የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በጊዜ ከአገር ክህደት ተግባሩ እንዲታቀብ ይደረግ…!!!
በሙሉዓለም ገ/መድኅን
(ፎቶ⇑አዲሱ የትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ኃላፊ ሌ/ጀኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ነው)
“የአገሪቱን የፖለቲካ ሥልጣን የጨበጠው የብልጽግና ፓርቲ ሸሪክ የሆነው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለአፈንጋጩ የህወሓት የዲፕሎማሲ ቡድን በግልጽም በስውርም ከሚያሰራጭበት የአገር ክህደት ተግባሩ እንዲታቀብ ማድረጉ ተገቢ ነው።
እንዲሁም ከትላንት በስቲያ የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዋና ኃላፊ ተደርገው የተሾሙት ሌ/ጀኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል በቅርብ ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው በሚመራው የህወሓት ሽምቅ ተዋጊ ላይጨክነው ‘እርምጃ ይወስዳሉ’ ብሎ ማሰብ፣ በተከፈለው መስዋዕትነት መሳለቅ ነው።
መንግሥት ጀኔራሉን በዚህ ዐይነቱ ከባድ ኃላፊነት ላይ ማስቀመጡ፣ የመታነቂያ ገመዱን በገዛ ፍቃዱ ማቀበል መሆኑን በማስታወስ፣ ስህተቱን በፍጥነት እንዲቀንስ አበክረን እንጠይቃለን። በነገራችን ላይ፣ ለረዥም ጊዜ የመከላከያ የመረጃ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ሌ/ጀኔራል ዮሃንስ፣ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ህወሓት የፈፀመውን ወንጀል በሙሉ የሚጋሩና በሕግ የሚያስጠይቃቸው መረጃዎች እንዳሉ ይታወቃል። በተቀረ፣ “የአገሩን ሰርዶ፣ በአገሩ በሬ” ዐይነቱ ቁማር ለሕወሓት ሰዎች ሰርቶ አለማውቁን ከድርጅቱ የ46 ዐመት ታሪክ መረዳት ብልህነት ነው።”
~
ይላል ከዛሬው የፍትህ መጽሔት ርዕሰ አንቀጽ የተቀነጨበው ወሳኝ መልዕክት። በዚህ አጋጣሚ ዝግጅት ክፍሉ ለያዘው አቋም ምስጋና ይገባዋል!
~
በብዙዎቹ የትግራይ ብሔርተኞች Globally Minded General የሚባልለት ይህ ሰው፣ ትግሬ African Jewish ነው ብሎ የሚያምን፣ ከእኩልነት ይልቅ የቀዳሚነትና የበላይነት ልክፍት ያለበት ሰው ነው። የመከላከያ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ እያለ ከኦጋዴን እስከ ጋምቤላ ድረስ የተፈፀሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን ቅድመ-ጥናት በመስራት ቀዳሚው ሰው ነው። [1994] በጋምቤላ የአኝዋክ ተወላጆች ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል ‹‹Operation Sunny Mountains›› ሪፖርት ብትበረብር ሰውየውን ፈልገህ አታጣውም። ሰውየው ከስብሃት ነጋ ጋር የጥቅም እንጅ የዓላማ ልዩነት አልነበረውም፤ ከሳሞራ ጋር የወንበር መገፋፋት እንጅ የአካሄድ ችግር አልነበረበትም። ከታደሰ ወረደ በዕድሜ ካልሆነ በትግራይ ጉዳይ በአስተሳሰብ ደረጃ ለይተህ ልታያቸው አትችልም።
እናም፣ ይህን ሰው የትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ኃላፊ አድርጎ መሾም ዳግማዊ ጥቅምት 24ን ከመጋበዝ የሚለይ አይለይም። ከተሳካለት መፈንቅለ መንግሥት ካልሆነለት ተከዜን ተሻግሮ የሚገባ ሰርጎ ገብ ኃይል ማዝመቱ ተገማች ነው። የዛሬም ሆነ የነገ መዳረሻ ህልማቸው ወልቃይትን የጦርነት ሜዳ ማድረግ ነው። የሰውየው ሹመት ከታለመለት [መደበኛዋን ትግራይ] የሠላምና ማረጋጋት ተልዕኮ መስመሩን ስቶ ለተከዜ ወዲ ማዶ ሰርጎ ገብ መልማይ እንዲሆን ዕድል አግንቷል።
ነገሩን በትህትና እንየው ከተባለ ይህ መደባ ዘመናዊውን counterinsurgency Model ግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ይችላል። በዚህ ሞዴል The aim of the war is to gain the support of the population rather than control of territory [የጦርነቱ ዓላማ ግዛት ከመቆጣጠር ይልቅ የሕዝቡን ድጋፍ ማግኘት ነው]
ሌ/ጀኔራል ዮሃንስ የትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ኃላፊ ተደርጎ ሲሾም የሕዝቡን ተቀባይነት እናገኛለን በሚል ስሌት ይመስላል። እውነታው ግን ይህ ሰው የትግራይን ሕዝብ ለዛሬው መከራ የዳረገው አስተሳሰብ ተሸካሚ የነበረ መሆኑ ነው። በእኩልነት ያለማመንና የመሬት ረሃብ የወለደው የተስፋፊነት አስተሳሰብን ከፈጠሩት አንዱ የሆነው ይህ ሰው የመፍትሄው አካል ሊሆን አይችልም። ይህ ፍርድ ወይም የጅምላ ጥላቻ ሳይሆን በተግባር የተፈተነ እውነታ ነው።
~
በመጨረሻም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሀገር የመምራት ኃላፊነት እጁ ላይ ያለው ገዥው ፓርቲ፣ የፖለቲካ አመራሩ በሁሉም የፀጥታና የፖለቲካ ተቋማት ላይ አይን እና ጆሮ ሊኖረው ይገባል። በፖለቲካ አመራሩ ዝንፈት ሰራዊቱ ዳግም ከጀርባው ሊወጋ አይገባም። ‘አምስተኛ ረድፈኞችን’ መመንጠር ለነገ የማይባል የቤት ሥራ ነው። ሚናውን ያልለዬ መሀል ሰፋሪም ሆነ የጠላት አስተሳሰብ ተሸካሚ (የሲቭልም ሆነ ወታደራዊ) አመራር በኃላፊነት ማስቀጠል ለሀገረ-መንግሥቱ ህልውና አደጋ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
–
የወልቃይት ጠገዴና ራያ ጉዳይ የተዘጋ ፋይል መሆኑ ታውቆ ለዕውቅናው ሴሪሞኒያል ነገሮች ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ውጭ ወደ ኋላ መንሸራተቱ ማዕከላዊ መንግሥቱን የበዛ ዋጋ ያስከፍለዋል። እናም የማይታሰበውን አለመሞከር የብልህ አስተዳደር ውሳኔ ነው።
–
በተረፈ የሚዲያው ሚና በኮምኒኬሽን ፕሮቶኮል የሚመራ፣ የዘመኑን Infornation Wars ባህሪያትን ያገናዘበ፣ ስትራቴጂክና ታክቲካል አጋሮችን የለዬና ያሰለፈ (ጠላት ላይ በጋራ የመዝመት antithesis approach) መርህ ሊከተል ይገባል። ይህ ከዜና እስከ ቃለመጠይቅ፣ ከትንታኔ እስከ ዘጋቢ ፊልም፣ … ዝግጅት ድረስ የተናበበ አጀንዳ መፍጠርን/ማጥቃትን ዓላማ ያደረገ (crosscutting issues with in mainstream medias) አሰራር መከተልን ይጠይቃል። አጀንዳዎች ከአንድ ማዕከል ወደዬ ሚዲያዎች የሚሰራጩበት አሰራር መፍጠር ካልተቻለ የዲፕሎማሲውን ክፍተት ይበልጥ ተጋላጭ ያደርገዋል። የዲፕሎማሲ ቅርቃሩን በአጭር ጊዜ መፍትሄ መስጠት የሚቻል አይደለምና አንጻራዊ የመረጃ/አጀንዳ ብልጫ ለመውሰድ የሚዲያ ቅኝቱ ከማዕከል ጋር የተያያዘ አሰራር ሊኖረው ይገባል። በተለየ ሁኔታ የትግራይ ቲቪ የፕሮግራም ይዘት ደጋግሞ መፈተሽ ይበጃል። በስምንት ቀን ‘የኩሪፍቱ ሪዞርት’ የገባ ወጣ ሥልጠና የሠላሳ ዓመት ትህነጋዊ የሚዲያ ቅኝት ሊስተካከል እንደማይችል አለመርሳት ይመከራል። እነዚያ እቡይ ጋዜጠኞች በአንድ ሳምንት ሥልጠና የአመለካከት ለውጥ ያመጣሉ ብሎ መጠበቅ በራሱ ያስገምታል!!
–
ዘርፈ ብዙ ብዙ ጦርነት ውስጥ ነውና ያለነው ከአመራር ሚና አኳያ ‘መንግሥት አለመሆን ይቅርታ የማያሰጥ ጥፋት ነው’ at any cost መንግሥት “መንግሥት” ሆኖ መገኘት አለበት።
[The State Security apparatus actions determine the fate of Ethiopia. If He will be a real ‘Statesman’, Rather than Project Manager activities, Abiy should straddle the Political & Security Structures.]