>

ኢዜማ ውስጥ ያለው ኀይል ክፉ በሽታ ያለበት ነው...!!! (ጌታቸው ሽፍራው)

ኢዜማ ውስጥ ያለው ኀይል ክፉ በሽታ ያለበት ነው…!!!

ጌታቸው ሽፍራው

አለመታደል ነው እንጅ  አላማዬ ብሎ እንደሚያወራው ቢሆን ኖሮማ ኢዜማ ከእነ አብን፤ ባልደራስና መአህድ ጋር ነበር መስራት የነበረበት።  በውስጥ የሚሰራውን ደባ ሳይሆን በመርህ ደረጃ የያዘውን ኢትዮጵያን ለማዳን ከሚሰሩ ኃይሎች፣ ኢትዮጵያን ከማይጎዱ ኃይሎች ሆኖ ቢሰራ ትልቅ አቅም ነበር።
ግን ኢዜማ ውስጥ ያለው ኀይል ክፉ በሽታ ያለበት ነው። ኤርትራ እያለ አዲኃን የአማራ ድርጅት ስለሆነ እሱን እያገለለ ከሌላው የብሔር ድርጅት ጋር ግን አብሮ ሲሰራ የነበር ድርጅት ነው። በዳያስፖራው ዘንድ ከኦነግ ጋር የኦነግን ባንዲራ ሰቅሎ አብሮ የሰራ ኃይል ነው።  ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ተገንጣይ ድርጅቶች ጋር ሁሉ አብሮ ለመስራት በተለያየ ጊዜ የተነጋገረ ኀይል ነው። ችግሩ የአማራ ኃይል ጋር ሲደርስ ነው! ስለ አንድነት ከሚሰራ የአማራ ኃይል ይልቅ አሁን ከትህነግ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን የወጋውን ትህዴንን ጋር ሲነጉድ ነበር። አሁን ንፁሃንን ከሚያርደው የቤንሻንጉል ኃይል ጋር አብሮ ሰርቷል። ይሄው ኢዜማ ውስጥ ያለው ኃይል “ህወሓት ውስጥም ኢትዮጵያዊ ኃይሎች አሉ” ብሎ በይፋ መግለጫ አውጆ የፖለቲካ ሴሰኝነት ውስጥ የገባ ቡድን ነው።
 የታጠቀ ኃይል ስላለው ብቻ የቀረበውን አርበኞች ግንባርንም ከተጠቀመበት በኋላ መጨረሻ ምን እንዳደረገው እናውቃለን።
ኢዜማ ውስጥ ያለው ኃይል ክፉ አባዜ ባይኖርበት ከአብን ጋር መስራት ነበረበት።    ከአማራ ኃይል ጋር ባለበት ችግር፣ አማራን በጎጥ የሚከፍሉትን በየአቅጣጫው እየዞረ እየለቀመ እየመዘገበ ነው። ይህ ኃይል ክፉ አባዜ ባይኖርበት እነ አብን ከኦነግም ከቤንሻንጉል ነፃ አውጭም ይሻሉት ነበር። አማራን በጎጥ ለመበተን ከሚሰሩት አብን ይሻለው ነበር። ግን ችግሩ መሰረታዊ የአማራ ተቃርኖ ነው።
በእርግጥ ኢዜማ ውስጥ ሁሉም ክፉ ነው ማለት አይደለም። ምርጫው ሲደርግ በግለሰብ ደረጃ የምንደግፋቸው አካላት አሉ። ምርጫው ሲደርስ የምናወጣቸው ተጨማሪ ሚስጥሮች አሉ።
በአንፃሩ ይህ ክፉ ኃይል አደብ ገዝቶ፣ ቢያንስ በአደባባይ በሚናገረው አላማ ኢትዮጵያን ለማዳን ከሚሰሩት ጋር ባይተባበርም ደባውን ከተወ ሲሆን እንደግፈዋለን። ባንደግፈው እንኳ አጀንዳ አናደርገውም። በዚህ ጠልነቱ ከቀጠለ ግን  እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ማድረግ የምንችልበት በርካታ መረጃና ማስረጃዎች  አሉን!
Filed in: Amharic