>
5:21 pm - Saturday July 21, 2192

የአፍሪካውያን ተሃድሶና የምጣኔ ሀብት እድገት ደረጀ መላኩ ( የሰብዓዊ መብት ተሟጋች )

የአፍሪካውያን ተሃድሶና የምጣኔ ሀብት እድገት

ደረጀ መላኩ ( የሰብዓዊ መብት ተሟጋች )

Tilahungesses@gmail.com

መግቢያ

አብዛኞቹ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገራት የፖለቲካ ነጻነታቸውን እንደተጎናጸፉ ፣ ኢኮኖሚያቸውን ( ምጣኔ ሀብታቸውን) ለማሳደግ ይረዳቸው ዘንድ ከውጪ ሀገር ይገቡ የነበሩ ሸቀጦችን ለመተካት ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት ሞክረው ነበር፡፡ ወይም እንዲህ አይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ገቢራዊ አድርገዋል፡፡  ስለሆነም የአፍሪካ መንግስታት በዚህ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ምክረ ሃሳብ ቀርቦላቸው ነበር፡፡

Since political independence, many sub-Saharan African countries have more or less adopted the so-called import substitution industrialization (ISI) to develop their economies

የአፍሪካ አጠቃላይ የምጣኔ ሀብት የተገኘው ከዚህ ሴክተር ነበር፡፡ ይህም ሴክተር በእንግሊዝኛ መጠሪያው “Growth Pol” strategy  ›› በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ ለአፍሪካ እድገት ታልሞላት የነበረው ልክ እንደ ካፒታሊስት ሀገራት ‹‹ ገበያ መር ›› ኢኮኖሚ ነበር፡፡ ይሄን ተከትሎ እንደ ምጣኔ ሀብት ጠበብት የጥናት ውጤት ከሆነ ለሌላው ማህበረሰብ የምጣኔ ሀብት እድገት ተምሳሌት የሆነው የህብረተሰብ ክፍል ማለትም የመሃከለኛው የህብረተሰብ ክፍል ሊፈጠር ይቻለዋል፡፡ ይህ የመሃከለኛው መደብ የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በፋንታው ስራ መፍጠር እና ኢንዱስትሪዎች መገንባት ይቻለዋል፡፡ ከዚህ ባሻግር የተለያዩ ሴክተሮችን በማገናኘት የሸማቾችን ፍላጎት ለሟሟላት፣የጥሬ ሀብት አቅርቦትን ለማሳለጥ፣ በተለይም ከእርሻ ኢኮኖሚ የሚገኙትን ማለቴ ነው ሁኔታዎች ይመቻቻሉ፡፡ በመጨረሻም የአፍሪካ መንግስታት ከእንዲህ አይነት የምጣኔ ሀብት እድገት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም የግብር ክፍያ በከፍተኛ ደረጃ ስለሚጭመር ነው፡፡

እንዲህ አይነት የምጣኔ ሀብት ሰትራቴጂክ የምጣኔ ሀብት እድገትን በገንዘብ ለመደጎም የአፍሪካ ሀገራት መተማመን ያለባቸው ወይም የሚችሉት በእርሻ ምርቶቻቸው ውጤቶችና በጥሬ ሀብታቸው እንደሆነ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡ ከዚህ ባሻግር ካደጉትና ከበለጸጉት ሀገራት  ምን አይነት የኢንዱስተሪ ግብአቶችን መግዛት ወይም ማስገባት እንዳለባቸው በቅጡ መረዳት አለባቸው፡፡ ይህ መፍትሔ ብቻ ነው ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትን ከባህለዊና ኋላ ቀር የምርት ስርአት የሚያላቅቃቸው፡፡ ለአብነት ያህል ከእጅ ወደ አፍ የሆነ የእርሻ ዘዴ ወደ ላቀ የቴከኖሎጂና ዘመናዊ የእርሻ ዘዴ ለመሸጋገር ይረዳል፡፡፣ ( በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት የእርሻ ዘዴ ብሔራዊ ሀብት ለመፍጠር አያስችልም)  እንደነ ዶክተር በፍቃዱ በቀለ የመሰሉ አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ጠበብት በጥናታቸው እንደደረሱበት ከሆነ የገበያ መር ኢኮኖሚን በያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ማስፋፋት እያደገ የመጣውን የአለም ኢኮኖሚ ለመከተል ያስችላል፡፡ )

የዚህ ሰትራቴጂ ውድቀት

ከላይ የተጠቀሰው የእድገት ስትራቴጂ ውጤታማ ሊሆን የሚቻለው እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1960ዎቹ ላይ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በጊዜው በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሰለጠኑ ሀገራት ካላቸው የጥሬ ሀብትና የእርሻ ምርት ውጤቶች ፍላጎት አኳያ ጥቅም ወይም ገቢ ያገኙ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት የራሳቸውን የኢኮኖሚ እንደገና ለመገንባት ፍላጎት አሳይተው ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጥሬ ሀብት ፍላጎት እየጨመረ የመጣበት ጊዜ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ከዚህ ተቃራኒ በሆነ መልኩ እንደጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ መጨረሻና 1970ዎቹ መጀመሪ ላይ በኢንዱስትሪ የገፉ ሀገራት የኢኮኖ,ሚ እድገት በእጅጉ ቀንሶ ታይቷል፡፡ የተለያዩ ግንባታዎች በአብዛኛው ተጠናቀው ነበር፡፡ በሌላው ሳንቲሙ ግልባጭ ደግሞ የጥሬ ሀብት ፍላጎት በአንጻሩ ቀንሶ ታይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአለም የነዳጅ ዋጋ በአንጻሩ በእጅጉ ጨምሮ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸው የምጣኔ ሀብት መሰረት የሌላቸው፣ የራሳቸውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ( ከራሳቸው ህዝብ የእድገት ፍላጎት ጋር የተመጣጠነ) ማውጣት ያልቻሉት የአፍሪካ ሀገራት ይህንን መራር እውነት መጋፈጥ ግዴታቸው ሆኖ ነበር፡፡ አፍሪካ ከባድ የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ ወድቃ ነበር፡፡ ለአብነት ያህል ከጥሬ ሀብት ገቢ የሚሰበስቡት ግብር በአስደንጋጭ ሁኔታ ወድቆ ነበር፣ ባጀት ገቢ ስላጡ ያቀዱትን ስትራቴጂ ገቢራዊ ለማድረግ ተስኗቸው ነበር፣ በግዜው የአለም የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ ስለነበር የአፍሪካ ሀገራት ለተጨማሪ ወጪ ተዳገው ነበር፣

ምን ይበጃል ?

አፍሪካ ከኢኮኖሚ ድቀት ለመውጣት የሚከተሉትን እርምጃ መውሰድ እንዳለባት ሞዮ (Moyo, 2009) የተባሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ይመክራሉ፡-

  • አፍሪካ ሀገራት ከጥሬ ሀብቶች ባሻግር ሌላ የገቢ ምንጮችን ማሰብ አለባቸው( ከጥሬ ሀብት ኢኮኖሚ ጥገኝነት መውጣት አለባቸው )
  • ከምእራብ ሀገራት እና ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ገንዘብ መበደር አለባቸው፡፡ ብድር ከአደጋ ነጻ አይደለም፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ የተበደሩትን ገንዘብ ለመክፈል የጥሬ ሀብታቸውንና የእርሻ ውጤቶችን በፍጥነት መሸጥ አለባቸው፡፡
  • የአፍሪካ ሀገራት የካፒታሊስት ሀገራት እና አለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪዎች የሚያወጡትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ገንዘብ ለመበደር የአለም አቀፍ ገንዘብ ተቋማትና የካፒታስት ሀገራት የሚያወጡትን መስፈርት ማሟላት አለባቸው

ሆኖም ግን ይሁንና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ሞዮ ከላይ የሰፈረውን ምክረ ሀሳባቸውን ቢያቀርቡም  ከምእራቡ አለምም ሆነ ከአለም የአራጣ አበዳሪዎች  የሚገኘው የብድር ገንዘብ አሁን ድረስ የአፍሪካ ሀገራትን ኢኮኖሚ ስር ነቀል በሆነ መልኩ ማሳደግ አልሆነለትም፡፡ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ( በአንዳንድ አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አጠራር አራጣ አበዳሪዎች) መጠነ ሰፊ እርዳታና ብድር ቢሰጡም በአፍሪካ ምድር ላይ  ጠንካራ የገበያ ትስስር መፍጠር አላስቻላቸውም ::

ይሄን ተከትሎ በመጀመሪያዎቹ ሁለት አስርተ አመታት በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ዝቅተኛ መሆን የተረዱት ወይም እርካታ ያልተሰማቸው የአፍሪካ ሚንስትሮችና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ‹‹ የፓን አፍሪካ የምጣኔ ሀብት እድገት አቅድ ›› ለማውጣት( ማዘጋጀት) ተገደው ነበር፡፡ (draft a pan-African plan of economic development

ይህም ብቻ አልነበረም፡፡ የአፍሪካ  እድገት እውን ለማድረግ ሲሉ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 1979 ግድም ‹‹ የሞኖሮቪያ መግለጫ ›› በተሰኘ ሰነድ የአፍሪካ አንድነት አባል ሀገራት ከአፍሪካ ህዝብ ጋር የሚጣጣም የአፍሪካን የወደፊት የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂክ ሰንድ ማውጣታቸውን እናስታውሳለን፡፡

In July 1979, the declaration known as the “Monrovia Declaration of Commitment of the Heads of States and Governments of the OAU” indicated the future strategy of economic development of the continent to meet the needs of the African people.

ከዚህ ባሻግር የሌጎስ የእቀድ ድርጊት ( እ.ኤ.አ. 1980- 2000) በማውጣት አፍሪካውያን በራሳቸው ተማምነው የምጣኔ ሀብት እና የማህበራ እድገትን ለማስመዝገብ ጥረትም ተደርጎ ነበር፡፡

The Lagos Plan of Action for the economic development of Africa, 1980-200 (OAU, 1979) is based on self-confidence in one’s power to advance economic and social developments

በሌጎሱ የእቅድ ድርጊት ውይይት ላይ ተካፋይ የነበሩት የአፍሪካ መሪዎች ሁሉ አፍሪካን ከድህነት አዘቅት ጎትቶ ለማውጣት ይህ መልካም አጋጣሚ እንደነበር መግባባት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ የአፍሪካ ሀገሮች የምጣኔ ሀብት እድገት ለማስመዝገብ ከፈለጉ በሌላው አለም በምእራቡም ሆነ በምስራቁ አለም ሀብታም ሀገራት የምጣኔ ሀብት ጠበብት መመራት የለባቸውም፡፡

የሌጎሱ የድርጊት አቅድ አውጪዎች  የካፒታሊስቱ አለም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በዋነኝነት ተደራሽነታቸው በትላልቅ ከተሞች ለሚኖረው ማህበረሰብ ነው የሚል እምነት ነበራቸው፡፡ ስለሆነም የካፒታሊሰት ገበያ መር ኢኮኖሚ የአፍሪካን ህዝብ ፍላጎትና የምጣኔ ሀብት ችግር ባማከለ መልኩ መሆን ይገባዋል፡፡ ለአብነት ያህል የአፍሪካን ህዝብ መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት በሚያስችል መልኩ ማለትም ተመጣጣኝ ምግብ ለማግኘት ይረዳ ዘንድ፣የንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ዘመናዊ የመጸዳጃ ቤት ለህብረተሰቡ ለመስራት፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የጤና አገልግሎትና ትምህርትን ለማስፋፋት በሚረዳ መልኩ የምጣኔ ሀብት አቅድ መውጣት አለበት የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ የአፍሪካ ህዝብን መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችል መልኩ ነበር የሌጎሱ የድርጊት እቅድ በአፍሪካውን የምጣኔ ሀብት ጠበብት የወጣው፡፡ በግዜው የተዘረዘሩትን የአፍሪካውያን መሰረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተገን አድርጎ ያልወጣ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ የአፍሪካን የምጣኔ ሀብት ችግር መፍታት አይቻለውም የሚል እምነት በግዜው የአፍሪካ መሪዎች ታምኖበት ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና አብዛኛው የአፍሪካ ህዝብ አሁን ድረስ በመሰረታዊ የምጣኔ ሀብት ችግር ተተብትቦ ይገኛል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የአለም አራጣ አበዳሪዎች የሚፈጥሩት ውስብስብ ጫና ነው፡፡ የአለም የገንዘብ ተቋማት የሆኑት የአለም ባንክ እና የአለም የገንዘብ ድርጅት ሌሎች ደሃ ሀገሮች በተለይም የአፍሪካ ሀገራት ራሳቸውን ችለው የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ በማውጣት ገቢራዊ እንዳያደርጉ የተለያዩ መሰናክሎችን ይደቅናሉ፡፡ ለአፍሪካ የምጣኔ ሀብት እድገት መድህን ሊሆን የሚችለውን የሌጎስ የድርጊት እቅድ ከሽፎ የቀረው በአለም የገንዘብ ተቋማት ሴራ ነበር፡፡ አፍሪካና አፍሪካውያን አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ አልተፈለገም ነበር፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት የራሳቸውን የምጣኔ ሀብት አቅድ በአፍሪካ ላይ መጫን ነው፡፡ ለአብነት ያህል የአለም የገንዘብ ድርጅት፣ የአፍሪካ ሀገራት መንግስታትን በማግባባት ስትራክቸራል አጀስትመንት የተሰኘውን የራሱን የኢኮኖሚ አቅድ በአፍሪካ ሀገራት ላይ ጭኗል፡፡

, the IMF could easily convince African governments with its plan, known as the Structural Adjustment Program (SAP)

እንደ ዶክተር በፍቃዱ በቀለ የመሰሉ ስመጥር አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ጠበብት በጥናት እንደደረሱበት ከሆነ የአለም የገንዘብ ድርጅት በአፍሪካ ላይ የጫነው የኢኮኖሚ እቅድ በምእራቡም ሆነ በተባበረችው አሜሪካ የምጣኔ ሀብት ታሪክ ውስጥ ገቢራዊ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይህ የዋሽንግተን ስምምነት በመባል የሚታወቅ የአለሙ የገንዘብ ድርጅት የምጣኔ ሀብት አቅድ በመጀመሪያ የታወጀው የታላቋ ብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር  ማርጋሪት ታቸር እና የተባበረችው አሜሪካ ፕሬዜዴንት በነበሩት ሚስትር ሬጋን ነበር፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ዋነኛ ፍላጎት ደግሞ የራሳቸውን የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለሟሟላት ካፒታሊስት የገበያ መርህ ወሳኝ ነው የሚል እምነት ስለነበራቸው ነው፡፡ በአጭሩ ለሌሎች ሀገራት በተለይም ለአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት ሊረዳ የማይችል ሆኖም ግን የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም ዝንተ አለም ለማስጠበቅ ያለመ ነበር፡፡ (ፍላጎታቸው፡፡) ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበረችው አሜሪካ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑትና የዚሁ የምጣኔ ሀብት አመንጪው ሚልተን ፍሪድማን ( Milton Freedman )  ይህ ገበያመር የካፒታሊስት ምጣኔ ሀብት ፖሊሲ በአግባቡ ተይዞ ገቢራዊ መሆን ከቻለ እድገትን ሊያመጣ ያስችለዋል፡፡

እንደ ኒኦሊብራል የምጣኔ ሀብት የጥናት ውጤት ከሆነ የአንድ ሀገር መንግስት በገበያ ውስጥ እጁን የሚያስገባ ከሆነ ለአንድ ሀገር እድገት ጠቃሚ የሆነው የገበያመር ኢኮኖሚ እድገት ይጎዳል፡፡ በእነርሱ የምጣኔ ሀብት አስተምህሮ መንግስት ከገበያ ውስጥ መውጣት አለበት፡፡ ከዚሁ ባሻግር እነኚሁ የካፒታሊስት ሀገራት አራጣ አበዳሪዎች ሁሉም ሀገራት ከታሪካቸው፣ ባህላቸው፣ ከማህበራዊ ልምዳቸው፣ ከስነልቦናቸው ውጪ ወይም ባልተጣጣመ መልኩም ቢሆን ይህንኑ የኒኦሊብራል ምጣኔ ሀብት ፖሊስን ገቢራ ማድረግ አለባቸው የሚል እምነት አላቸው፡፡

በአጭሩ የአፍሪካ መንግስታት ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በብድር ስም እርዳታ ማግኘት ከፈለጉ የአለም የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ የሚያስቀምጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ግድ ይላቸዋል፡፡

If African governments want to receive financial support in the form of loans from international institutions, they must accept the preconditions of the IMF and the WB.

ቻሁድ (Chahoud, 1987) የተባለ ምሁር እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1987 እንደጸፋው ከሆነ የአለም ገንዘብ ድርጀት ቅድመ ሁኔታ ቀላል ሲሆን፣ ሆኖም ግን ይሁንና ገቢራዊ ከተደረገ በኋላ ከፍተኛ አደጋን የሚጋብዝ ነው፡፡ አንድን ሀገር ዝንተ አለም የአለም አራጣ አባዳሪዎች ጥገት ላም የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአለም የገንዘብ ድርጅት ገንዘብ የሚበደሩ ወይም አርዳታ የሚያገኙ ሀገራት ሁሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ድርጅቶቻቸውን ለግል ባለሀብቶች መቸብቸብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ወይም ማናቸውንም በመንግስት የሚተዳደሩ ፋብሪካዎችን፣ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ አየርመንገድ፣ቴሌ፣ መብራት ሐይል ወዘተ ወደ ድንበር ዘለል የውጪ ካምፓኒዎች ማስተላለፍን ሊጨምር ይችላል፡፡ ቻሁድ በእንግሊዝኛ የጻፈው የበለጠ ገላጭ በመሆኑ እንደወረደ ጠቅሼዋለሁ፡፡ 

. The premises of the IMF known as “conditionalities” (Chahoud, 1987), are simple but have devastating effects if they are applied. Countries that want to borrow must privatize state-owned enterprises

ከዚህ ባሻግር የተባዳሪ ሀገራትን የመገበያያ ገንዘብ ከአሜሪካን ዶላር አኳያ ዋጋው ዝቅ እንዲል ያስገድዳሉ፡፡ እንደ አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና የአለም ባንክ ምልከታ ወይም ጥናት ከሆነ የአንድ ተበዳሪ ሀገር የመገበያያ ገንዘብ ዋጋ በቀነሰ ቁጥር ሀገራት ወደ ውጪ ሀገር በተወዳዳሪነት የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለመላክ ይቸገራሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እነኚሁ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለምግብ፣ ለጤና አገልግሎትና ለሌላ መሰል መሰረታዊ የሰው ልጆች ፍላጎቶች ሀገራት የሚሰጡትን ድጎማ እንዲቀንሱ ወይም ፈጽሞ እንዲያቆሙ ማስገደድ ፣ እንዲሁም  ገበያው ለውስጥም ሆነ ለውጪ ባለወረቶች ነጻ መሆን እንደ አለበት፣ በተለይም ለውጪ ሀገር ድንበር ዘለል ካምፓኒዎች አመቺ ሁኔታዎች እንዲፈጠር ማድረግ የአለም የገንዘብ ተቋማት ቋሚ ፖሊሲ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ እንደ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የምጣኔ ሀብት ጠበብት ምክረ ሃሳብ ከሆነ፣ ሀገራት የአለም አራጣ አበዳሪዎችን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ በትክክለኛው መንገድ ከተጠቀሙበት የምጣኔ ሀብት እድገታቸው ይጎመራል፡፡ ድህነትና አርዛትን መክላት ያስችላቸዋል፡፡የኑሮ እድገት ይጨምራል፡፡ የማናቸውም የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ በሁለት እግሩ መቆም ይቻለዋል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ከአለም የገንዘብ ተቋማት ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መልኩ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት አመርቂ አይደለም፡፡ ዛሬም አፍሪካ በኑሮ እድገት አይታይባትም፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን በችጋር ይሰቃያሉ፡፡ አብዝሃው የአፍሪካ ወጣት ስራ የለውም፡፡ ያለ ሆስፒታል አገልግሎት የሚወልዱ እናቶች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ አፍሪካ ዛሬም ከእርዳታ ነጻ አልወጣችም፡፡ አብዛኛውን ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ቁሶችን የምታስገባው ከምእራቡ አለም፣ ከቻይና እና ከኤሽያ ሀገራት በግዚና እርዳታ ነው፡፡ በአጭሩ የአለም አራጣ አበዳሪዎች የምጣኔ ሀብት አቅድ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ያመጣው ፋይዳ አጥጋቢ አይደለም፡፡ ነገሩ ላም አለኝ በሰማይ…….መሆኑ ነው፡፡

በነገራችን ላይ በአንድ አካባቢ ወይም ሀገር( አህጉር) የገበያ መር ወይም ካፒታሊስት ኢኮኖሚ  በሁሉም አቅጣጫ የምጣኔ ሀብት እድገት እንዲያመጣ  ከተፈለገ የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት እንዳለባቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ምክረ ሀሳብ ያርባሉ፡፡

  • ብቃት እና ጥንካሬ የተላበሱ፣ እንዲሁም ነጻነታቸውን ያስከበሩ የዲሞክራቲክ ተቋማት መገንባት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው፡፡
  • የስራ ክፍፍል በፍትህና ህግ መሰረት ላይ መቆም አለበት
  •  በእቅድ ላይ የተመሰረቱ፣ የተደራጁ ከተሞች መገንባት፤ የሚመጋገቡ ከተሞች ለኢኮኖሚ እድገት ፈር ቀዳጅ ናቸው፡፡
  • ማናቸውም የመገናኛ አውታሮች መገንባት ለገበያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ናቸው፡፡

ከላይ የጠቀስኩትን ምክረ ሀሳቦች ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እድገት ጠቃሚ ግብአቶች ፊልድማን፣ ሀዲሚካኤል እና ሹምፕተር የተባሉ ምሁራን በጥናት ወረቀታቸው ላይ አስፍረውታል፡፡ እንደሚከተለው አሰፍሬዋለሁ፡፡

 As a matter of fact, for the development of a coherent economy that can expand in all directions, efficient and democratic institutions, an evolving division of labor, well-planned and organized cities, all types of infrastructures are prerequisites for a market or a capitalistic economic system. (Feldman, & Hadjimichael, 2016, Schumpeter, 1993

ሆኖም ግን ይሁንና የአለም አራጣ አበዳሪዎች ( የአለም ባንክና የአለም የገንዘብ ድርጅት) የገበያመር ኢኮኖሚ የአዳጊ ሀገራትን ኢኮኖሚ እንዲገነባ ወይም እንዲያሳድግ በሚችል መልኩ ገቢራዊ እንዲሆን ፍላጎታቸው አይደለም፡፡ በአጭሩ ከላይ የተጠቀሱት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ያነሷቸው ምክረ ሃሳቦች ( የገበያ መር ኢኮኖሚ  በአንድ ሀገር ገቢራዊ ከመሆኑ በፊት ማለቴ ነው) ስለመሟላታቸው ወይም አለመሟላታቸው በተመለከተ የሚደማ ልብ የላቸውም፡፡ እነርሱ ምንግዜም ቢሆን የሚያስቡት እና ገቢራዊ የሚየደርጉት የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ የምእራባውያንን  ኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስጠብቅ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

በነገራችን ላይ አንዳንድ ይሀንኑ የምእራባውያን ገበያ መር ኢኮኖሚ ፖሊሲ በጥልቀት ያጠኑ

የምጣኔ ሀብት ጠበብት የምእራቡ አለም በአዳጊ ሀገራት ላይ ገቢራዊ ያደረገውን የምጣኔ ሀብት 

ፖሊሲ “Shock Doctrineበሚል ስያሜ ይጠሩታል፡፡

እንደ ኬሊን (Klein, 2001) የመሳሰሉ ከምእራቡ አለም የምጣኔ ሀብት ጠበብት የተለየ 

የኢኮኖሚ ጥናት ንድፈ ሃሳብ የሚያራምዱ ምሁራን በጥናታቸው እንደደረሱበት ከሆነ የገበያ

የገበያ መር ኢኮኖሚ በአፍሪካ አህጉር በአለም ባንክና የገንዘብ ድርጅት ገቢራዊ ሲደረግ በተሳሳተ 

መንገድ ወይም ምእራባውያን አበዳሪ ሀገራትን በሚጠቅም መልኩ  እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡

ከዚህም እልፍ በማለት የኒኦሊብራል ኢኮኖሚ ገቢራዊ በሆነባቸው ሀገራት ሁሉ የኢኮኖሚ

አለመረጋጋትን እንደፈጠረ፣የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም እንዳላስቻለ፣

በአንድ ሀገር የሚገኘውን ብሔራዊ ኬክ እኩል ለዜጎች ማካፈል እንዳልተቻለ ወዘተ 

በጥናት ወረቀታቸው ላይ ያስቀመጡት መራር ሀቅ ነው፡፡ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ

የአለም የገንዘብ ድርጅትና የአለም ባንክ በአፍሪካ የተገበሩት የገበያ መር ፖሊሲ አፍሪካ

የጥሬ ሀብትና የእርሻ ውጤቶች አቅራቢ እንድትሆን፣ እነርሱ ደግሞ የኢንዱስትሪ ውጤቶች

አቅራቢ እንዲሆኑ ያስቻለ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አፍሪካ የእነርሱ የኢኮኖሚ ጥገኛ እድትሆን 

ያስቻለ መሰሪ እቅዳቸው ነው፡፡ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት 

የህዝባቸውን የምጣኔ ሀብት እደገት ባስጠበቀ መልኩ የምጣኔ ሀብት ስርአት ለመዘርጋት 

ቢሞክሩም እነርሱም ቢሆኑ በአለም የገንዘብ ተቋማት ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡ ስለሆነም 

በርካታ የምጣኔ ሀብት ጠበብት እንደሚስማሙበት ከሆነ የጥሬ ሀብትና እርሻ ውጤቶችን 

ወደ ኢንዱስትሪ ምርት ሳይለወጡ ወደ ውጭ ሀገራት መላክ ብቻውን ፈጣን የኢኮኖሚ 

እድገትን አያስገኝም፡፡ ለአብነት ያህል ቡና ለጀርመን የምትልከው ኢትዮጵያ፣ ሰሊጥ ለቻይና 

የምትልከው ኢትዮጵያ፣ ሁለቱም ሀገራት፣ ሁለቱንም የእርሻ ውጤቶች ወደ ኢንዱስትሪ ምርት 

ቀይረው ገቢ ከሚያገኙት ሀገራት አንጻር ያላትን የኢኮኖሚ ጥቅም በተመለከተ ስላለው የገቢ 

ልዩነት ማለቴ ነው ለአንባቢው ትቼዋለሁ፡፡

.ሬነርት  (Reinert, 2007) የተባለ የምጣኔ ሀብት ሊቅ በጥናቱ እንደደረሰበት ከሆነ አንዲት 

በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ሀገር ያላትን የተፈጥሮ ጥሬ ሀብት በቀጥታ ወደ ውጭ ሀገር 

ለሽያጭ የምትልክ ከሆነ በዛች ሀገር ላይ የገበያ እጥረት ይከሰታል፡፡ ወይም ያላት 

የገንዘብ መጠን ይቀንሳል፡፡ ድንበር ዘለል የካፓምፓኒ ባለቤቶች ደግሞ ይሄንን

ይፈልጉታል፡፡ እነርሱ በአንድ ሀገር የሚገኝን የተፈጥሮ ሀብት አውጥተው በቀጥታ ወደ 

ሀገራቸው መላክ ይፈልጋሉ፡፡ በሀገራቸው ኢንዱስትሪ ውስጥ የተፈጥሮ ሀብቱ ወደ

ኢንዱስትሪ ምርትነት ከቀየሩ በኋላ መልሰው በውድ ዋጋ ለአፍሪካ ይሸጣሉ፡፡ ለአብነት 

ያህል የካካወ ምርትን ከምእራብ አፍሪካ በተለይም ጋና በገፍ ከገዙ በኋላ ወደ ኢንዱስትሪ

ምርት ለውጠው ለአፍሪካና ለቀሪው አለም እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ ይሸጡታል፡፡

በአጭሩ የተፈጥሮ ጥሬ ሀብትና የእርሻ ምርት ውጤቶችን በቀጥታ ወደ ኢንዱስትሪ ምርትነት

ሳይቀይሩ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ብሔራዊ ሀብትን ለመፍጠር አያስችልም፡፡ ወይም

የውጭ ባለሀብቶች ገብተው መስራት የሚመርጡት አካባቢ የተፈጥሮ ሀብት

ብሄራዊ ሀብት ባልሆነበት አካባቢ ነው፡፡

Foreign investors always prefer to invest in areas where they cannot create true

National wealth

ከዚህ በተጨማሪ ከአለም የገንዘብ አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ መበደር ጥገኝነትን ይፈጥራል

የሚል እምነት ስላላቸው ገንዘብ ለአፍሪካ ሀገራት በገፍ ያበድራሉ፡፡

ከምእራቡ አለም ተመርተው በሚመጡ የኢንዱስትሪ ምርቶች መማረክና ሸማች መሆን፣ 

የማይታይ መጠነ ሰፊ የስራ እጥ ቁጥር መጨመር፣ ሀግወጥ ንግድ መስፋፋት፣የድሃ መንደር

በአስደንጋጭ ሁኔታ መስፋፋት፣ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ ደግሞ ሀብት በጥቂት ሰዎች

እጅ ውስጥ መውደቅ ወዘተ የተከሰቱት የምእራብ ሀገራት የመዋቅር እድገት ፖሊሲ

ያመጣብን ጣጣ እንደሆነ (Bandow, & Vásquez, 1994) የተባሉ የምጣኔ ሀብት ምሁራን

ይከራከራሉ፡፡

ኢትዮጵያዊው የምጣኔ ሀብት ምሁር ዶክተር በፍቃዱ በቀለ በበኩላቸው ‹‹ በብዙ የአፍሪካ

ሀገራት ያለው የገበያ ሁነታ ጤናማ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የገበያው ሁኔታ ከሳይንስና 

ቴክኖሎጂ በተጻራሪ የቆመ ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ከሳይንስና ቴክኖሎጂ አኳያ ተጻራሪ

የሆነውን የምእራቡ አለምን ገበያ መር ኢኮኖሚን ዝም ብሎ አገበስብሶ በአፍሪካ ገቢራዊ

ማድረጉ አግባብ እንዳልነበረ ዶክተር በፍቃዱ ምክረ ሃሳባቸውን ያቀርባሉ፡፡

ዶክተር ባቀረቡት ጥናት መሰረት በአፍሪካ ገቢራዊ እንዲሆኑ የተደረጉት የሚከተሉት

ፕሮግራሞች አፍሪካ የምትገኝበትን ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ሁኔታ አለወጡትም

  1. የሚሊንየሙ የልማት ግብ (the Millennium Development Goals 2015(MDG) (UN, 2000)
  2. የብይነ መንግስታቱ ዘለቄታዊ የልማት ግብ (UN Sustainable Development Goals (UN, 2015) )

እጅግ ውብ የሚመስለው እና አማላዩ የምእራባውያን እቅድ ወረቀት ላይ ብቻ ቀርቷል፡፡ እንዚህ ሁሉ ፕሮግራሞች ገቢራዊ መሆን የማይችሉ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የውጭ ሀገር ምሁራን ወይም አክስፐርቶች  በአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ያሉትን እውነተኛ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎችን ማንበብ ስለማይችሉ ይመስለኛል፡፡ ከተሳሳትኩ ልታረም ዝግጁ ነኝ፡፡ ከዚህ ባሻግር ሁሉም የኢኮኖሚ እድገት ፕሮግራም አቅዶች በእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገራት ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ውይይት አልተደረገበትም ወይም ውይይትና ክርክር እንዲደረግበት አልተደረገም፡፡ ስለሆነም የአለም አራጣ አባዳሪዎች ( የአለም ባንክና የአለም የገንዘብ ድርጅት ) ሃሳብ የአፍሪካን ሀገራት እውነታ አይመሰክርም ወይም አያሳይም ብሎ መደምደም የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም የችጋርና የኢኮኖሚ ውድቀት መሰረታዊ ምክንያቶችን ሳንረዳ ፣ ሳንወያይ፣ በበቂ ሁኔታ ሳንተነትን እንደው ዝም ብሎ ከሌላ አካባቢ የመጣን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሳያላምጡና በሀገር ወዳድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ሳያስጠኑ ገቢራዊ ማድረጉ ችግሩን ያባብሰዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

አመቺ የልማት ሞዴል መፈለግ

ከብዙ ግዜ ብስጭት ወይም ተስፋ መቁረጥ በኋላ የአፍሪካ ሀገሮች የራሳቸውን መንገድ ለመፈለግ ግዴታ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ‹‹ አዲሱ የአፍሪካውያን መነሳሳት ›› እቅድ አወጡ፡፡ (The plan, known as the “New African Initiative ) በነገራችን ላይ ይህ አዲሱ የአፍሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ እቅድ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 2001 በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ውይይት ተደርጎበት ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የደቡብ አፍሪካዊት ሪፐብሊክ ፕሬዜዴንት የነበሩት ሚስተር ታቦምቤኪ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ተሃድሶ ልማት እቅድን እንዲቀበሉ የማግባባት ስራ አከናውነው ነበር፡፡

ሎው የተባለ ምሁር እንደገለጸው ከሆነ ከላይ የተጠቀሰው የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ አቅድ አዲስ ባይሆንም የአፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ደረጃ ለማሳደግ ያስችላል፡፡

በነገራችን ላይ የቀድሞ የአፍሪካ ልጆች የነበሩት የጋናው ክዋሚ ንክሩሃማ፣የታንዛኒያው ፕሬዜዴንት ጁሊየስ ኒሬሬ ( ሙዋሊሙ)፣ ፕሬዜዴንት ኬኔት ካውንዳ ወዘተ ወዘተ በየራሳቸው ሀገራት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመስርተው የራሳቸውን ሀገራት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለመንደፍ ሞክረው እንደነበር ታሪክ ያስተምረናል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች የተነሳ ታላቅ ህልማቸው ህልም ሆኖ ቀርቶባቸዋል፡፡ የመጀመሪያው የቅኝ ገዢዎች ውርዴ የሆነው እና እጅጉን ስር የሰደደው የፖለቲካና የመንግስት መዋቅር ህልማቸውን አምክኖባቸዋል፡፡ በአጭሩ የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኝ የነበሩት የሶስቱ ሀገራት መሪዎች የኢኮኖሚ እቅድ መክኖ የቀረው በቅኝ ገዚዎች ተንኮልና ሴራ ነበር ማለት ይቻላል፡፡  ሁለተኛው ተጨማሪ ምክንያት ደግሞ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ የጠከሰተው የአለም የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ሌላው እንቅፋት ነበር ብሎ መደምደም የሚቻል ይመስለኛል፡፡ በነገራችን ላይ የተባበረችው አሜሪካ ጥቅም አስጠባቂ የሁኑት አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የሆኑት የአለም የገንዘብ ድርጅትና የአለም ባንክ በግዜው የአፍሪካ መሪዎች ላወጡት እጅግ ጠቃሚ የምጣኔ ሀብት አቅድ ገቢራዊነት ተባባሪዎች አልነበሩም፡፡

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠርቸ1983 ቴዝላፍ የተባለ ምሁራን ይሄንኑ እውነት የሚረጋግጥ ጽሁፍ  አቅርቧል፡፡ እጠቅሰዋለሁ፡፡

International institutions such as the IMF and the WB, which serve more as an instrument of power for the USA were not helpful in this regard (Tetzlaf, 1983)

 የራሳቸውን የኢኮኖሚ ልማት መንገድ ከተከተሉት እና በአለም ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ከበቁት የኤሽያ ሀገራት ማለትም ደቡብ ኮሪ፣ጃፓን እና ሲንጋፖር ጋር ሲወዳደደሩ የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው መንገድ የኢኮኖሚ ልማት እድገት እንዳያወጡ ደንቃራ ወይም እንቅፋት ሲፈጠርባቸው ቆይተዋል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት በተለይም የፈረንሳይ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑት ዛሬም በቅኝ አገዛዝ ውስጥ እንዳሉ የሚቆጥሯቸው ሞለተው ተርፈዋል፡፡ የመገበያያቸው ገንዘብ የፈረንሳይ ገንዘብ መጠሪያ‹‹ ፍራንክ ›› ነው፡፡ ወደ ዩሮ ለመንደርደርም እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ መራር እውነት መረዳት የምንችለው ቁምነገር ቢኖር የኢኮኖሚ ፖሊሲም ሆነ የመገበያያ ገንዘባቸውን ለመወሰን ነጻ እንዳልሆኑ ነው፡፡ እንደ እነ ዶክተር በፍቃዱ በቀለን የመሰሉ ስመጥር የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች በጥናታቸው እንደደረሱበት ከሆነ በርካታ የምእራብ አፍሪካ ሀገራት ባለወረቶች ገንዘባውን የሚያስቀምጡት በፈረንሳይ ማእከላዊ ባንክ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን ገንዘብ ለራሳቸው ህዝብ በሚጠቅም መልኩ ወይም በህብረተሰባቸው መሰረታዊ ችግሮች ላይ ተመስርተው ኢንዱስትሪ ለማቆም አይፈቀድላቸውም፡፡ በአጭሩ የአፍሪካን ህዘብ መሰረታዊ ችግር ለመፍታት መዋለ ንዋያቸውን የሚያፈሱት አፍሪካዊ ባለወረቶች እጅጉን ጥቂት ናቸው፡፡ በጋና አክራ፣ በናይጄሪ አቡጃ፣ በኬንያ ናይሮቢ፣ በኡጋንዳ ካምፓላ፣ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ወዘተ ወዘተ አውራ ጎዳናዎች ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ይነከራተታሉ፡፡ የሚበሉት የሚልሱት አጥተው ማስቲሽ እና ቤንዚን በጨርቅ አድረገው ሲመጡ ማየት ያማል፡፡ የትኛው አፍሪካዊ ባለወረት ወይም መንግስት ነው መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ የጎዳና ላይ ወጣቶችን ህይወት ለማሻሻል የጣረው፡፡ ለአብነት ያህል በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ላይ እየተንከራተቱ የሚኖሩ ( ኑሮ ከተባለ ማለቴ ነው) ኢትዮጵያዊ ዜጎች ሞልተው ተርፈዋል፡፡ ቁጥራቸው በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨመረ እንጂ አልቀነሰም፡፡ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን የማህበራዊ እድገት በማቋቋም፣ በደርግ ዘመን ደግሞ በዝዋይ የህጻናት አምባ በማቋቋም፣ በስጋ ሜዳ የህጻናት ማሳደጊያ በመቋቋም የጎዳና ህይወትን ለመክላት ጥረት እንደተደረገ አስታውሳለሁ፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ አዲስ አበባ ላይ በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ተገንብተዋል፡፡ ከህንጻዎቹ ግርጌ ወይም ፊትለፊት ቀን የጨለመባቸው ወጣቶች የጸሃይ ንዳድ ሲለበልባቸው ይውላል፡፤ ሌት ደግሞ በቁር ይንዘፈዘፋሉ፡፡ ይህ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ዋና ከተማዎች የሚታይ መራር እውነት ነው፡፡ የምእራባውያን ባለወረቶች በአፍሪካ ምድር ለራሳቸው ገነት ፈጥረው ስለሚኖሩ ለአፍሪካዊው ምንዱባን እና እግልት የሚደማ ልብ የላቸውም፡፡ ለእነርሱ እጅግ በዘመኑ ሆቴሎች ውስጥ ቁጭ ብለው የሚሰሩትን ሰርተው ስለሚሄዱ ለአፍሪካ አጠቃላይ እድገት በምንም አይነት መልኩ ሊቆረቆሩ አይችሉም፡፡

በነገራችን ላይ የአፍሪካ ህዝብ እድገት እጅጉን ፈጣን ነው፡፡ ከዚህ ባሻር አብዛኛው የአፍሪካ ህዝብ በወጣት የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ወጣቱ ትውልድ ደግሞ በተስፋ የተሞላ ነው፡፡ ስለሆነም የአፍሪካን ወጣቶች ፍላጎትና ምኞት የሚያሟላ ሌላ የምጣኔ ሀብት እቅድ ማውጣት ( ማዘጋጀት) ምክንያታዊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለሆነም የአፍሪካን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ‹‹ የአፍሪካ ተሃድሶ ልማት›› እቅድ ሁነኛ መፍትሔ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የገበያ መር ኢኮኖሚን እንደገና በማደስ ወይም በአዲስ መልክ ለማቅረብ መሞከር የአፍሪካን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እንደማያስችል አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ወይም ይከራከራሉ፡፡

የተሃድሶ ጽንሰ ሀሳብ መቀንቀን የተጀመረው እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ከ14ኛው ክ.ዘ. እስከ 16ኛው ክ.ዘ. እንደነበር ታሪክ ያስተምረናል፡፡ የተሃድሶ ጽንሰ ሃሳብ የተገኘው እና የተሰራጨው ከጥንታዊ ግሪክ ክላሲካል እውቀት ማለትም ከጥንታዊት ግሪክ ፍልስፍና፣ሂሳብ፣ሳይንስ፣ስነህንጻ፣ ግጥምና ድራማ እንደነበር ከታሪክ እንማራለን፡፡

The idea of Renaissance had originated in Europe between the 14-16th centuries. The term Renaissance implies to revive and spread the old Greek classics, such as philosophy, mathematics, science, architecture, poetry, and drama as new foundations of social development

በነገራችን በግዜው በበሽታ ወረርሽኝ፣ በጦርነት፣መጥፎ አገዛዝ፣በወግ አጥባቂ የካቶሊክ ሀይማኖት አባቶች ፍዳዋን ታይ ለነበረው አውሮፓ ፣ ኋላ ቀር ለነበረችው አውሮፓ፣ በጨለማ ዘመን ውስጥ ለነበረችው አውሮፓ ሰብዓዊነት ያለው ሞዴል ያስፈልጋት ነበር፡፡ ይሄን ተከትሎ አውሮፓ መሰረቱን በሰብዓዊነት ላይ ያደረገ የኢኮኖሚ ንድፈ ሃሳብ ለማንበር ስልሆነላት ዛሬ ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ ላይ ለመድረስ በቅታለች፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና አፍሪካ እንደ አውሮፓ ሁሉን አቀፍ የሆነ የምጣኔ ሀብት ተሃድሶ ለማንበር አልሆነላትም፡፡ ይህ ማለት ግን አፍሪካ እንዲህ አይነት ሁሉንም ዜጎቿን በሚጠቅም መልኩ የምጣኔ ሀብት አቅድ ማውጣት አይሆንላትም ማለት አይደለም፡፡ እንደ ዶክተር በፍቃዱ ጥናት ውጤት ከሆነ አፍሪካ ህዝቧን ከችጋር ለመገላገል፣ በእድገት ጎዳና ለመጓዝ በትክክለኛ ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ አፍሪካ ሁሉንም ህዝቦች ያማከለ የምጣኔ ሀብት እቅድ ማውጣት የምትችልበት ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ የአፍሪካ ተሃድሶ ሞዴል ሁሉን አቀፍ ሞዴል መሆን እንደሚችል የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡ ምክንያቱም እንዲህ አይነት የምታኔ ሀብት ሞዴል በርካታ ውድቀቶችን ለምሳሌ ያህል አፍሪካ የገጠማትን የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ውድቀቶቿን ወይም ችግሮቿን ለመፍታት ያስችላታል፡፡

እንደ አንዳንድ አፍሪካዊ ኤክስፐርቶች ትርጓሜና ትንተና ከሆነ የአፍሪካውያን የተሃድሶ ልማት አቅድ አፍሪካን ከእንቅልፏ ሊያነቃት የሚያስችላት ነው፡፡ ለአብነት ያህል ባሬል የተባሉ ምሁር በእንግሊዝኛ ቋንቋ ካሰፈሩት የጥናት ወረቀት ላይ የሚከተለውን እጠቅሳለሁ፡፡

(Barell, 2000). Both concepts, namely the “African Renaissance” and “Reawakening Africa”, would be appropriate if they have theoretical and scientific foundations.

በነገራችን ላይ አፍሪካ ለቀሪው አለም የእውቀት ምንጭ እንደነበረች ማስታወሱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ እንደ ፕሮፌሰር Cheikh Anta Diop,ጥናትና ምርምር ውጤት ከሆነ የጥንታዊት  ግሪክ ፈላስፋ የነበሩት ፕላቶ፣ ፓይታጎረስ እና ሌሎች ከግብጽ ነበር፡፡ ( ግብጽ በጥንት ዘመን ስትገዛ የነበረው በጥቁር ፈርኦኖች ነበር፡፡) ይህ በእንዲህ እንዳለ ማርቲን ቤረናል ( እ.ኤ.አ. 1987) በጥናቱ ላይ እንዳረጋገጠው የጥንታዊት ግብጽ እና ግሪክ የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ በተለይም የግሪክ ስልጣኔ መሰረቱ የተጣለው ከጥንታዊት ግብጽ ጋር ከነበራቸው ግንኙነት አኳያ ላይ ተመስርቶ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ‹‹ ጥቁሯ አቴና ›› በተሰኘው መጽሀፉ ላይ በርናል እንደጠቀሰው ከሆነ ግሪክ በአፍሪካዊቷ ግብጽ ተገዝታ ነበር፡፡ ስለሆነም የግሪክ ፍልስፍና፣ሳይንስ፣ አርት( ስነ ስእል)፣ ሂሳብ፣ ወዘተ ስልጣኔ ምንጭ ጥንታዊት ግብጽ ናት ተብሎ ቢጻፍ ስህተት አይመስለኝም፡፡ በሌላ አነጋገር ጥንታዊት ግሪክ ብዙ ስልጣኔዎቿን ያገኘችው ከግብጽ ነበር፡ ስለሆነም የአፍሪካ አህጉር የጥንቱን ስልጣኔ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማሳለጥ ለአፍሪካ እድገት የሚበጅ የምጣኔ ሀብት አቅድ ቢያወጣ ስህተት አይሆንም፡፡ የሰው ልጆች ታሪክ ገና አልተጠናቀቀም፡፡ ስለሆነም በርካታ የምጣኔ ሀብት ጠበብትና ፈላስፋዎች አሁን ድረስ ተለዋጭ የምጣኔ ሀብትና ማህበራዊ ፖሊሲ ማውጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይህን የአፍሪካ ተሃድሶ ልማት አቅድ ማሰብ ደግሞ ስህተት አይደለም፡፡ ፕሮፌሰር Cheikh Anta Diop በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሰፈሩትን ለአስረጂነት አቀርባለሁ፡፡

According to Professor Cheikh Anta Diop, the ancient Greeks such as Plato, Pythagoras, and others had acquired their knowledge in Egypt, then ruled by the Black Pharaohs (Harding & Reinwald, 1990) In his comprehensive work, Martin Bernal (1987) also proves that the ancient Egyptians and the Greeks used to have intimate relations that laid the foundation of the Greek civilization.  In his book “Black Athena”, Bernal claims that Greece was a colony of Black Egypt. It would not be wrong then to recognize Greek philosophy, science, art, mathematics, and others as a further development of the Egyptian civilization. In other words, the Greeks had copied many things from Egypt, and therefore it is not wrong that the continent introduces again its lost legacy by adapting it to the new circumstances.  Since human history has not yet completed, and many economists and philosophers are also convincingly formulating an alternative path of economic and social policy, I think it would not be wrong to rethink and further develop the “African Renaissance.” (Kate, 2017)

ምንም አንኳን ታቦምቤኪና የሃሳበቸው ደጋፊዎች የሆኑ የምጣኔ ሀብት ምሁራን በትክክለኛ ጊዜ ተገቢ የሆነ ጥያቄ በማንሳት፣ የአፍሪካን ህዝብ ፍላጎት ለሟሟላት፣ እንዲሁም መጠነ ሰፊ የሆነውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ ስችላቸው ዘንድ ተለዋጭ የምጣኔ ሀብት እና የማህበራዊ አቅድ ቢያወጡም፣ ገበያ መር የካፒታሊስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሀገሪቱን ስር የሰደደ የኢኮኖሚ ችግር አለመፍታቱ በነቢብም በገቢርም የታወቀ ቢሆንም የኒኦሊብራል ኢኮኖሚ አቀንቃኝ የሆኑ የምእራብ ሀገራት እና የአለም የገንዘብ ተቋማት የምጣኔ ሀብት ኤክስፐርቶች የገበያ መር ኢኮኖሚ አማራጭ የለውም ባይ ናቸው፡፡ በኒኦሊብራል ፖሊሲ መሰረት ፖለቲካ፣ ባህል፣ማህበራዊ ጉዳይና ማህበረሰብ ትኩረት አይሰጣቸውም፡፡ በእነርሱ አስተሳሰብ ሞራል፣ ስነምግባር፣ ባህል፣ የሰዎች ማህበራዊ ግንኙነት እና ፖለቲካ የገበያመር ኢኮኖሚን እድገት ይገታል፡፡ በእነርሱ አስተሳሰብ ሞራል እና ስነምግባር ሳይንሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች አይደሉም ስለሆነም ከሰው ልጆች አይምሮ ውስጥ መጥፋት አለባቸው፡፡ ሞራልና ስነምግባር በገንዘብ አይተመኑም፡፡

እንደ ኒኦሊብራል የምጣኔ ሀብት አቀንቃኞች ስብከት ከሆነ ገበያ መር ኢኮኖሚ መንግስት በምጣኔ እና ኢኮኖሚክ እድገት መሃከል ያለውን ያለመመጣጠን ለማሰተካከል በሚል ጣልቃ መግባት የለበትም፡፡ ምክንያቱም የመንግስት ጣልቃ ገብነት የገበያ መር ተፈጥሮአዊ ህግን ሊያዛባው ይቻለዋል፡፡

ቢኒያሚን አፔልበም የተባሉ የኢኮኖሚክ ጠበብት በቅርቡ ባሰተሙት እና ‹‹ የምጣኔ ሀብት ጠበብት›› በተሰኘው መጽሀፋቸው ላይ እንዳስቀመጡት ከሆነ የገበያመር ኢኮኖሚ ገቢራዊ በማያደርጉ ሀገራት የሚኖሩ ማህበረሰቦች በእጅጉ የምጣኔ ሀብት እድገታቸው ይገታል፡፡

.  The latest book by Binyamin Appelbaum, “The Economists’ Hour,” shows how fatal it becomes for a society when a country is reduced to a mere arena of free-market forces. (Appelbaum, 2019)

በነገራችን ላይ አፍሪካ ለገጠማት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለአብነት ያህል በፖለቲካ፣ ምጣኔ ሀብት፣ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ስነልቦናዊ እና አካበቢያዊ  አንጻር የደረሱ ጉዳቶች የሚመነጩት ለገበያ መር ርእዮት ዓለም ካላቸው የተሳሳተ ግንዛቤ የሚመነጭ ቢሆንም በመሬት ላይ ያለውን እውነታ መርሳት የለብንም፡፡

እንደ እነ ዶክተር በፍቃዱን የመሰሉ ስመጥር አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ጠበብት በደረሱበት ድምዳሜ መሰረት አፍሪካ ላለፉት ስልሳ ( 60) አመታት የምእራባውያን እና የአለም የገንዘብ ተቋማት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ምርምር ቤተ ሙከራ ሆና ቆይታለች፡፡ የአፍሪካ ህዝብ እንደ ሰው አልተቆጠረም፡፡ 

.  Over the last 60 years, the continent was degraded to an experiment field. The people of the continent were not considered as human beings                  የአፍሪካን ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎት በቅጡ ሳያጠኑ በገበያመር ስም የኢኮኖሚ ፖሊሲ ያወጣሉ፡፡ ይህ የምእራባውያንን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚዘጋጀው  የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደግሞ ለአፍሪካ እውነተኛ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት ማምጣት አልተቻለውም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም በምእራቡ አለም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች  የሚዘጋጅ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የአፍሪካን ህዘብ የመፍጠር ( የፈጠራ) ችሎታ የሚገታ ወይም የሚያስተጓጉል ነው፡፡ 

በተለይም ባለፉት 30 ዓመታት የነበሩት አብዛኞቹ የአፍሪካ የፖለቲካ ልሂቃን የአለም የገንዘብ ድርጅትና የአለም ባንክ እንዲሁም የአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አካላት ያወጡትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ እና ምክር  ለአፍሪካ መሰረታዊ እና አንገብጋቢ ችግር መፍትሄ ይሆናል ወይም አይሆንም የሚሉ ቁምነገሮችን  ለአብነት ያህል የአፍሪካን ህዝብ የምግብ ፍላጎት፣ የንጹኅ ውሃ አቅርቦት፣ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ መኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ማስቻሉን በተመለከተ የትምህርትና የጤና አቅርቦትን በበቂ ሁኔታ ማዳረስ ስለመቻሉ  ወዘተ ሳይመረምሩ፣ገቢራዊ እንዳደረጉ በርካታ ገለልተኛ አቋም ያላቸው አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ጠበብት የሚስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡

የዚህ አይነት የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ ውጤቱ ደግሞ እንደታየው እጅግ መጠነ ሰፊ ቁጥር ያለውን ህዝብ ለችጋር ዳርጓል፡፡ የአፍሪካን ሀብት አባክኗል፡፡ ተገቢ ላልሆነ ብድር ዳርጓል፣ አፍሪካን የሌሎች ጥገኛ አድርጓታል፡፡ ምንም እንኳን ይሁንና አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት እጅግ የታደለች አህጉር ብትሆንም፣ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ወደ ቀሪው አለም በመላክ በብዙ ቢሊዮን የሚገመት የአሜሪካን  ዶላር  ገቢ ብታገኝም ዛሬም ከአለም ባንክና ከአለም የገንዘብ ድርጅት ገንዘብ ትበደራለች፡፡ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ ደግሞ በብዙ ቢሊዮን የሚገመት የአሜሪካ ዶላር ከአፍሪካ አህጉር ወደ ቀሪው አለም በተለይም ወደ ምእራቡ አለም ባንኮች እንደሚላክ ጥናቶች ያሳያሉ ፡፡ ስለሆነም የአፍሪካ ምሁራን በመንግስታቶቻው ላይ ተጽእኖ ለማድረግ የሞራል ሃላፊነት ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ የአፍሪካ ምሁራን የአብዛኛውን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ሊያሟላ የሚያስችል እቅድ አውጥተው ለሀገራቸው መንግስት ማስረከብ፣ ለገቢራዊነቱም መሟገት፣ መታገል አለባቸው ብዬ አስባለሁ፡:

ከዚህ ባሻግርር የአፍሪካ የምጣኔ ሀብት ተጠባቢዎች ‹‹ የምጣኔ ሀብት ልማት›› ጽንሰ ሃሳብ ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙን በትክክል ማስቀመጥ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ (It is also important to define the meaning economic development ) ምንም አይነት ግልጽ ሃሳብ ሳይኖረን፣ የኢኮኖሚክ ፖሊሲን የንድፈሃሳብና የሳይንሳዊ መሰረቱን በተመለከተ ውይይት ሳይደረግበት ወዘተ ወዘተ እውነተኛ የኢኮኖሚክ ሞዴል ማዘጋጀት በፍጹም አዳጋች ነው፡፡

ስለሆንም የምጣኔ ሀብት እድገት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መዳረስ ያለበት ሂደት አንደሆነ ሁላችንም ግንዛቤ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ የኢኮኖሚክ እድገት ፖሊሲ ሃሳብ መመንጨት ያለበት ከሀገር ውስጥ ከህብረተሰቡ መሰረታዊ ችግር በመነሳት ቢሆን ይመረጣል፡፡ የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ እንዲሉ የአንድ ሀገር ህዝብ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር ሊፈታ የሚቻለው በዛች ሀገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ወዘተ ወዘተ ችግሮች የተመሰረተ ሲሆን ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ምድር ዘላቂ እና ቀጣይነት ያለው የምጣኔ ሀብት እድገት እውን እንዲሆን ከተፈለገ በቅድሚያና በዋነኝነት የአፍሪካ ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎት  ጥያቄዎች መሟላት አለባቸው፡፡ ከዚህ ባሻግር የምጣኔ ሀብት እድገት ከማህበራዊና ባህላዊ እድገት ተነጥሎ መታየት የለበትም፡፡

የልማት እቅድ ለኤክስፐርቶች ብቻ መተው የለበትም፡፡ እውነተኛ የምጣኔ ሀብት የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው፡፡ ሕብረተሰቡን በንቃትና በስፋት ለማሳተፍ ያስችል ዘንድ ትምህርት ወሳኝነት ስለአለው ሕብረተሰቡን በስፋት የእውቀት ተቋዳሽ ማድረጉ እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ የሕብረተሰቡ ንቃተ ህሊና በዳበረ ቁጥር፣ በትምህርት ሲገፋ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ተሳታፊ ይሆና፡፡ ስለሆነም መንፈሳዊና ቁሳዊ ልማቶች እውን መሆን ይሆናሉ፡፡ በውጤቱም የአፍሪካ ተሃድሶ እውን ይሆናል፡፡ እዚች ላይ ኡብአንቱ( Ubuntu) የተሰኘውን የአፍሪካን ጥንታዊ ፍልስፍና መጥቀሱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡ ‹‹ ዋጋ ያለቸው ነገሮች ለአብነት ያህል ሀዘኔታ( ለሌላው ማዘን ወይም ፍቅር ማሳየት)፣ compassion እራስን ብቻ አለመውደድ፣ሌላውንም እንደ ራስ አድርጎ መውደድ፣ selflessness የተቸገሩትን መርዳት ( charity )አጋርነት (solidarity) ወዘተ ወዘተ በጎ ተግባራትን ማድረግ ለአፍሪካ የተሃድሶ እድገት እንደ ቅድመ ሁኔታዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

የጽሑፍ ምንጭ፡- ዶክተር በፍቃዱ በቀለ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ

ዶክተር በፍቀዱ በቀለ ማን ናቸው ?

ነዋሪነታቸውን ጀርመን በርሊን ያደረጉት ዶክተር በፍቃዱ በቀለ በልማታዊ ኢኮኖሚክስ የዶክሬት ድግሪያቸውን የጨበጡ ሲሆን፣ በዩነቨርስቲ መምህርነት አገልግለዋል፡፡ ከዚህ ባሻግር  በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴሚናሮችን ሰጥተዋል፡፡ አሁን ድረስ በልማታዊ ኢኮኖሚክስ፣ ስለ ልማት ትርጉም፣ ስለ አለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት ሁኔታ፣ስለ ካፒታሊዝም ጽንስ ሃሳብ፣ስለ ግሎባላይዜሽ ሂደት እና ግሎባላይዜሽ በአፍሪካ ሀገራት ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ቅርጽ ላይ ስላስከተለው ጫና ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ አጅግ ብዙ መጠነ ሰፊ ጽሁፎችን አሳትመዋል፡፡ ከዚህ ባሻግር የበርካታ መጽፍት ደራሲ ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻግር ከቅርብ ግዜ በፊት‹‹, “African Predicaments and the Method of solving them effectively ›› የተሰኘ መጽሐፍ ለህትመት አብቅተዋል፡፡ ዶክተር በፍቃዱ አሁን ካለው የአለም የምጣኔ ሀብት አስተሳሰብ ወጣ ያለ አስተሳሰብ በማረመድ የሚታወቁ ጎምቱ የምጣኔ ሀብት ጠበብት ናቸው፡፡

Filed in: Amharic