>
5:13 pm - Thursday April 19, 2227

ይሄ ፎቶ በጣም ብዙ ነገር ይናገራል፤ ኢትዮጵያዬ ለነገሽ መጥኔ ይስጥሽ!!! ጌታቸው ሽፈራው

ይሄ ፎቶ በጣም ብዙ ነገር ይናገራል፤ ኢትዮጵያዬ ለነገሽ መጥኔ ይስጥሽ!!!

ጌታቸው ሽፈራው

 

*…. ሰው ሰክሮም አብዶም እንዲህ አይሰራም…!!!
 
1) ከልክ ያለፈ ተወዳጅና አስመሳይነት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩን አድዋ ዘማች አድርገዋቸው አረፉት። በቀጣይ ደግሞ የእምነት በዓል አክብሩ ሲባሉ ከአንዱ መላክ ጎን ለጎን ወይ አስመስለው ያስቀምጧቸዋል። በነገራችን ላይ ከዚህ ይልቅ የአድዋ ዘማቾች ፎቶ ጠጋ ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተነሱትን ፎቶ ቢለቁ ይሻላቸው ነበር።
2) የሀሰት ትርክት ፍጥጥ፣ ግጥጥ ብለው የመጣበት ነው። አሁን አብይ አህመድ በአድዋ  ጦርነት እንደነበሩ አስመስሎ የሚያቀርብ ኃይል አጤ ምኒልክ ጡት ቆረጠ ብሎ ሀውልት መትከሉኮ አይገርምም።  አጤ ምኒልክ ጥይት ተኩሶ ያረገፋቸው ኮከቦች አሉ ብሎ አጤ ምኒልክን ዓለምን ጨለማ ለማድረግ የሰራ አድርገው ቢዋሹ አይፈረድባቸውም።
3) የአድዋ ድል በዓልን ተሻምተው እያከበሩት ያሉት አድዋን ወድደውት አይደለም። እንዲያውም በእጅጉ ስለሚጠሉት ነው። በዓሉን በማክበር ስም ታሪክ አጣምመው፣ አበላሽተው ዋጋ አልባ ማድረግ ነው። ልክ የኢትዮጵያውያን የሆነችውን አዲስ አበባን ዋጋ አልባ እናደርጋለን እንዳሉት፣ የኢትዮጵያውያን መለያ የሆነውን አድዋን  ዋጋ አልባ አድርጎ መጣል ነው የሚፈልጉት። ከአመታት በኋላ ካድሬ ድንኳን ውስጥ እንደሚያከብረው ጊዜ አመጣሽ በዓል  ሕዝብ ጣል እርግፍ አድርጎ እንዲተወው ይፈልጋሉ። በሚቀጥለው አመት ደግሞ የክልላቸው ካድሬ እስከነቀፈቱ አንዱ የአድዋ ጀግና ፎቶ ጎን ለጎን ይቀመጣል። አሊያም አብይን የአድዋ ጀግና አድርገን አሳምነናቸዋል ብለው አብይን እንደ አድዋ ጀግና አድርገው ማዶ ለማዶ ያነኛውን ከእነ ቀፈቱ ይለጥፉታል።
አድዋን ቢያከብሩት ኖሮ የአድዋን እሴት ያከብሩ ነበር። ከአድዋ በዓል ይልቅ በዓሉን አዲስ አበባ ላይ ማክበራቸው፣ እነ አጤ ምኒልክ  እንዳይወሱ ያደረጉትን ጥረት እንደ ትልቅ  ድል ያዩታል። በዚህ በዓል አከባበር እየተናገሩ ያሉትን ተመልከቱ። በዚህ በዓል ሰበብ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ጥላቻ ነበር ሲያወራ የነበረው። ታሪክ ሽሚያና ቅሚያ አለ ሲል ነበር። ያን በምን አጣጣሙት? የአብይን ፎቶ በማስገባት። የኢትዮጵያ ታሪክ ፀሐፊዎች ሀሰት ሲፅፉ ነበር ብሎ ሲደነፋ ነበር። የማያውቀውን ታሪክ በሀሰት የተፃፈ ነው እያለ በቀደም ወደ ስልጣን የመጡትን ሰውዬ በእነ አጤ ምኒልክ ቦታ አስቀምጦ የአድዋ ድል መሪ አድርጎ አቅርቧል።
ሰው ሰክሮም አብዶም እንዲህ አይሰራም። እነሱ ምን እንደሆኑ እንጃለታቸው።
Filed in: Amharic