>
5:13 pm - Sunday April 19, 8787

"በጭንቅ ቀን የመጣ ንጉሥ - አጼ ዓምደ ጽዮን" (ጸጋው ማሞ)

“በጭንቅ ቀን የመጣ ንጉሥ – አጼ ዓምደ ጽዮን

ጸጋው ማሞ

 “The kingdom of Ethiopia shall endure  till the coming of christ ”  አፄ ዓምደ ጽዮን
   
” ኢትዮጵያ አትፈርስም” ይላሉ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ … ግራ የሚያጋባ  እና የሚያስጨንቅ ንግግር ነው ። አንዳንድ ጊዜም ፌዝም ይመሥለኛል ። 
ንጉሥ አምደጽዮን  ደግሞ  “The kingdom of Ethiopia shall endure  till the coming of christ ” ኢትዮጵያ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ለፍርድ እስኪመጣ ትቀጥላለች ይላል ። የአምደጽዮን አሳምኖኛል ሰርቶ አሳይቶኛል…የአምደጽዮን ንግግር ዐብይ አሕመድን ይሸፍነዋል ወይም ያሻግረዋል ነገር ግን  ጭንቁና እልቂቱም አይዘነጋም ። 
 
         ዓምደ ጽዮን  
         ======
 ሀገሪቷ በአራቱም አቅጣጫ  ጭንቅ በሆነችበት በዚያን ወቅት ፤ የጦርነት ነጋሪት በሁሉም አቅጣጫ ሲጎሰም…  በምዕራብ የቤተ እስራኤላውያን አመጽ ፣ በሰሜን የእንድርታው ያእብቃ እግዚእ አመጽ ፣በደቡብ የሲዳማ አመጽ ፣ በምስራቅ  በአረቦች የሚታገዘው የይፋት ፣ የአዳል እና የሞራ የእስላማዊነት  የአመጽ እንቅስቃሴ ሃገሪቷን  ሰቅዞ በያዛት በዚያን ወቅት ፤ ዓምደ ጽዮን ደግሞ ኢትዮጵያን ለማዳን  ተጉለት ላይ ይመክር ነበር ። ያልተነገረለት ፣ ያልተዘመረለት ኢትዮጵያን የሠራ ፣ ቆፍጣና  የጀግንነት ልክ ማሳያ ፣ የቁርጥ ቀን  ልጅ የጭንቅን ቀን ያዘገየ ኢትዮጵያዊ  ንጉሥ ነው ። ኢትዮጵያ አሁን ትኖር ዘንድ ዓምደ ጽዮን መኖር ነበረበት ።
   —————-
     ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪው ኘሮፌሰር  Edward Ullendorff  እንዲህ ይላል ” Amde seyon was one of the most outstanding Ethiopian kings of any age and singular figure  dominating  the horn of Africa ”  አምደ ጽዮን በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ  የሌለው ጀግና መሪ እንደነበር ሲመሰክር ።  ኘሮፌሰር  ታደሠ ታምራት  ደግሞ “Amdetsion reign is one of the most important formative period in the religious ,Literacy  and poletical history ”  ሥልጡን የፖለቲካ ፣ የሀይማኖት እና የሥነጽሑፍ  ዘዋሪ መሐንዲስ  እንደሆነ ይመሠክሩለታል ።
ኢትዮጵያ ትቀጥላለች 
  ( አምደጽዮን)
ጥቂት የሠለጠኑ ልዩ ኃይሎች (special force) አዘጋጀ ። ለምሳሌ  ተኩላው (The strong ) ፣ ኮረም (ፈረሰኞቹ)  ፣ ቀስተ ንሕብ ፣ ጎጃም ፣አማራ ፣ዳሞት ፣ ሃድያ ፣ጎንደር  በሚባሉ ሲበዛ  ሥልጡንና በራሳቸው የሚተማመኑ ጦረኞችን  በፍጥነት አዘጋጅቶ አንድ አመት  ከሁለት ወር  በፈጀ ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ  ከቀይ ባሕር እስከ ዘይላ  እና ከዘይላ የሕንድን ውቅያኖስ  እያካለለ እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ  ትጥቃቸውን ሳይፈቱ በአረቦች የሚመራውን ኃይል በማደባየት በዘመኑ በኢትዮጵያችን ላይ  የተደገሰውን የመበታተን ተልእኮ በድልና በኩራት ተወጥቶአል ። ይሕንን ድንቅ ድል የሰሙ  እንዲሕ በማለት በግእዝና በአማርኛ ተቀኙለት
ሐርበኛ ዓምደ ጽዮን መላላሽ የወሰን ፣
ወሀ እንደ መስን መላላሽ የወሰን ፣
.
.
የወንዶች ገራገራ፣
በሐድያ እስከ ጉዴላ፣
በባሕር እስከ ኤርትራ፣
አምደ ጽዮን ሥም የዘራ ። የ14ኛው ክ/ዘ ግጥም ነው
ዓምደ ጽዮን ሲበዛ ጥቃትና በደልን አይችልም… የኢትዮጵያዊነት ደመ ቁጡነት ማሳያ  ነው ።  ለጦርነት የሚወጣው በደል  ገፍቶት እና  ከፈጣሪውም ጋር ተማክሮ ነው ።  በመጀመሪያ በታቦቱ ፊት ተንበርክኮ  ይጸልያል ። የኢየሱስ  ክርስቶስ መላእክ ከፊቱ እንደሚቀድም ያምናል ፤ ንግስቲቷና ቀሳውስቱ  በመቅደሱ ውስጥ የተስፋይቱ ምድር ለትውልድ ትቀጥል ዘንድ ካለማቋረጥ  በጸሎት ይተጋሉ ።  አምደ ጽዮንም ለወታደሮቹ እንዲሕ ይላቸዋል “be not Afraid in the face of rebels, for the God of the christians will help us and he will save as from their hands ”  Hunting ford  page 89
ይቀጥልና አሁን የምትዋጉት ለእኔ ወይም ለወርቅና ለብር አይደለም ለኢየሱስ ክርስቶስና ለሕዝቡ ነው ። ” ሰይፋችሁን ታጠቁ ፣ልባችሁን አጽኑ ፣…እኔ ግን በአምላኪዬ  በእግዚአብሔር ልጅ  በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ድል ሳላደርግ… እንዳልመለሥ ሠማይንና ምድርን በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ምያለሁ ልቤንም  በክርስቶስ ጸንቶአል ”   ይላል  “…ከይኩኑ አምላክ እስከ ልብነ ድንግል ገጽ 80
 ይሕን በማለት እቅጩን ተናግሮ ኢትዮጵያን ከመበጣጠስ ወይም ከአረብ ቅኝ ግዛትነት አዳናት ።
 በራስ የመተማመን ጥግ ፣በፈጣሪው የመታመን ልክ  ፣ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፣ የሃገር ፍቅር ልክፍት በአጼ አምደ ጽዮን  ደም ውስት ሲፈላና ሲተገበር ይታያል ።
አሑን ላይ አምደጽዮናዊነት የሚጠየቅበት እና   የሚተገበርበት ጊዜ  ይመሥላል ። የተሥፋይቱ ምድር  የአውሮፓና የአረቦች የውክልና ጦር ሜዳ ከምትሆን አምደጽዮናዊነትን ማማጥና መውለድ  ፍቱን መድሐኒት ነው ።
Filed in: Amharic