ከ ማይጨው እስከ ኦጋዴን…!!!
ጸጋዬ ማንደፍሮ
የኢትዮጵያውያን የክፉ ቀን ታማኝ ወዳጅ የካርል ጉስታቭ ቮን ሮዘን እውነተኛ ታሪክ
መጽሓፉ በሁለተኛው የኢትየጵያና የጣሊያን ጦርነት ወቅት አባቶቻችን እናቶቻችን በማይነገር ጭካኔው በኩራት ከሚመካ እግዚአብሄርን ከማያቁ ልበ ድፍን ሠራዊት ጋር የተጋፈጡባቸዉን ክፋዎቹን የጦርነተን ወራት በዓይነ ህሊናችን የሚያሳየን የገዛ ራሳችን ታሪክ ነው። ሮዶልፎ ግራዚያኒ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ሙሶሊኒ ዘንድ ቀርቦ ተናገረው የተባለው አባባል ዘወትር በህሊናችን ታትሞ የሚኖር ነው::” ኢትዮጵያን የምትፈልጋት ከኢትዮጵያውያን ጋር ነው ወይስ ያለ
ኢትዮጵያውያን?”
ይህ መጽሐፍ በመጽሐፉ ደራሲ በሄሊ ቮን ሮዘን በወጉ የተደራጀ መረጃና ያገላለጽ ውበት በኢትዮጵያውያን ብርቱ የጦር ሜዳና የዲኘሎማሲ ተጋድሎ ነፃነት ተመለሰ ከተባለ በኋላ ንጉሡ፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በገቡበት አዲስ የፈተና ምዕራፍ ወስጥ ያሳልፈናል። በዚህኛው ምዕራፍ ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከጦርነቱ መልስ በጦርነቱ የፈራረሰውን የመንግስት ሥርዓት የደቀቀውን ኢኮኖሚና የተጎሳቆለውን ኢትዮጵያዊ ሞራል መልሰው ለማቀናት አቅማቸውና ዘመናቸው በፈቀደላቸው መጠን ያለፋበትን አድካሚ ጉዞ ገድላቸውን ሳያጋንን ፡ ጉድለታቸውን ሳይሸሽግ በነጻ ታዛቢ ሚዛናዊነት በየረድፉ ያስቃኘናል፡፡ ይህን መጽሐፍ ስናነብ ንጉሱ በረጅም የግዛት ዘመናቸው በመንግስታቸው ውስጥ በነበሩ፡ በመሣፍንቱና በዘመናዊያኑ ልሂቃን መካከል የግራቀኙን ሚዛን ጠብቀው አገሪቱን ወደፊት ለማራመድ የተጓዙበትን የሠርከስ ገመድ ላይ ጉዞ የሚመስለውን የፓለቲካ ህይወታቸውን እያስተነተነ ለህሊና ዳኝነት ያቀርብልናል፡፡
ሰለዚህ ነው መጽሐፉ የባለታሪኩ የካርል ጉስታቭ ቮን ሮዘን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የኛ የኢትዮጵያውያን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ማህደር ጭምር ነው የምችለው