>
1:50 pm - Tuesday June 6, 2023

በትግራይ ሚዲያ ሀዉስ  አቶ ጌታቸዉ ረዳ ድምፃቸዉ ተሰማ!!

በትግራይ ሚዲያ ሀዉስ  አቶ ጌታቸዉ ረዳ ድምፃቸዉ ተሰማ!!“እኔ አደባባይ ላይ ወጥቼ ኢትዮጵያ እናቴ የሚለው ቋንቋ መናገር የምችልበት ሰአት አይደለም!”
 
“ጦርነት አልቋል የሚባለው ምኞት ነዉ !!”
የህዉሀት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸዉ ረዳ ትናንቱን በትግራይ ሚዲያ ሀዉስ ላይ በስልክ ገብተዉ ብዙ ሲናገሩ ተሰምተዋል::
አቶ ጌታቸዉ ከተናገሯቸዉ ዉስጥ :-
ጦርነት አልቋል የሚባለው ምኞት እንደሆነ : ጦርነት ያልተካሄደበት ቀን እስካሁን እንደሌለ : ጦርነት አልቋል የሚባለው ተረት እንደሆነ ተናግረዋል::
የነ አብይ ትልቅ የጦር መሳርያ ሆኖ ያለው : ትግራይ ከመላው አለም መገናኘት የምትችለውን ኮሙኒኬሽን በመዝጋት እነሱ የሚሉት ነገር ብቻ እውነታ ሆኖ የሚቀልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው ብለዋል::
የትግራይን ህልውና ለማጥፋት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለማክሸፍ የሚያስችሉ : ህዝባችን ወጣቱ ከዳር እስከ ዳር እየተነቃነቀ ነው መነቃነቁ መቀጠል መቻል አለበት::
– የኤርትራ ሰራዊት በተመለከተ ፈርኔሎ የሚዘርፍ አለ : ያረጀ ፎጣ የሚለብስ አለ : ሁሉም አይነት አላማ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ ሀይል ነው::
– በአሁኑ ሰአት መሬታችን የማስለቀቅ ጉዳይ ተደርጎ ብቻ መወሰድ የለበትም :ህልውናችን ላይ የተቃጣ አደጋ ስለሆነ : ይህንን የህልውና አደጋ ለመፍታት በሚያስችል ደረጃ በስፋት መንቀሳቀስ ይኖርብናል ብለን : በዛ ላይ ተመስርተን እየተንቀሳቀስን ነው ያለነው::
ኢትዮጵያን መቀጠል አለባት ብለው በጣም በፅኑ ከሚያምኑት የህወሓት አመራሮች አንዱ ነኝ ብየ ነው የማምነው : በአሁኑ ሰአት ትግራይን ነጥሎ በተለይ በተለይ : ሌላው ይቅር እና ከጠላት መንግስት ጋር በመተባበር ትግራይን ለማዘረፍ : የትግራይ መሰረተ ልማቶችን ለማውደም : የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ : የትግራይ ህዝብ ለማዋረድ በስፋት የሚሰሩ የአማራ ኤሊት ግዛቴ በሚላቸውን መሬቶችን ለማስመለስ በሚል ሰበብ የጋራ ጠላት ስለተገኘ : በዚህ ላይ ተመስርተው የትግራይ ህዝብ ላይ እየተሰራ ያለው ግፍ ግምት ውስጥ አስገብተህ : እኔ አደባባይ ላይ ወጥቼ ኢትዮጵያ እናቴ የሚለው ቋንቋ መናገር የምችልበት ሰአት ላይ አይደለሁም::
– ኢትዮጵያ መቀጠል አለባት/የለባትም በሚለው ጉዳይ ላይ የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ውሳኔ መወሰን ያለበት መብቱም የሆነ የትግራይ ህዝብ ነው:: በአሁኑ ሰአት አጀንዳችን ከምንም ነገር በላይ ትግራይ ከወረራ ነፃ የምትወጣበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው:: ያ ካደረግን በኃላ የትግራይ ህዝብ የሚወስነውን ውሳኔ የምንቀበል ነው የሚሆነው::
– ጁንታ የሚባል እንዳለ በቅርቡ ነው የሰማሁት : ጁንታው የሚባል የሆነ ደካማ አውሬ የሚፈልጉ አይነት ተደርጎ ነው የሚላኩት: እነዚህ ጋር ፀብ የለንም ብለዋል❗
Filed in: Amharic