>

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኤሊቶች የጋራ ችሎታ ውድቀት፣ ታሪካዊ ምልከታ - ደረጀ መላኩ ( የሰበዓዊ መበት ተሟጋች)

 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኤሊቶች የጋራ ችሎታ ውድቀት፣ ታሪካዊ ምልከታ

Heaven and earth are such an immense realm that it can only be grasped by the collective intelligence of all intelligent beings.” — The Faust-Legend and Goethe’s ‘Faust’ H. B. Cotterill

 

ክፍል አንድ

ደረጀ መላኩ ( የሰበዓዊ መበት ተሟጋች)

Tilahungesses@gmail.com


መግቢያ

በዛሬው ጽሁፌ ላይ ለመዳሰስ የምሞክረው ዋነኛ ጭብጥ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ኤሊቶች ፖለቲካዊ ችግሮችን ይሆናል ወይም በወፍ በረር መቃኘት ይሆናል፡፡ ትንተናው የሚጀምረው ከዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ( እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1889- 1913) እስከ ዶክተር አቢይ አህመድ አሊ ዘመነ መንግስት ያለውን ይሆናል ( እ.ኤ.አ. 2018 አሁን ድርስ የኢትዮጵ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡) በሌላ አነጋገር ጽሁፌ ለመሸፈን የሚሞክረው የዳግማዊ አጼ ምንሊክ ዘመነ መንግስት( Emperor( Menelik II )፣ የአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት, (Emperor Haile Selassie’s era (1930 to 1974), )፣ የደርግ ወታደራዊ መንግስት( the Military regime (Derg[2]) of Socialist Ethiopia (1974–91), ፣ የኢህአዲግ ወያኔ አገዛዝ the EPRDF (TPLF) regime (1991-2018))[2] አሁን ያለውን የብልጽግና አገዛዝን ይሆናል (the current Biltsigina (ብልጽግና) regime (2018-2021).)

 ጸሃፊው የሚከተሉትን ነጥቦች ለመዳሰስ ይሞክራል፡-

 • ፖሊሲዎችን
 • የዲፕሎማቲክ እውቀት
 • የፖለተካ ሳይንስ
 • ተጠያቂነት
 • መንግስትን
 • የመንግስት ውሳኔዎችን
 • የፖለቲካ ተጠያቂነትን
 • የህግ ተጠያቂነትን
 • የሙያ ተጠያቂነት
 • ቢሮክራቲክ ተጠያቂነት
 • የዜግነት ተጠያቂነት

ለዛሬው ከላይ ያነሳኋቸውን ሁሉንም አንኳር ነጥቦች ላይ በሰፊው አልሄድባቸውም፡፡ ለግዜው ከተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ያገኘኋቸውን አንኳር ግኝቶች እና የራሴን ምልከታ አቀርባለሁኝ፡፡

ከላይ ለማስቀመጥ በሞከርኳቸው መለኪያዎች መሰረት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ኤሊቶችን ኮሌክቲቭ ኢነተልጄንስ ስለካው ወድቆ ወይም ዝቅ እያለ የመጣ ይመስለኛል፡፡

 እንድ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ለብዙ አመታት ለመምራት የሚከተሉት ነጥቦች አስፋላጊ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡-

1.ከፍተኛ የሆነ የማሰብ ችሎታ( strong mind (high IQ);

2.በሰዎች ስሜት ላይ ተጽእኖ የማሳደር ችሎታ (strong ability to influence people on an emotional level (high EQ); )

3.ለመልካም ነገር አርአያ መሆን (strong positive character (high CQ )

 የስነ ልቦና ባለሙያ ባለመሆኔ የስነ ልቦና መለኪያዎችን በመጠቀም የሰውን የአስተሳሰብ ችሎታ ወይም ኢነተለጀንሰ ለመለካት አልነሳም፡፡ የማላቀውንም ሳይንስ ለመዘባረቅ አልፈልግም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ሆኖም ግን ባለፉት ሰላሳ አመታት እና  ከዛም በላይ አመታት በፊት የተነሱ የጎሳ ፖለቲካ አመራሮችና ጠባብ ብሄርተኞችን ፐርሰናሊቲ ስመረምር ከታሪክ ለመማር ዝግጁ የሆኑ አልመስልህ አለኝ፡፡ በነገራችን ላይ ባለፉት ሰላሳ አመታት የተነሱትን ጠባብ ብሔርተኞች በገቢርም በነቢብም ያየኋቸው ሲሆን ከአርባ አመታት በፊት የተነሱትን ግን ከመጽሀፍት ንባብ ከቃረምኩት እውቀት በመነሳት አስተያየት ለመስጠት እንደተነሳሳሁ አንባቢውን ሳስታውስ በአክብሮት ነው፡፡ በአጭሩ ጠባብ ብሔርተኞች ወይም የጎሳ ፖለቲካ ኤሊቶች፣ እንዲሁም አንዳንድ የፖለቲካ ኤሊቶች ከታሪክ ወይም አሁን ካላው ተጨባጭ የአለም እና የኢትዮጵያ ነባራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመማር ዝግጁ አይደሉም ተብሎ ቢጻፍ ስህተት አይመስለኝም፡፡ ከተሳሳትኩ በምክንያታዊ መልስ ለመታረም ዝግጁ ነኝ፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም እነርሱ በሚፈጽሙት የፖለቲካ ስህተት በሚፈጠረው ችግር ብዙም አይጨንቃቸውም፡፡ ከዚህም እልፍ ብሎ በእነርሱ የተሳሳተ የፖለቲካ ትርክት ሀገሪቱ እንጦርጦስ ብትወርድ ህዝቡ መጠነ ሰፊ ችግር ውስጥ ቢዶል፣ የሚደማ ልብ የላቸውም፡፡ አይምሮአቸውም አይቆስልም፡፡

ለምን ይሆን ከአፍንጫቸው አርቀው የማያስቡ ሰዎች ወይም የማሰብ ችሎታቸውን መጠቀም ያልቻሉ ሰዎች፣ ወይም ከፍተኛ እውቀት ያላቸው ሰዎች ከፋፋይ እና ወግ አጥባቂ ርእዮት አለምን የሚከተሉት ? እስቲ በየሰፈራችሁ፣ የሃሳብ ገበያ የሚንሸራሸርባቸው ቡና ቤቶች ወዘተ ወዘተ ተወያዩበት፡፡

እውን ጎሰኞች፣ ጠባብ ብሔርተኞች ዘረኞች ሊሆኑ ይቻላቸዋልን ? እንደ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ጥናት ውጤት ከሆነ መልሱ አዎንታዊ ነው፡፡ እነርሱ ከአንድነት ይልቅ በልዩነት ላይ የሚተኮሩ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ተመልሶ ተመላልሶ ጭቃ እንዲሆን የሚያደርጉት በአብዛኛው የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞች ናቸው፡፡ያለውን አጠቃላይ የሀገሪቱን ሰላም አስተማማኝ እንዳይሆን ያደረጉት የጎሳ ፖለቲከኞች እና በሌላ በዜግነት ፖለቲካ ላይ ተሳታፊ ነን የሚሉ አንዳንድ የከንቱ ከንቱ አድርባይ ፖለቲከኞችም ቢሆኑ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ውሃ ወቀጣ አድርገውታል፡፡ በእውነቱ ያሳዝናል፡፡ በነገራችን ላይ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ አብንም ሆነ ባደራስ፣ ብልጽግናም ሆነ ኢዜማ፣ ኦነግም ሆነ ኦብነግ፣ኦፌኮም ሆነ መኢአድ ወዘተ ወዘተ እኩል ናቸው፡፡ማንም ኢትዮጵያዊ የፈለገውን ፖለቲካ ፓርቲ ለመደገፍ ነጻ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ቁምነገሩ ለሀገሪቱ እጅግ ስር ለሰደደው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሰራሄ መፍትሔ ያለው ርእዮት አራማጁ የትኛው ፖለቲካ ፓርቲ ነው የሚለውን ማወቅ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ምላሽ ለማግኘት ቁጭ ብሎ የሚያስብ፣ የሚነጋገር፣ የአይምሮ ሀይሉን መጠቀም የሚችል ዜግ ግድ ይላል፡፡ በጥፊ የሚመታህን ሰው በቦክስ ልተመታው ትችላለህ፡፡ ይህ ግን ትክክለኛ ምላሽ አይደለም፡፡ ስለሆነም ለምላሹ አርቆ ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ ፍጹም ነጻ፣ ፍጹም ሰላማዊ ኑሮ አይታሰብም፡፡ ስለሆነም በተገደበ መብት፣ አንድ ማህበረሰብ፣ አንድ ዜጋ፣ ማህበራዊ ህይወት ለመፍጠር በብዙ መትጋት አለብን፡፡አረ ለመሆኑ ለምንድን ነው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ላይ ተሳታፊና የፖለቲካ ፓርቲዎች ደጋፊ ነን የሚሉ ቁጥራቸው የትዬ የሌሌ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ወንድሞች፣ አህቶች፣ አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ወጣቶች ከስሜት ፖለቲካ መውጣት የተሰናቸው ወይም ለምን ይሆን ስሜታዊ ደጋፊ የሆኑት ? ኢትዮጵያ ረቂቅ ሀገር ናት፡፡ ፖለቲከኞቻችን ላለመስማማት መስማማት ተስኗቸው  እንኳን ህዝቡ አለ፡፡ ይህ በእግዜአብሔር ቸርነት የሆነ ይመስለኛል፡፡ ለማናቸውም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ህይወት ውስጥ አስተዋይ ባሕርይ እና ብልህነት አስፈላጊ ነው፡፡ በነገራችን ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚጠሩት ሁለቱ ቃላቶች ማለትም፣intelligent’(አስተዋይ) and ‘intelligent behavior’ ( አስተዋይ ባሕርይ) በአማርኛ ቋንቋ ያላቸውን ልዩነት ወይም አንድነት ለማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ለአብነት ያህል በእንግሊዝኛው ቋንቋ አንድ ግለሰብ ያለምንም አጋዥ ችግርን ማስወገድ፣ፍጥነት፣የማስታወስ ችሎታ፣ ምክንያታዊ መሆን፣ ከቻለ አስተዋይ intelligence’. የሚል ስያሜ ሊሰጠው ይቻለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ግን ብዙ ግዜ ከተጠቀሰው ሃሳብ ተቃራኒ ሃሳቦች ሲሰዘነዘሩ ይስተዋላል፡፡ ለአብነት ያህል በርከታ ህጻናት ከትምህርት ቤት በአስተማሪዎቻቸው የሚሰጣቸውን የቤት ስራዎች አንድ ላይ በህብረት ይሰራሉ፡፡ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ኢትዮጵያዊ ወላጆች ደግሞ ልጆቻቸውን አንድ ላይ አጥኑ የሚል ትእዛዝ መስጠት ትክክለኛ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ወይም ልጆቻቸው ትምህርታቸውን እንዲያጠኑ ማበረታቻ ቃላት የተጠቀሙ ይመስላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህን ትእዛዝ ለልጆቻቸው ሲሰጡ፣ የልጆቻቸውን የክፍል ደረጃ እና ችሎታ ከግምት ውስጥ አይከቱትም፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ህይወት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ደረጃ ሳይቀር የግለሰብ ልዩ ችሎታ ትኩረት አይሰጠውም፡፡ ህጻናት ልጆቻቸው በራሳቸው የአይምሮ ሀይል ተጠቅመው ለችግሮች መፍትሔ እንዲፈልጉ አያበረታቱም፡፡

በነገራችን ላይ አስተዋይ ሰው ማለት የአይምሮ ችሎታ፣ ምክንያታዊ መሆን፣ እቅድ የሚያወጣ፣ ችግርን መፍታት የሚችል፣ በጥልቀት ማሰብ የሚችል፣የተወሳሱቡ ሃሳቦችን በቅጡ የሚረዳ ፣ በፍጥነት የሚማር እና ከህይወት ልምዱ የሚማር ሰው ማለት ነው፡፡ ከዚህ ባሻግር አስተዋይነት የሚመነጨው ከትምህርት ቤት ውስጥ ከሚገኝ እውቀት ብቻ ሳይሆን፣ ከተፈጥሮ አካባቢ፣ከአረጋውያን የህይወት ልምድ በመቅሰም ጭምር ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰው ልጅ አካባቢውን በጥልቀት ማጥናት፣ ማስተዋል እንደሚችል ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ ባሻግር አንድ ላይ ከመስራት ባሻግር ማስተዋል እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ አንድ ላይ የተሰባሰቡ ሰዎች አንድ ላይ እንዲተባበሩ፣ማሰብ እንዲችሉ ይረዳል፡፡ ከዚህ አንጻር ማስተዋል፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኤሊቶች አብረው እንዲሰሩ በእጅጉ ይረዳል ብዬ አስባለሁ፡፡ 

ጎትፍሬንደሰንስ የተባለ ምሁር እንደ ጎርጎሲኑ አቆጣጠር 1998 አስተዋይ ምን ማለት እንደሆነ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስቀመጠውን ጽንሰ ሃሳብ ለአንባቢው ግንዛቤ ይሰጣል በሚል እንደሚከተለው አስፍሬዋለሁ፡፡

I partly share Gottfredson’s (1998)[6] conception of intelligence. Intelligence is a very general mental capacity which, among other things, involves the ability to reason, plan, solve problems, think abstractly, comprehend complex ideas, learn quickly and learn from experience. It is not merely book-learning, a narrow academic skill, or test-taking smarts. Rather, it reflects a broader and deeper capability for comprehending our surroundings- and hence catching on, making sense of things, or figuring out what to do (p.13). At a collective level,[7] it refers to being capable of collaborative and imaginative thinking; it entails social dimension regarding ability of groups [in this case the political elites of Ethiopia] to achieve unity of purpose, action and thought. Teams with high levels of collective intelligence (CQ) achieve a state of interdependence and flow when they are working together[8]

ኢትዮጵያ በዛሬው ዘመን በሚገኙ የፖለቲካ ኤሊቶች አኳያ አሮጋንሲ Arrogance ፣ ኋላቀርነት Ignorance,፣ ብቁ ተወዳዳሪ አለመሆን ባህሪያቸው እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡ የእኔ ትኩረት የሚሆነው እንደ ውሃ ወቀጣ ተመሳሳይ ባሪ ስላለው በሲቪል አገልግሎት እና በመንግስት ቢሮ ውስጥ ስለተታጨቁትና መሰረታቸውን ጎሳ ላይ ስላደረጉ የፖለቲካ ኤሊቶች ላይ ይሆናል፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የነበረው አገዛዝ ተወዳዳሪ መሆን ያልቻለ፣ ደካማ፣ ውጤታማ መሆን ያልቻለ፣ስልጣን ብቻውን የተቆጣጠረ፣በጉቦ ጭንቅላቱ ድረስ የተነከረ፣ ነበር፡፡ ስለሆነም ከ2010 ዓ.ም. ወዲህ በስልጣን ኮርቻ ላይ የተፈናጠጡት ጠንካራ፣ውጤታማ፣ ከጉቦ ነጻ መሆን፣ ይጠበቅበታል፡፡ ከሌሎች የፖለቲካ ተፎካካሪዎች ጋር በጋራ አጀንዳ ላይ ለመወያየት ዝግጁ መሆን ያለበት ይመስለኛል፡፡ ስልጣን ላይ ቁጢጥ ለማለት ብቻ በምርጫ ለመወዳደር መዘጋጀት ኋላ ላይ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ በነገራችን የአንድ ማህበረሰብ ጥንካሬ የሚመነጨው ከመሪዎች ጥንካሬ ይመስለኛል፡፡

በዛሬው ጽሁፌ ላይ እውነታን ለማግኘት ስል የራሴን አመለካከት ነው ለማስፍር የሞከርኩት የማንም ሰው ወይም ድርጅትም አቋም ላለማንጸባረቅ ጥንቃቄ ለማድረግ እሞክራለሁኝ፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቴን በመጠቀም የሃሳብ ገበያ ለመፍጠር ነው አነሳሴ፡፡

 

የጋራ ኢንተለጀንስ በአራቱ የፖለቲካ ዘመን ፣በኢትዮጵያ

የጋራ ኢንተለጀንስ ለሌሎች ማስተማር ወይም የአንድ ቡድን ችሎታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ኮሌክቲቭ ኢንተለጀንስ እውን ሊሆን የሚቻለው በርካታ ግለሰቦች መወዳደርና መተባበር ሲቻላቸው ነው፡፡ አረ ለመሆኑ የጋራ ኢንተለጄንስ መለኪያው ምን ይሆን ?

እውን የጋራ ትምህርት፣ የጋራ ኢነተለጀንስ መፍጠር ያስችል ይሆን ? አንድ የፖለቲካ ኤሊት ወይም የፖለቲካ ኤሊቶች ከሌሎቹ የፖለቲካ ኤሊቶች በምን መስፈርት ነው ከሌሎቹ የበለጠ ችሎታ የሚኖራቸው? እውን ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ግሰለሰቦች ስብስብ የሆኑ ቡድኖች፣ ከሌሎች መካከለኛ ወይም ዝቅተኛ ችሎታ ካላቸው ስብስብ ቡድኖች የተሻለ የጋራ ችሎታ አላቸውን ? እውን የዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት አመራር እና በዙሪያቸው የነበሩት በዛሬወ ዘመን ካሉት አመራሮች የተለየ ችሎታቸው ምን ነበር ? ለቀረቡት ጥያቄዎች ወደ ድምዳሜ የሚወስዱን መልሶች መሰረታቸው ምን ይሆን ? 

በእኔ አኳይ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ (ግጭቶች)  ወደ ሚወስዱ ሃሳቦች ለመውሰድ ፍላጎቴ አይደለም፡፡ ወይም እንዲህ አይነት ጉዳይ ውስጥ መግባት አልፈልግም፡፡ ወይም የጽሁፌ ዋነኛ አላማ አይደለም፡፡ እኔ በጋራ ችሎታ ላይ ፍላጎት የለኝም፡፡ የጋራ ደድብናን እንደማወግዘው ሁሉ በጋራ ችሎታ ላይም ማተኮር ፍላጎቴ አይደለም፡፡

 

I abstain to delve into disputes. I am loosely interested in the concept of collective intelligence as opposed to collective stupidity in certain group-motivated actions or inaction

በነገራችን ላይ የእኛ የጋራ ችሎታ የተመሰረተው፣ ከቤተሰባችን፣ ከወጣንበት ማህበረሰብ፣ ከማህበራዊ ቡድን፣ ወይም ካለን የጥበብ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና አንዳንድ ቡድኖች በእንዲህ አይነት ዘዴ እውቀት ለማግኘት ሲቸገሩ ይታያል፡፡ በእኔ አስተያየት ይህ የጋራ ውድቀትን ያስከትላል ብዬ አስባለሁ፡፡ I believe, collective stupidity.

በኢትዮጵያ የአንድ መሪ ባላዊ ባህሪ የሚሽረከረው በመሪው ችሎታ ላይ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ለብዙ ሺህ አመታት በኢትዮጵያ የነበረው እውነታ ንጉስ ወይም ንግስት ለመሆን የበቃነው በእግዜአብሔር ቸርነት ነው ብለው ያምኑ ነበር ወይም የዚች ሀገር ንጉስ ወይም ንግስት ለመሆን በእግዜአብሔር ተቀብተናል ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ( ሥዩመ እግዜአብሔር)፡፡ የአምባገነን አገዛዝ ደግሞ መሰረቱ ሁል ግዜ በአንድ ሰው ወይም በተወሰኑ ቡድኖች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የማሰብ ችሎታ ያላቸው፣አሰላሳይ መሪዎች የተበቡት በአርቆ አስተዋይ ህዝብ እንደሆነ መታወቅ ያለበት ይመስለኛል፡፡ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ ደግሞ ደደብ መሪዎች ደግሞ የተከበቡት በደደብ ደጋፊዎቻቸው ነው፡፡ በእኔ አስተያየት በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍል መሰረታቸውን ጎሳና ሀይማኖት ላይ አድርገው የተፈጸሙ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የጋራ የአስተሳሰብ ችግሮቻችን ማሳያ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ በሌላ አነጋገር በአንድ የሀገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጸሙ ጩሀታቸውን የሚያሰሙት በደል የደረሰባቸው ብቻ ወይም በጣት የሚቆጠሩ የመብት ተሟጋቾች ( ድርጅቶች) ብቻ ናቸው፡፡ ለምን ? ለሰብዓዊ መብት መሟገት የበፍቃዱ ፣ መስከረም ወይም የአቶ ያሬድ ሃይለማርያም ግዴታ ብቻ አይመስለኝም፡፡ ለምንድን ነው ሁላችንንም ሊያሳስበን ያልቻለው ? አምባገነኖች ተራ በተራ ለምን የሰብዓዊ መብቶቻችንን ሊገፉን ቻሉ ብለን ጠይቀን እናውቅ ይሆን ? እኛ የጋራ ግንዛቤ ስላጣን ኢትዮጵያን ለከፋ ችግር እየዳረግናት እንገኛለን፡፡ ሰብዓዊ መብቶቻችንን በጋራ ማስከበር ተስኖናል፡፡ ስለ ሰብኣዊ መብት ጽንሰ ሃሳብ ያለን የጋራ ግንዛቤ እጅጉን ደካማ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ባህሪ ስር በሰደደባቸው ሀገራት የፖለቲካ ኤሊቶች እንደፈለጉ ይፈነጫሉ፣ የፖለቲካ ኤሊቶች ብቁ ተወዳዳሪ መሆን አይችሉም፡፡ ከዚህ ባሻግር የዛች ሀገር መሪ በሚመራው ህዝብ ላይ ተጽኖ መፍጠር ሲሳነው፣ መልካም አርአያ መሆን ሲሳነው፣ ወዘተ የሚከተሉት መራር እውነታዎች እንዲፈጠሩ ግድ ይላል፡፡

 1. ለራስ ከበቂ በላይ ግምት መስጠት (Egoism) 
 2. ሴረኝነት ( የሴራ ፖለቲካ) Machiavellianism;
 3. ሞራል አልባነት (. Moral disengagement;)

4.ስግብግብነት (Narcissism; )

5.የስነ ልቦና ተጽእኖ መፍጠር (Psychological entitlemen )

 1. የስነ ልቦና ችግር (. Psychopathy)

7.ሀዘን (Sadism )

8.የግል ፍላጎት ብቻ ማሳደድ  (Self-interest )

 1. Spitefulness 

ከላይ ላነሳኋቸው ነጥቦች እውነትነት ኢትዮጵያ ቋሚ ምስክር ናት፡፡ በተለይም ባለፉት አርባ አመታት ( 40 ) አመታት የበቀሉ የፖለቲካ ኤሊቶች፣ የፖለቲካ መሪዎች እና ጭፍን ወይም የስሜት ደጋፊዎቻቸው ከላይ ካሰፈርኳቸው ዘጠኝ ባህሪያቶች ውስጥ አብዛኛውን ይጋራሉ፡፡ ወይም ዘጠኙንም ባህሪያቶችን ያሳያሉ ተብሎ ቢጻፍ ስህተት አይመስለኝም፡፡ ከተሳሳትኩ ልታረም ዝግጁ ነኝ፡፡ በነገራችን ላይ ሁሉንም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኤሊቶችን ከላይ የጠቀስኳቸውን ባህሪያት ይላበሳሉ ብሎ መደምደም ከባድ ስህተት፡፡ ኢትዮጵያን በቅን ልቦና አገልግለው ያለፉ የፖለቲካ ኤሊቶች ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ታሪክ ዘለአለማዊ ተግባራቸውን አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም ቢሆን ለሀገራቸው እድገትና ብልጽግና የሚባጁ አይጠፉም፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱት ባህሪዎች እንዲህ አይነት የፖለቲካ ኤሊቶችን አይመለከትም፡፡

በእኔ ምልከታ ወይም አስተያየት መሰረት፡- ካለፉት 40 አመታትና ከዛ በፊት በነበሩት አመታት የስልጣን ማማ ላይ ቁጢጥ ብለው የነበሩ ቁጥራቸው ማይናቅ የፖለቲካ ኤሊቶች የሚከተሉትን ባህሪያት የተላበሱ በሩ

ሀ. ድንቁርና (ignorance,)

ለ.ሌሎችን አለማበረታታት ( መልካም ለሰሩ ግለሰቦች ለመልካም ስራቸው እውቅና መንፈግ)

ሐ. የሞራል ዝቅተኝነት

መ. የበታችነት ስሜት

ሠ.ለህዝብ አለማሰብ 

ከላይ ላሰፈርኩት የፖለቲካ ኤሊቶች ባህሪያት ምክንያቶቼ ወይም ድምዳሜ ላይ እንድደርስ ያደረጉኝ መላምቶች ደግሞ የሚከተሉት ፍሬ ሃሳቦች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡-

ሀ.የፖለቲካ ተጣያቂነት ዝቅተኛ መሆን

ለ.የበሮክራሲው ተጠያቂነት ( ምን ያህል ህዝቡን ያለ አድሎ ያገለግሉታል ?ለጥፋታቸው በፍትህ መሰረት ላይ ቆመው ይጠየቁ ይሆን ? መልሱን ለአንባቢው ትቼዋለሁ፡፡)

ሐ. የዜጎች ተጠያቂነት ( ለሚፈጽሙት ጥፋት…)

መ. የህግ ተጠያቂነት ( ህግን ከመጣስ አኳያ የፖለቲካ ኤሊቶች ( በተለይም በስልጣን ማማ ላይ ቁጢጥ ያሉት የፖለቲካ ኤሊቶችና ተራው ዜጋ እኩል ተጠያቂ ናቸውን ? መልሱን ህሊና ለፈጠረባችሁ ትቸዋለሁ፡፡

ሠ.የሙያ ተጠያቂነት ( በተለያዩ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሙያ ሥነምግባራቸውን ሲጥሱ እኩል ይጠየቃሉን ? )

ምንም እንኳን ይሁንና የአጼ ምንሊክ ዘመነ  መንስት ኢትዮጵያ ባህላዊ አስተዳደር ቢኖራትም፣ የማህበራዊ እድገት ባይኖርም፣ ዘመናዊነት ባይስፋፋም ፣ ከላይ ካሰፈርኩት መመዘኛዎች አኳያ ( ከሀ- ሠ ከሰፈሩት ቁምነገሮች ውስጥ ማለቴ ነው) የአጼ ምንሊክ ዘመነ መንግስት ጠንካራ ጎኖች ነበሩት፡፡

በአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት የነበሩት የፖለቲካ ኤሊቶችም ቢሆኑ ከጋራ ችሎታ አንጻር ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ፣ እውቀትም የነበራቸው ናቸው፡፡ አጼ ሀይለስላሴ ዘመናዊ ትምህርትን አስፋፍተዋል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ዘመናዊ ትምህርቱ የሀገሪቱን ፍላጎት ለማጣጣም እንዳልቻለ እንደ እነ ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ( አፈሩን ገለባ ያድርግላቸው) በጥናት ጽሁፎቻቸው ያረጋገጡት ጉዳይ ነው፡፡ የትምህርት ፖሊሲው ተዘጋጅቶ የነበረው ለሌላ ህብረተሰብ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ የህብረተሰብ እድገት የምጣኔ ሀብት፣ የማህበራቀዊና ፖለቲካዊ ደረጃዎችን ማለፍ ግድ ይለዋል፡፡ ለአብነት ከፊውዳሊዝም፣ወደ ካፒታሊዝም፣ ምናልባትም ወደ ሶሻሊዝም ወይም ወደ ኮምኒዝም ሊሆን ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ከላይ የተጠቀሱትን  ደረጃዎች በማለፍ ሳይሆን፣ በቀጥታ ከፊውዳሊዝም፣ ወደ ሶሻሊዝም በማለፍ ነው፡፡ የካፒታሊዝም እድገትን ዘሎት ነበር ያለፈው፡፡ ሀብትን ሳይፈጥሩ ፣ሀብትን በጋራ ለማከፋፈል ነበር የተሞከረው፡፡ ግን አልተሳካም፡፡ የኢትዮጵያን አብዛኛውን ህዝብ ከድህነት ነጻ ማውጣት ሳይችል ነበር የደርግ ስርዓት የተገረሰሰው፡፡ ወይም የወቀደው፡፡

It went straight to equal distribution of wealth without creating the wealth itself

በነገራችን ላይ የአጼ ሀይለስላሴ አገዛዝ በደርግ ስርዓት መቀየር በርካታ ለውጦችን አምጥቶ የነበረ ቢሆንም ፣ በብዙ መልኩ ሀገሪቱን ጎድቷት እንደነበር የሚያሳዩ መረጃዎች በበርካታ ምሁራኖች ተጽፈዋል፡፡ ለአብነት ያህል የሀገሪቱ የታሪክ መሰረት የነበረው የንጉሳዊ አገዛዝን ያሰውገደው ደርግ ፣ እንደነ ጃፓን ወይም ታላቋ ብሪታኒያ አይነት በህገመንግስት እውቅና ያለው የንጉስ ስልጣን  በመስጠት ታሪክን ማስቀጠል ሲችል ለማድረግ አልፈለገም ነበር፡፡ ከሃይማኖት ተጻራሪ የሆነ ርእዮት ( ሶሻሊዝም፣ ማርክሲዝምና ሌሊንዝም) የተሰኙ ርእዮት ብቻ መከተሉ

አልጠቀመንም ነበር፡፡ በነገራችን ላይ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት የነበረውን የዲፕሎማቲክ ተጋድሎ ወይም የዲፕሎማቲክ እውቀት ለንጽጽር ማቅረብ አይቻልም፡፡ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት የተፈጸሙት የዲፕሎማቲክ ተጋድሎዎች የሚከተሉትን ውጤቶች አስገኝተው ነበር፡፡

 • በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነጻ እንዲወጡ አድርጓል
 • የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና  የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተመስርተዋል፡፡ እነኚህ ሁሉ በአጼ ሀይለስላሴ አመራር ሰጪነት ነበር እውን ሊሆኑ የቻሉት፡፡ ታሪክ አይሸፈጥም፡፡ ሁላችንም እንደምናስታውሰው  ‹‹ ሀይማኖት የግል፣ አገር የጋራ ›› በሚለው የአጼ ሀይለስላሴ ፍልስፍና መሰረት (As the slogan was “Faiths are personal and country is communal)  በንጉሱእና ነገስታት ዘመነ መንግስት  በባህላዊ ትምህርት ቤቶች ( በቄስ ትምህርት ቤቶች) ውስጥ ለተማሪዎች በግእዝ ቋንቋ አመሃኝነት  የክርስትና ትምህርት ይሰጥ ነበር፡፡ የእስልምና ተቋማትም የራሳቸውን ድርሻ ይወጡ ነበር፡፡ መድራሳ እና ኡላማዎች ሀይማኖቱ በሚያዘው መሰረት ሀይማኖታዊ ትምህርት ይሰጡ ነበር፡፡ በርካታ እንደሚያምኑበት እና በጥናታቸው እንደደረሱበት ከሆነ ሀይማኖታዊ መሰረት ያላቸውን እውቀት ለልጆች ማስተማር፣ ልጆች ትክክለኛ መንገድ ላይ እንዲቆሙ፣ መልካም ስነምግባር እንዲኖራቸው፣ ሞራል እንዲኖራቸው፣ ትክክለኛ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው፣ ጤናማ አይምሮ እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡

በአንዳንድ ምሁራን የጥናት ስራዎች ላይ እንደተጠቀሰው የጥንቱ የሀይማኖት ትምህርት፡-

 • ለማህበራዊ ህይወት መሳለጥ እና
 • ለስነ ልቦና ዝግጁነት ( ጤንነት) ይረዳል፡፡

በአጼ ምንሊክ እና አጼ ሐይለስላሴ ዘመነመንግስት የነበረው የትምህርት መሰረት ባህላዊ ወይም ሀይማኖታዊ ነበር፡፡ ስለሆነም በግዜው ፈሪሀ እግዜአብሔር ነበር፡፡

Emperors Menelik and Haile Selassie’s era were relatively high in the realms of classic learning ፈሪሀ እግዚአብሔር (God Fearing learning) and fairness, as I was told by my parents and grandparents.

የጥንቱ ባህል የሚተማመነው በአለቃ ( በመሪዎች) አመራር ችሎታ ላይ ነበር መመሪያው ‹‹(ተመልከት አላማህን ተከተል አለቃህን). የሚል ነበር፡

Old tradition depends on the qualities of leadership. The adage is “Look at the your angina and follow your leader

ስለሆነም ውድቀት ወይም አሸናፊነት ሊከሰት የሚቻለው በአመራር ብቃት ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ለአብነት ያህል በምኒሊክ ብልህ አመራር ኢትዮጵያ የአድዋን ድል በመጎናጸፏ ምክንያት በአለም ታሪክ ላይ ትልቅ ስፍራ የሚቸረው ነው፡፡ ወይም የአለምን ታሪክ  ነው፡፡ ከብዙ አመታት በፊት አውሮፓውያን በአለም ላይ ማንም አያሸንፈንም ብለው ያስቡ ነበር፡፡ አለምን ሁሉ መግዛት ይቻለናል ብለው ተነስተው ነበር፡፡ በገቢርም በነቢብም አሳይተውን ነበር፡፡ የአድዋ ድል ግን ጥቁሮች ነጮችን ማሸነፍ እንደሚችሉ አሳይቷቸዋል፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም መላው የአለም ጥቁር ህዝብ በተለይም አፍሪካውያን ፣ ኤሽያውያን፣ላቲን አሜሪካንስ ከቅኝ ገዚዎች ነጻ እንዲወጡ የሞራል ስንቅ የሆናቸው የአድዋ ድል ነበር፡፡ አፍሪካውያን ብረት አንስተው ለነጻነታቸው ተዋግተዋል፡፡ ኋላም ከቅኝ ገዢዎች ነጻ ወጥተዋል፡፡ በነገራችን ላይ  በቅርቡ በየካቲት ወር 2013 ዓ.ም. አጼ ምንሊክ በሰጡት ብልህ አመራር ኢትዮጵያ በአድዋን ጦርነት ፋሺስት ጣሊያንን ድል መንሳቷን ያልዘነጋው ታዋቂውና ስመጥሩው የኡጋንዳው ማካራሬ ዩንቨርስቲ የአድዋን ድል የሚዘክር ሲምፖዚየም በማዘጋጀቱ  ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ( በዚህ አለም አቀፍ ሲምፖዚዬም ታዋቂ የአፍሪካ የታሪክ ሰዎች ጽሁፍ ማቅረባቸውን፣ ኢትዮጵያን የወከሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖችም መታደማቸውን ልብ ይሏል፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው (እንደምንገዘበው) ዳግማዊ አጼ ምንሊክ ስትራቴጂስትና ጎበዝ መሪ ብቻ አልነበሩም፡፡ እርሳቸው ልበ ርሁሩሀ፣ ፈሪሃ እግዜአብሔር ያደረባቸው፣ የሰውን ስሜት በከፍተኛ ደረጃ መግዛት የሚችሉ ታላቅ ንጉስ ነበሩ፡፡

It is significant that Menelik was not only a strategist and intelligent leader. He was also kind-hearted, God-fearing, and had a strong ability to influence people on an emotional level (high EQ):

አጼ ምንሊክ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቧ ከሰሩት በርካታ ቁምነገሮች ባሻግር ፣ ደግና ልበ ርሁሩሩ መሪ ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን በዚህ አስተያየት የማይስማሙ ግለሰቦች ሊኖሩ ቢችሉም፣ አጼ ምኒሊክ እጅግ በተለየ ሁኔታ ደግ እና ለሰው አዛኝ መሪ እንደነበሩ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ታሪክ አይሸፈጥም፡፡ ለእርሳቸው ደግነት አንዱ ማሳያው ወይም ደግ እንደነበሩ ለማሳየት፣የእምባቦ ጦርነትን እንደ ታሪክ ምስክርነት ማቅረብ ይቻላል፡፡ በእምባቦ ጦርነት በአጼ ምንሊክ ጦር እና በንጉስ ተክለሃይማኖት ጦር መሃከል የተካሄደ ጦርነት እንደነበር ከታሪክ እንማራለን፡፡ አጼ ምንሊክ ከንጉስ ተከለሃይማኖት ጋር ያደረጉት ደም አፋሳሽ ጦርነት፣ በታሪክ የእምባቦ ጦርነት በመባል ይታወቃል፡፡ በእምባቦ ጦርነት አሸናፊው አጼ ምኒሊክ ሲሆኑ ተሸናፊው ደግሞ ንጉስ ተክለሃይማኖት ነበሩ፡፡ በጦርነቱ ማብቂያ ላይ የጎጃሙ ንጉስ ተክለሃይማኖት ቆስለው የተማረኩ ሲሆን፣ ምኒሊክ ግን እንዲታከሙ በማድረግ ከሌሎች ምርኮኛ ወታደሮቻቸው ጋር አብረው ምህረት አድርገውላቸዋል፡፡ ለንጉስ ተክለሃይማኖት ምህረት ከማድጋቸው በፊት አንተ እኔን ብትማርክ ምንታደርግ ነበር ብለው ላቀረቡላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ እገድልህ ነበር የሚል ምላሽ እንደሰጡ ከተለያዩ የታሪክ መጽሐፍት እንዳነበብኩ አስታውሳለሁ፡፡ ደጉ ንጉስ ግን አልተቀየሙም ነበር፡፡ ስልጣን ሰጥተው ነበር የለቀቋቸው፡፡ በሌላ በኩል የወላይታውን ንጉስ ጦናን በጦር ሜዳ ድል ከነሱ በኋላ መልሰው የወላይታ ንጉስ አድርገው እንደሾሟቸው፣ በወታደሮቻቸው የተዘረፉ እንሰሳቶችን እንዲመለስ ማድረጋቸውን ከታሪክ እንማራለን፡፡ የከፋ ንጉስ የነበሩትንም እንዲሁ በተመሳሳይ መልኩ፣ ምህረት አድርገውላቸው ነበር፡፡ ይህም ብቻ አይደለም በርካታ የከዷቸውን  ታላላቅ ሹሞቻውን ምህረት በመስጠት ደግነታቸውን በተደጋጋሚ ግዜ ያሳዩ ንጉስ ነበሩ፡፡ 

ክፍል ሁለት ሳምንት ይቀጥላል

Filed in: Amharic