>
5:26 pm - Monday September 15, 8651

በሬሳ ክምር መሀል በህይወት የተገኘው አሳዛኙ ህፃን!! (ስንታየሀ ታከለ)

በሬሳ ክምር መሀል በህይወት የተገኘው አሳዛኙ ህፃን!!

ስንታየሀ ታከለ

እናትና አባት እንዲሁም ዘመዶቹን በሙሉ ገድለውበታል፡፡ በምን አግባብ እንደተረፈ እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ ህጻኑ አስከሬን ልናነሳ ወደ ሟች ወገኖቻችን ባመራንበት ወቅት በደም የታጠበች እናቱ ጋ ሂዶ ጡት ይጠባል፡፡ ከስልሳ ሰወች አንድ ህጻኑ ተርፏል።  አባትና እናት እህትና ወንድሙ አንድ ላይ ታርደው ተጥለዋል። ህጻኑ ስለመሞታቸው እንኳን አያውቅም ነበር፡፡ እህትና ወንድሞቹ ተኝተዋል ብሎ በማሰብ እየሄደም ሊቀስቀስና አብሯቸው ሊጫወት ይሞክራል። ነገር ግን ሁሉም ትተውት ሂደዋል። በዚህች መራራ ዓለም አራት እህትና ወንድም ሁለት እናትና አባቱን አጥቶ ከ60 አስከሬን አንድ ብቻውን እሱ ተርፎ ተገኝቷል።
 ህጻኑ እንኳን ማንነቱን ሊያውቅ ይቅርና ቤተሰቡ ማንቀላፋታቸውን እንጂ መገደላቸውን አያውቅም ነበር፡፡ ከእሱ ጋር በእድሜ ሚመሳሰሉትም አብረው ተገድለዋል። ይህ ህጻን እንዴት እንደተረፈ ቤተሰቦቹ ሲጨፈጨፉ የት እንደነበር አምላክ ይወቀው፡፡ ጨካኝና ሰው በላ አረመኔወች አቅፈን እናጫውትህ ቢሉት እንኳን እጁን ዘርግቶ እቀፉኝ የሚል ነው። ነገር ግን ከአማራው አብራክ ወጥቷልና የምህረት ዓይናቸው ታውሯል፡፡ ጀግንነታቸውም ያልታጠቀን ገበሬ ሴትና ህጻናትን በሰቅጣጭ ግድያ መግደል ነው። የእነሱ ጀግንነት ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ክልል ባለስልጣናት በዚህ ሁኔታ ይደሰቱ ይሆናል ነገር ግን በቀልም ይሁን ምህረት ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል!!
    ይህንን ህጻንና መሰል ወገኖቻችንን ለመታደግ በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ያለነው አንድም ከቦታው ርቀት ሁለተኛም የኦሮሙማው መንግስት ክልሉን በ30+ ዙር የሰለጠነውን ጦሩን ድንበር ላይ በዝግ አሳጥሮ ነው፡፡ አማራው አጸፋ ሚሰጥ ከሆነ ኦነግ ወደ ጫካው ገብቶ በምትኩ የኦሮሞ ልዩ ሀይል መሳሪያ ገፈፋ በሚል ህዝባችንን በህጋዊ ሽፋን መልኩ ይጨፈጭፋል።
በዘመነ ወያኔ አክሱም ወይም ሽሬ ላይ የአማራ ህዝብ ቢጨፈጨፍ እዚያው ድረስ ገብቶ መታደግ እንደማይቻል ሁሉ በመተከልና ወለጋም እንዲሁ በንቀት ታይቶ ከክልል ክልል የመሻገሩን ሁኔታ  እንኳንስ የኦሮሞ ልዩ ሀይል ~ህይወቱን(ተቋሙን) የታደግነው የሀገር መከላከያ ለኦነግ አንቀላፍቶ እያሳለፈ ህዝባችንንም እያስጨፈጨፈ አማራው ተደራጅቶ ራሱን ሲከላከል ፈጥኖ የደረሰ በማስመሰል ውጊያውን ከአማራው ገበሬ ጋር የሚያደርግ ስብስብ ነው። ስለዚህ መንግስታዊነትን እንደ ሽፋን እየተጠቀሙ ያሉ ኦነጋዊ አመራሮች ሚከሽፉት የቆሙበትን ስርዓት ስንንጠውና ስናፈርሰው መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል።
 ማስታወሻ
ሀዘን ነጋሪ የሆንነው በእድሜ ከእኛ ሚበልጡ ታላላቅ ወንድምና እህቶች እናትና አባቶቻችን ቀድመው የአማራውን ህልውና የሚያስጠብቅ ተቋምና ስርዓት  ባለመስራታቸው እንጂ ይህ አዲሱ ትውልድ የሆነበትን በፍጹም አይረሳም!!
Filed in: Amharic