>
5:26 pm - Friday September 15, 1950

"ሰብዓዊነትና ፍቅር፤ ለመተከልና ለትግራይ!!!" (ጽዮን አበበ)

“ሰብዓዊነትና ፍቅር፤ ለመተከልና ለትግራይ!!!”

ጽዮን አበበ

በመተከልና በትግራይ ክልል ችግር ላይ ላሉ ዜጎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡
* ” ችግሩ ይመለከተኛል በማለት የአንዱን ህመም መታመም፤ የሌላው ምግብ መጠማት የኔም ነው ልንል  ይገባል ፤ ሁሉም በቻለው አቅም ሊረዳ ይገባል!”
አርቲስት ታማኝ በየነ
“ሰብዓዊነትና ፍቅር፤ ለመተከልና ለትግራይ”በሚል መልዕክት የድጋፍ ማሰባሰብ መርኃ ግብር ተጀመሯል።
በግሎባል አልያንስ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ጥምረት፣ የኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞችና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች ማኅበር ፣ የመተከልና ትግራይ እርዳታ አሰባሳቢ በጎ ፈቃደኞች እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በጋራ መላው ኢትዮጵያዊ በመተከልና በትግራይ ችግር ላይ ለወደቁ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ በንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ስም በተከፈተው የአካውንት ቁጥር 10003277016559 ላይ ገቢ እንዲያደርጉ ጥምረቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የግሎባል አሊያንስ ሰብሳቢና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ ችግሩ ይመለከተኛል በማለት የአንዱን ህመም መታመም ይገባል ብሏል፡፡ ሁሉም በቻለው አቅም ሊረዳ እንደሚገባ ጠይቋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ – ከአዲስ አበባ
Filed in: Amharic