መግለጫው የኦነግ ጦር የሚባለው፣የማን ጦር እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው!!!!!
አቻምየለህ ታምሩ
ወለጋ ውስጥ ያ ሁሉ አማራ በቤቱና በቤተክርስቲያን ውስጥ ተከልሎ ድረሱልኝ እያለ የሚደርስለት አጥቶ በኦነግ ጦር ሲፈጅ አንዳች ነገር ትንፍሽ ያላለው በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ፓርቲና ሺመልስ አብዲሳ የሚመራው ክልል፤ የኦነግ ጦር አማራ ክልል በሚባለው ውስጥ ገብቶ በአጣዬና በከሚሴ ወረራና ፍጅት ሲፈጽም ይህንን የኦነግ ወረራና ፍጅት የሚከላከለውን የአማራ ልዩ ኃይል በጦር ወንጀለኛነት የሚከስ መግለጫ ማውጣቱ፤ አንድም የኦነግ ጦር የሚባለው የማን ጦር እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው፤ ሁለትም ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ፓርቲና ሺመልስ አብዲሳ የሚመራው ክልል በሚያስተዳድሩት ወለጋ ውስጥ አማራ ድረሱልኝ እያለ የሚደርስለት አጥቶ ያ ሁሉ ፍጅት በአማራ ተወላጅነቱ ብቻ ሲካሄድበት ከሚሴና አጣዬ ላይ ኦነግ ተነካብን ብለው በወገናዊነት ስሜት እንዳረጉት እንኳን ባይሆን ለይስሙላ ያህል መግለጫ ያላወጡት የወለጋ የአማራ ተወላጆች የኛ ወገን ናቸው ብለው ስለማያስቡና የሚፈጸምባቸውም ግፍ የማይሰማቸው በመሆኑ የወለጋ አማራ ፍጅት በኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ፓርቲና ሽመልስ አብዲሳ በሚመራው ክልል እውቅና እየተካሄደ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው።