ማፈር ደህና ሰንብት ማለት አሁን ነው!
አቻምየለህ ታምሩ
ባለፉት 27 ዓመታት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ምድር በአማራ እናቶች፣ ሕጻናትና ሴቶች ላይ ሲፈጸም የኖረው ዘግናኝ የአስገድዶ መድፈር አረመኔያዊ ወንጀል ሕወሓት አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋትና በአማራ ላይ ያለውጥ ጥላቻ ለማሳየት ሲጠቀምባቸው ከኖሩት የፖለቲካ መሳሪያዎች መካከል አንዱ ነበር። አስገድዶ መድፈር በሰው ልጅ ላይ ከሚፈጸሙ በጣም ዘግናኝ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ቢሆንም ቅሉ ባለፉት 27 ዓመታት ግን በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ምድር በአማራ እናቶች፣ ሕጻናትና ሴቶች ላይ ሕጋዊ ተደርጎ በእቅድ ሲፈጸመ የኖረ አስነዋሪ ተግባር ነበር።
ባለፉት 27 ዓመታት ሕወሓት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ያሰፈራቸው “ታጋዮች” በየአማራ ተወላጁ ቤት እየሄዱ አባወራውን አባርረው ሚስቱን አስገድደው ሲደፍሩ፤ እያንዳንዱ የሕወሓት ታጋይ እስከ አስር የሚደርሱ የአማራ ሴቶችንና ሕጻናትን አስገድዶ እየደፈረ፣ መሬትና ሀብት ባለበት ደግሞ ባለትዳሮችን በኃይል ከትዳራቸው እንዲፋቱ እያደረገ ወይም አባወራው በማሰርና በመግደል አማወራዋን እየደፈረ ትግሬ ልጅ እንዲወልድና በወረራ በተያዙት አካባቢዎች ነባሩ ሕዝብ እየጠፋ በትግሬ እንዲተካ ሲያደርጉ ነው የኖሩት።
ሕወሓት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት በአማራ እናቶች፣ ሴቶችና ሕጻናት ላይ እንዲፈጸም ሕጋዊ ባደረገው ዘግናኝ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተነግሮ የማያልቅ ጭካኔ ተፈጽሟል፤ ለመስማት የሚዘገንን ሰብዓዊ ቀውስና መከራም ደርሷል። ይህንን ሕጋዊ ተደርጎ ሲፈጸመ የኖረን የተደራጀ ወንጀል ግን እስካሁን በመንግሥትነት የተሰየመው አካልም ይሁን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት በአማራ እናቶች፣ ሴቶችና ሕጻናት ላይ ሕወሓት ሲፈጸመው የኖረው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በተገቢው አኳኋን እንዲጠናና እንዲመረጅ አድርገው የወንጀሉ ፈጻሚዎች ተገቢውን ቅጣት፤ ተጠቂዎቹ ደግሞ ፍትሕና ካሳ እንዲያገኙ አላደረጉም። ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች አገርና መንግሥት አላቸው? ወገን አላቸው?
ባጭሩ ሕወሓት ባለፉት 27 ዓመታት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ምድር በአማራ እናቶች፣ ሕጻናትና ሴቶች ላይ እንዲፈጸም ያደረገው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መጠንና ስፋት በቅርቡ የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የሚታወቅ አይደለም። ከሰሞኑ አስገድዶ መድፈርን እንቃወማለን ሲሉ የምንሰማቸው ያገራችን የመንፈስ ደካሞች ተመጻዳቂነት ግን ያሳስገርመኝ አልቀረም። እነዚህ አስገድዶ መድፈርን እንቃወማለን ሲሉ የምንሰማቸው በመንግሥትነት ጭምር የተሰየሙ የመንፈስ ደካሞች ሕወሓት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት በአማራ እናቶች፣ ሴቶችና ሕጻናት ላይ ሕጋዊና ሥርዓታዊ አድርጎ በታጋዮቹ እንዲፈጸም ሲያደርግ ስለኖረው አስከፊ የአስገድዶ መድፈር ወንጀልና ስለከተለው ሰብዓዊ ቀውስ አንዳች ነገር ትንፍሽ ማለትና እውቅና መስጠት አይፈልጉም።
እነዚህ ሰዎች ሕወሓት አማራን ለማጥፋትና በአማራ ላይ ያለውን ጥላቻ ለመግለጽ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ምድር በአማራ እናቶች፣ ሕጻናትና ሴቶች ላይ እንዲፈጸም ሕጋዊ ያደረገው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በአማራ ላይ ሲፈጸም ወንጀል የማይሆን፤ ለእድሜ ልክ የአካል እና የአእምሮ ሕመም፤ ለብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እና ውስብስብ ችግሮች የማይዳርግ ይመስላቸዋል ማለት ነው?
የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በማንም ላይ ይፈጸም፣ በማንም ይፈጸም፣ መቼም ይፈጸም፣ የትም ቦታ ይፈጸም፣ ለምንም አላማ ሲባል ይፈጸም በሰው ልጆች ሁሉ መወገዝ ያለበት አስነዋሪ ወንጀል ነው ብለው ካሰቡ፤ ሕወሓት ባለፉት 27 ዓመታት ተቋማዊ አድርጎት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ምድር በአማራ እናቶች፣ ሕጻናትና ሴቶች ላይ ሲያስፈጸመው የኖረውን በመጠንና ስፋቱ በቅርቡ የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የሚታወቅ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈጸም ሲባጅ የት ነበሩ? ለም መሬቱን ስለተመኙትና ነባሩ ሕዝብ በትግሬ እንዲተካ ስለተፈለገ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ምድር በአማራ እናቶች፣ ሕጻናትና ሴቶች ላይ ሕጋዊ የተደረገውን ሥርዓታዊ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለ27 ዓመታት ሙሉ ሲያስፈጸሙ የኖሩት ወያኔዎች በከባድ ወንጀል የሚጠየቁ ጥፋተኞች የሚያገኙትን ከፍተኛውን ቅጣት እንዲያገኙ ምነው አልጮሁም?
ሕወሓት ባለፉት 27 ዓመታት ተቋማዊ አድርጎ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ምድር በአማራ እናቶች፣ ሕጻናትና ሴቶች ላይ ሲያስፈጸመው የኖረውን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመጠኑና ስፋቱ ልክ በአደባባይ እውቅና ሰጥተው ሳያወግዙ፤ ወንጀለኛ ወያኔዎች እንዲቀጡና ግፉዓኑ የአማራ ተወላጆች እንዲካሱ ሳይጠይቁ በምን ሞራላቸው ነው ዛሬ ተነስተው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለመሆን የሚጋበዙት? ማፈር ደህና ሰንብት፤ መሽኮርመም ደህና ሰንብት ማለት አሁን ነው!