደተራገፉ መረጃ ገልፆል፡፡ መንግሥት መግለጫ ቢሰጥበት ይመከራል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሥነ-ህዝብ (Demography) ፕወዛ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው የዘር ማፅዳት ዋና  ተዋናዬች የሆኑት ኦነግ ሸኔና የጉሙዝ ፓርቲ ሲሆኑ ዋና አላማቸውም የአማራን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ብሎም አማራ ህዝብን ከመተከል አስወጥተው በስድስተኛው ዙር ምርጫ እነሱ ለማሸነፍ እንዲችሉ ነው፡፡ ታህሳስ 13/2013 ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ሁለት መቶ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ይታወቃል፡፡
ጥር ማክሰኞ 4/2013 ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በደባጤ ወረዳ፣ ዳለቲ ቀበሌ ከሰማንያ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገልፆል፡፡ የሟቾች ቁጥር ከመቶ በላይ ይገመታል፡፡ እንደ ኢሰመጉ መረጃ መሠረት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በአመዛኙም የአማራ ተወላጆችን በማረድ የዘር ማጥፋት በኦነግ ሸኔና የጉሙዝ ፓርቲ ተጠያቂ እንደሆኑ መረዳት ተችሎል፡፡ በክልሉ በመቶ እስከ ሁለት መቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ተሰደዋል፡፡  የኢትዮጵያ ምርጫ ባርድ ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና ሲል መስተዋሉ ህዝቡ ምርጫው ይቆየን፣ የመታረጃ ሜንጫው፣ ገጀራው፣ ቢላው፣ ጦሩ በፊት ይሰብሰብልን ብሎ ይጠይቃል!!! ኢሠመኮ እና ኢሠመጉ የተደረገው ወንጀል የዘር ማፅዳት ብለው ከመጥራት በመቆጠብ ግጭት በማለት አድበስብሰውታል፡፡ ስለስድስተኛው ዙር ምርጫም  በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ያዩትን በመግለፅ ለምርጫው አስተማማኝ የፀንታና ደህንነት ሁኔታ እንደሌለ በመመስከር ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽን አስተማማኝ ሁኔታ እንደሌለ መመስከር ይገባቸዋል እንላለን፡፡
በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ሥነ-ህዝብ (Demography) ፕወዛ
ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በዘር ማፅዳት ሥራ ላይ ከተሠማራ ሦስት አመታት ተቆጥሮል፡፡ ከኤርትራ ወደ ሃገር መሣሪያ ሳይፈታ የገባው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ይዞቸው የገባውን ጦር አንድ ሽህ አምስትመቶ የሚሆነውን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር እንዲቀላቀል በማድረግ ከሦስት ሽህ አምስት መቶ የሚገመተውን ከነትጥቁ በኦነግ ሸኜ ስም አንዴ ለአባገዳዎች ተሠጥተዋል ወዘተ ብለው እየቀለዱ ኦነግ ሸኜ በየትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ብዙ ሽህ ወጣቶችን በመመልመል፣ ሃያ ሦስት ባንኮች በመዝረፍ፣ የአማራ ተወላጆችን በማረድ፣ በዘር ማጥፋት ሥራ እንዲሠማራ ስምሪቱን ህወሓት፣ኦነግና ኦዴፓ ብልፅግና  ሃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡  አነግ ሸኔ ከስድስተኛው ዙር ምርጫ በፊት ከክልሉ ሌላዎቹን ዘር አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ በማስወጣት ምርጫውን ለማሸነፍ  የነደፈው የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ሴራን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተባባሪ በመሆን ህዝቡን በመሸጥ ከምርጫው በኃላ እንባሣደር ሆነው ለመሾም ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡
* የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የህዝብን የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ ባለመረዳት ምርጫ ለማካሄድ በሚያደርገው ጥረት የብዙ ንፁሃን ደም ሊፈስ እንደሚችል አልተረዱም፡፡‹‹በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉድሩ ውስጥ አባይ ጮመን በተባለው ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ሁለት የዓይን እማኞች በኅዳር 29/2013 ዓ.ም ላይ ሰባት ሠላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እንደተመለከቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “ማክሰኞ ምሽት በድምጽ ማጉያ ለአስቸኳይ ስብሰባ የሚደረግ ጥሪ ሰማን” ይላሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት የአካባቢው ነዋሪ። “ስምንት ጸጉራቸው ረዥምና ፊታቸውን የሸፈኑ ታጣቂዎች፤ ከተሰበሰበው ሰው መካከል አማራዎች የሆኑ እራሳቸውን እንዲያሳውቁ ከጠየቁ በኋላ ቀሪዎቻችንን ወደ ቤታችን እንድንሄድ ነገሩን። ከዚያም 10 የሚሆኑትን ይዘዋቸው ሄዱ።” “ተለቀው ይመጣሉ ብለን ሌሊቱን በሙሉ ብንጠብቅም ሳይመጡ ቀሩ። በሚቀጥለው ቀንም የሰባቱን አስከሬን አገኘን” ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።›› (ሠላማዊ ነዋሪዎች ሰለባ እየሆኑበት ያለው የኦሮሚያ ክልል ግጭት 12 ጥር 2021/ቢቢሲ አማርኛ ድረ-ገፅ)
* የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሞ ፖሊስ ኮሚሽነር የህዝብን የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ በኦነግ ሸኔ አራጅ ብድን የብዙ ንፁሃን ደም እየፈሰሰ እንዳለ የፖሊስ ኮሚሽነሩን ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ብርቱካን ሚደቅሳ መጠየቅ ይገባታል እንላለን፡፡ ‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር አበሩ ባላቸው ከአንድ ሽህ በላይ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መውስዱንነ የኦሮሞ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ገልፀዋል፡፡ በፀጥታና ፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ሰዋችን አደራጅቶ በመያዝ ከጎነግ ሸኔ ጋር  የሚሰሩ አካላትጨምሮ ከ1000 በላይ የፖሊስ አባላት ላይ የተለያዩ  እርምጃዎች መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆል፡፡ በቡድኑ የጥፋት ተልእኮ አልፎ አልፎ የሚሳተፉ፣ የሚጠረጠሩ፣ መረጃ የሚሰጡ፣ ከእነርሱ ጋር የሚያብሩ፣ ከጎሰኝነት፤ ከከባቢነትም ተነሰተው ከ ፀጥታ መዋቅርና አመራር ጋር በሚመሳጠሩት ላይ በየወቅቱ ግምገማዎች እየተካሄደ እርምጃ ይወሰዳልም ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡(EPA)›› የሰሜን ዕዝን መከላከያ ሠራዊት ህወሓት/ ወያኔ ሠርጎ በመግባት ሠራዊቱን በመውጋት  ገደሉ፣ አሰሩ፣ አገቱት መጨረሻቸውም የወያኔ መደምሰስ ሆነ፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በኦነግ ሸኔ ድብቅ ቡድን ውስጡ ተቦርቡሮል፣ ከውስጥ መረጃ የሚሰጡ ፖለሶች ስላሉ ኦነግ ሸኔን ማጥፋት አልቻሉም፡፡  የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ጥቃት ምን ይማራል? አበው ‹‹አሥር ጊዜ ለካ፣ አንድ ጊዜ ቁረጥ!!!!›› ይላሉ፡፡
በተመሳሳይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በምርጫው እንደማይሳተፍ እየገለፀ ይገኛል፡፡ የታሰሩት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ ጎዶቹ በግፍ መታሰር የአዲስ አበባ ህዝብ ምርጫውን ላለመሳተፍ የእስክንድር ነጋን አንድ ፊሽካ ብቻ ነው የሚጠብቀው ከወህኒ ቤት ሆኖ፡፡ እስክንድር ነጋ ብቻውን የአዲስ አበባን ህዝብ እንዲወክል ህዝብ እውቅና ሰጥቶታል፡፡ አስክንድር ነጋ በእምነቱና በፅናቱ አንድ ክፍለጦር ይመክታልና፡፡
የትግራይ ክልል መንግሥት ምርጫ በጦርነቱ ምክንያት ለሌላ ጊዜ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተወስኖል፡፡
በአዲስ አበባና ድሬዳዋ የከተማ አስተዳደር ሥነ-ህዝብ (Demography) ፕወዛ
በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ንዋሪዎችን የአዲስአበባ የመታወቂያ ካርድ በመስጠት የከተማዋን ሥነ-ህዝብ በመቀየር  ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማሸነፍ የሚደረገውን ህገወጥ ሥራ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዝምታ አልፎል፡፡ የመታወቂያ ካርድ በአዳነች አቤቤ ትእዛዝ በየአስሩም ክፍለ ከተሞች በተረኞች ይታደላል፡፡ ነፃና እንከን የለሹ ምርጫ፣ ዴሞክራሲ  አፍንጫውን ተሰንጎ ጭር እንዳለች ዶሮ ዝቅዝቅ ተሰቅሎል፡፡ ኦዴፓ ብልፅጋና ፓርቲ በዴሞክራሲ ስም ስንት ግፍ ሠራ!!!
የኢትዮጵያ ምርጫና የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ
እንደ ፉድ አሲስታንስ ፋክት ሽት የአፕሪል 16 ቀን 2020 እኤአ (FOOD ASSISTANCE FACT SHEET – ETHIOPIA ዜና ዘገባ መሠረት፥
በሃገር አቀፍ ደረጃ ስምንት ሚሊዮን ህዝብ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በዚህ አመት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ችግሩ በግጭት፣ በዝናብ እጦት፣ በአንበጣ ወረራ፣ የበሽታ መከሰት እንደ ኮቪድ አስራዘጠኝ ወረርሽኝ የህብረተሰቡን ህይወትና ኑሮ ህልውና በማናጋቱ የተነሳ የዕለት ጉርሳቸውን ያጡት ወገኞች ቁጥር ጨምሮል፡፡ “Conflict and climatic shocks contribute to elevated emergency needs and population displacement in Ethiopia, according to the country’s 2020 Humanitarian Needs Overview.  Nationwide, more than 8 million people may require humanitarian assistance during the year, with violence, erratic rainfall, pest infestations, and disease outbreaks negatively affecting the lives and livelihoods of vulnerable people.
* በግምት አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በሃገር ውስጥ በግጭትና በዓየር ለውጥ የተፈናቀሉ መሆኑ ታውቆል፡፡አንድ ሚሊዮን ህዝብ ወደቀያቸው በመመለስ የስብዓዊ እዳታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ይላል እንደ 2020 የስብዓዊ ድጋፍ ፕላን ፡፡ ኢትዮጵያ ሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት ሽህ ስደተኞች ከጎረቤት ሃገራት የመጡ ይገኛሉ፡፡ “Approximately 1.8 million Ethiopians who are internally displaced due to conflict and climate shocks and more than 1 million Ethiopians who have returned to prior areas of residence are in need of humanitarian assistance, according to the 2020 Humanitarian Response Plan.  Ethiopia also hosts 758,000 refugees from neighboring countries.”
* በ2020 እኤአ 176,983 ሜትሪክ ቶን እህል (174.1 ሚሊዮን ዶላር) ስብዓዊ እርዳታ አግኝታ ነበር፡፡
* በ2019 እኤአ 500,800 ሜትሪክ ቶን እህል (428.8 ሚሊዮን ዶላር) ስብዓዊ እርዳታ አግኝታ ነበር፡፡
* በ2018 እኤአ 573,928 ሜትሪክ ቶን እህል (397.9 ሚሊዮን ዶላር) ስብዓዊ እርዳታ አግኝታ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ እስከዛሬ በምርጫም ሆነ በሜንጫም አንባገነን ሥርዓት ነው የተገነባው!!!  ማንኛውም ሰው የመኖር መብቱ ይጠበቅለት!!! በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ይሁን!!!  በሃገራችን በዴሞክራሲ ስም ብዙ ግፍ ተሰርቶልና!  ምርጫው ይቆየን፣ የመታረጃ ሜንጫውና ገጀራው፣ በፊት ይሰብሰብ!!! የምርጫ ሥጋታችንን ገልፀናል እናንተስ?
(ኢት-ኢኮኖሚ) [Ethiopoint]
Filed in: Amharic