>
5:13 pm - Friday April 19, 9022

እነ እስክንድ ነጋ ጉዳያቸው ሳይታይ  ለየካቲት 8 ተቀጠሩ .... !!! (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ)

እነ እስክንድ ነጋ ጉዳያቸው ሳይታይ  ለየካቲት 8 ተቀጠሩ …. !!!

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

 የእነ እስክንድር ነጋ ጠበቆች ተከሳሾቹ ባልተገኙበትና ሕግ ተኮር ግልፅ የአዳራሽ ውስጥ ክርክር በማይደረግበት ችሎት ደብዳቤ ለማመላለስ መቅረባቸው ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸዋል…!
በግፍ እስር ላይ የሚገኙትን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ጉዳይ የሚዳኘው ሰበር ሰሚ ችሎት አዳራሽ ውስጥ በግልፅ መደረጉ ቀርቶ ወደ ደብዴቤ ልውውጥ ተቀይሯል። የህሊና እስረኞች በግልፅ ችሎት እንዲቀርቡ የጠየቁ ቢሆንም ፖለቲካዊው ፍርድ ቤት አልተቀበለውም።
በመሆኑም የደብዳቤ ችሎቱ ዛሬ የካቲት አምስት ቀን 2013 ዓ.ም. ተጀምሯል። ይሁን እንጂ በግልፅ ችሎት እስካልተደረገ ድረስ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ የእነ እስክንድር ነጋ ጠበቆች አስታውቀዋል። ተከሳሾቹ ባልተገኙበትና ሕግ ተኮር ግልፅ የአዳራሽ ውስጥ ክርክር በማይደረግበት ችሎት ደብዳቤ ለማመላለስ መቅረባቸው ተገቢ እንዳልሆነም አብራርተዋል።
ዳኞች በግልፅ ያልተሰየሙበት የፅህፈት ቤት ችሎቱ ለደብዳቤው የመልስ መልስ ለመስጠት ለፊታችን የካቲት ስምንት ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በዛሬው ችሎት ምስክሮቹ በግልፅ ችሎት ስለመቅረብ አለመቅረባቸው ሰበር ሰሚ ችሎቱ ብይን እንደሚሰጥ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ቀጠሮው አልተከበረም።
Filed in: Amharic