>

የካይሮ ሰዎች የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነትን ለታይታ እንጂ በተግባር አይፈልጉትም!!! (ጋዜጠኛ ሥለዓባት ማናየ)

የካይሮ ሰዎች የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነትን ለታይታ እንጂ በተግባር አይፈልጉትም!!!
ጋዜጠኛ ሥለዓባት ማናየ

ግብፃዊያን ለአፍሪካዊ ብሔርተኝነት ያላቸው ተስፋ  የት ድረስ ነው?
 
እየገነቡ መደራደር እየሰሩ ማሴር( አዋጩ  የግድብ ፖለቲካ ዲፕሎማሲ)
የግብፃዊያን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለይ በሁለት ጠርዝ ላይ ቆመው ይታያሉ። የአረብ ብሔርተኝነት እና የአፍሪካ ብሔርተኝነት ዙርያ። የሁሉም ጠንሳሽ እና አራማጅ ፍኖተ ካርታ ትልም አስያዥ ደግሞ አንድ ሰው ናቸው።
የአረብ እና የአፍሪካ ብሔርተኛው የቀድሞው የግብፅ መሪ ገማል አብደል ናሰር ። ናስር በ1950ዎችመጀመሪያ ላይ ወደ ስልጣን ሲመጡ እጅግ አብዮተኛ እና ብሔርተኛ ነበሩ። በምድር ላይ የሚኖር የሰው ልጅ ሁሉ በሁለት አብዮቶች ማለፍ የግድ ይለዋል የሚሉት ገማል አብደል ናስር
አንድም በፖለቲካ አብዮት ውስጥ ሁለትም በማህብራዊ አብዮት ውስጥ ይላሉ። ሁለቱም አብዮቶች ደግሞ እርስ በእርስ የሚቃረኑ ናቸው። ገማል አብደል ናስር ግን በሁለቱም አብዮቶች ውስጥ አልፈዋል ።
(The philosophy of the revolution ) በሚለው መጣጥፋቸው እና በፕራግ ዩኒቨረሲቲ በአውሮፓዉያኑ 1967 ላይ በታተመው የአብዮተኞች መጽሐፍ ስብስብ ውስጥ ገፅ 144 ላይ በይፋ እንዳብራሩት ፡
ግብፃዊያን በሁለቱም አብዮተኞች ያልፉ ዘንድ የስነ ህዝብ እና አካባቢያዊ አኗኗራቸው ግድ ብሏቸዋል።
በቦታ አቀማመጥ አፍሪካዊ በባህል እና በታሪክ ደግሞ አረባዊ ብሔርተኝነት ግድ ይላቸዋል እንደ ናስር። ናስር የአረብ ብሔርተኛ ወጣቶችን ሰብስበው የተባበረች አረብን የመፍጠር ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተው ጅምር ውስጥ ገብተው ነበር።
እየተገነባ እየፈረሰ ዳግም የሚገነባው የአረብ ፖለቲካ በእርሳቸውም ላይ ሰለሰ እንጂ። የአፍሪካ ብሔርተኝነትንም ከእነ ቀኃሥ ጋር አብረው ቀምረዋል።
የስልጣን መቋጫቸው አካባቢ ከአፍሪካ ይልቅ አረባዊነት ላይ ያተኮሩት ናስር።
ናስር በዓባይ ናይል ወንዝ ላይ ግን ከአፍሪካዊነት ይልቅ አረባዊነት መንፈሳቸው ጎልቶ ወጥቷል። ሰሞኑን 50ኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው የታላቁ አስዋን ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ እና የናስር ሐይቅ ምርቃት ላይ የጋበዟችው እንግዶች አረቦች ነበሩ።
የሶሪያ እና ልክ እንደ ግብፅ የምትወዛወዘውን የሞሮኮ ንጉሥ። ናስር ሄዱ ሳዳት መጡ ሳዳት ሄዱ ሙባረክ መጡ ሙባረክ ሄዱ ሞሀመድ ሙርሲ መጡ ሙርሲ ሄዱ አል ሲሲ መጡ!!!
በእነዚህ የፖለቲካ መሰላል ውስጥ ግብፃዊያን አካሄዳቸው እና አመጣጣቸው አሸኛኘታቸው የተለያየ ቢሆንም ፤በዓባይ ፖለቲካ ግን ተመሳሳይ አቋም ነበራቸው አላቸውም። ዓባይ (ናይል) አፍሪካዊነቱን ዘንግተው አረባዊ የማድረግ የሴራ ፖለቲካ እና የተግባር የእርሻ መርሃ ግብር መሬት ላይ ትግብራ ።
ግብፅ ራሷ ብቻ ሳትሆን ሱዳንንም በእርሷ የውሃ ዲፕሎማሲ ራዳር ውስጥ በአረብ ዲፕሎማሲ ማዕቀፍ ውስጥ ለመክተት ከትናንት እስከ ዛሬ ድረስ እየሰራች ነው። አሁንም ቢሆን በሦስትዮሹ ድርድር የሄድ መለስ ፡የመውጣት እና መግባት ዲፕሎማሲ እየተከተሉ ያሉት ኢትዮዽያንበመሰልቸት ጎዳና እንድታዘግም በማድረግ በራሷ በቃኝ ባይነት እንዲቋርጥ የማድረግ፡ለሌላ የሴራ ፖለቲካ ዝግጁ የማድረግ አካሄድ ነው።
ካይሮ የአፍሪካ ህብረትን የድርድር አካሄድ ከጥንስሱ ጀምሮ አትፈልገውም ። ለይስሙላ ነው የገባችበት። ግን የሌሎችን የአፍሪካ ሀገራት ብሎም የጥቁር ህዝቦችን አዝማሚያ በማየት ከአፍሪካ ህብርት ብትውጣ የራሱ የሆነ የዲፕሎማሲ ተፅእኖ ይኖረዋል በሚል ስጋት ነው በአሳሳች ዲፕሎማሲዋ እደባች የምትጓዘው።
እነዚህን የካይሮ ወ ካርቱም መርዛማ ዲፕሎማሲ ምን አይነት ማርከሻ እናዘጋጅለት? የውሃ ዲፕሎማሲን ከቻይና እና ቱርክ ከፍ ብለን ከሩስያ ተመክሮ እንውሰድ።
እነዚህ ሦስቱ ሀገራት እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የላይኛው ተፋሰስ አባል ሀገራት ናቸው። ግዙፉ ግድቦችን አንድ ሳሆን ከደርዘን ባለይ ሲገነቡ የተከተሉት ዲፕሎማሲ እጅግ አስትማሪ ነው። እየገነቡ መደራደር እየሰሩ ማሴር የሚል ነው።
ቤጂንግም ሆነች አንካራ አልያም ሞስኮ የጀመሩትን ግድብ ለአፍታም ያህል ሳያቆሙ በድርድሩ አለምም እጅግ አሰልቺ ጉዞ ተጉዘዋል። ግን ሁሉም መጨረሻቸው በስኬት ተጠናቋል ።ዛሬ አትክልት እና ፍራፍሬ ከእነዚህ ሀገራት በገፍ ወደ ውጭ ይላካሉ።
ከታችኞች ተፋሰስ አባል ሀገራት ይደርስባቸው የነበረው የዲፕሎማሲ ጫና እና የአዞ እንባም ከንቱ ሆኖ ቀርቷል።
አሁን ታሪክ ተቀይሮ ከጫና ፈጠራ ወደ ትብብር እየዞሩ ነው ፡፡ ኢትዮጵያም እየገነባች  መደራደር እየሰራች ማሴር  አለባት።
ደግሞ ማሴር ምንድን ነው?
በዚህ የውሃ ዲፕሎማሲ ዙርያ ከቱርክአካሄድ እና  የእነ Mark Zeitoun; Jeroen Warner  የውሃ የበላይነት ዲፕሎማሲ ቀመርን ተከትለን ወደፊት የምናፍታታው ይሆናል።
Filed in: Amharic